Prosperity Party Dire Dawa Construction Bureau

Prosperity Party Dire Dawa Construction Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Prosperity Party Dire Dawa Construction Bureau, Political organisation, Dire Dawa.

12/08/2026
28/07/2026

#ዜና /በድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታቸው የተጠናቀቁ 548 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ሐምሌ 28 እንደሚካሄድ ተገለፀ

ሐምሌ 21/2018

በድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪ መንደር 3 ተኛ ሳይት ላይ ተገንብተው የተጠናቀቁ 17 ብሎኮች አጠቃላይ 548 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 28 እንደሚካሄድ ተገለፀ ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢማጅ አብደላ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት ከዚህ ቀደም የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ ሐምሌ 4 እንደሚካሄድ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በወቅቱ ሶፍትዌሩ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ቀኑ መራዘሙን አስታውቀዋል ።

ሶፍትዌር ላይ ያጋጠመው ብልሽት አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስተካክሎ አቶ ኢማጅ አስታውቀው የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 28 የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል ።

የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችም የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 28 ኤርፖርት መሄጃ አካባቢ ባለው የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከጠዋቱ 3 ሰዓት አንስቶ በመገኘት የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱን መከታተል እንደሚችሉና በእለቱም መገኘት የሚይችሉ በተለያዩ ሚያዎች በቀጥታ ስርጭት መከታተል እንደሚችሉም ነው አቶ ኢማጅ ያስታወቁት ።

በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በሰላም አበበ
ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DGCOMU
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB
ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

03/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፀጥታ ኃይል አካላት እንዲሁም ሕዝቡ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለተወጡት ሀገራዊ ኃላፊነት እና ላሳዩት ፅናትም ምክር ቤቱ ያለውን ምስጋና እና አድናቆት ገልጿል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ “ልዩነቶቻችንን እና ችግሮቻችንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመፈታት በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል የበኩላችንን ሚና እንወጣ፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም” ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

26/05/2026

Address

Dire Dawa

Telephone

+251915048530

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity Party Dire Dawa Construction Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Prosperity Party Dire Dawa Construction Bureau:

Shortcuts

Share