26/07/2026
የደመወዝ ማሻሻያ እና የፍትሐዊ ግብር ጥያቄ!📢 ለመላው የመንግሥት ሠራተኞች እና ዜጎች የተደረሰ የድምፅ ማሰባሰቢያ ጥሪ!
ለሠራተኛው ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ እፎይታ የሚሰጥ፡ የደመወዝ ማሻሻያ እና የፍትሐዊ ግብር ጥያቄ!
አሁን ላይ የመንግሥት ሠራተኛው የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ ከወቅታዊው የገበያ ዋጋ እና ከኑሮ ውድነቱ ጋር ፈጽሞ ሊቀራረብ አልቻለም። ያለውን ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በመጀመሪያ የሠራተኛው ደመወዝ ከወቅቱ የኑሮ ውድነት ጋር የሚመጣጠን ማሻሻያ ሊደረግለት ይገባል!
ከዚህም በተጨማሪ የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ያገናዘበ የሚከተለው የፍትሐዊ ግብር ስሌት ቢተገበር ለሠራተኛው ትልቅ እፎይታ ይሆን ነበር፦
🔹 5% 👉 በዝቅተኛ ደመወዝ (ከ 10,000 - 20,000 ብር)
🔹 10% 👉 በመካከለኛ ደመወዝ (ከ 20,001 - 35,000 ብር)
🔹 15% 👉 በከፍተኛ ደመወዝ (ከ 35,001 - 55,000 ብር)
🔹 20% 👉 በጣም ከፍተኛ ደመወዝ (ከ 55,001 - 80,000 ብር)
🔹 30% 👉 እጅግ በጣም ከፍተኛ ደመወዝ (ከ 80,001 ብር በላይ)
💡 ይህ ጥያቄ ለምን አስፈለገ?
አሁን ባለው የስራ ግብር ተመን ዝቅተኛ ደመወዝ የሚያገኘው ሠራተኛ ላይ የሚጣለው ግብር እና አጠቃላይ የኑሮ ጫና ተመጣጣኝ አይደለም። ደመወዝ ተስተካክሎ፣ ግብር በዚህ መልኩ በፍትሐዊነት ቢሰላ፦
1️⃣ የሠራተኛውን የመግዛት አቅም ያጎለብታል፣
2️⃣ በስራ ላይ ያለውን ተነሳሽነት ይጨምራል፣
3️⃣ የቤተሰብን መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ያግዛል።
ይህ ሃሳብ ፍትሐዊ እና ወቅቱን ያገናዘበ ነው ብለው የሚያምኑ ከሆነ ሼር (Share) በማድረግ ለሠራተኛው ድምፅ እንሁን!!
#የደመወዝማሻሻያ #ፍትሐዊግብር #የመንግሥትሠራተኛ #ኢትዮጵያ
📰 ለታማኝ መረጃ እና ለነገ ተስፋ!
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገጻችንን Follow,Like እና Share ያድርጉ!
Dire dawa City ✍️