Dire Dawa Adm. Code Enforcement Office

Dire Dawa Adm. Code Enforcement Office ደንብና ስርዓት የሚከበርባት ጽዱ: ውብ: ማራኪና ለኑሮ ተስማሚ ድሬደዋ::
Clean, Beautiful, Attractive and suitable City.

15/12/2023

#ለመረጃ ያህል
ቅዳሜ በቀን 6/2016 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር ነዳጅ የሚገኝባቸው ማደያዎች ስም ዝርዝር፦

ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም
ን/ኢ/ኢ/ቢሮ ህዝብ ግንኙነት

የክላስተር/ቡድን ሁለት የደንብ አስከባሪ አባላትና አመራር በቀፊራ የአትክልት ገበያ ዙሪያ ህገ-ወጥ የጎዳና ላይ ንግዶችን በመቆጣጠር ላይ ናቸው::  #የጎደና ላይ ንግዶች በመንግስት: በመንገ...
15/12/2023

የክላስተር/ቡድን ሁለት የደንብ አስከባሪ አባላትና አመራር በቀፊራ የአትክልት ገበያ ዙሪያ ህገ-ወጥ የጎዳና ላይ ንግዶችን በመቆጣጠር ላይ ናቸው::
#የጎደና ላይ ንግዶች በመንግስት: በመንገድ አጠቃቀምና በተሽከርካሪዎች ላይ ከሚያስከትሉት ችግር ባሻገር የሚሸጡበት ቦታና የአያያዝ ሁኔታ በተጠቃሚው ሊያስከትል የሚችለው የጤና ችግር ምን እንደሆነ ወደፊት በዝርዝር የምናቀርብ ይሆናል::
#የደንብ ጥሰትንና ህገ-ወጥነትን በጋራ እንከላከል!

14/12/2023
ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን የመከላከል ስራ በመደበኛ የክትትልና ቁጥጥር ደንብ አስከባሪ አባላት በተለያዩ ወረዳዎች እየተከናወነ ይገኛል:: #የክላስተር ሁለትና ክላስተር ሶስት ደንብ አስከባሪዎች...
14/12/2023

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን የመከላከል ስራ በመደበኛ የክትትልና ቁጥጥር ደንብ አስከባሪ አባላት በተለያዩ ወረዳዎች እየተከናወነ ይገኛል::
#የክላስተር ሁለትና ክላስተር ሶስት ደንብ አስከባሪዎች የተሰሩ ስራዎች::

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን በጅምሩ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በአሰሊሶ ወረዳ ስር በሚገኙ የከተማ አዋሳኝ ቀበሌዎች የተወረሩ መሬቶችን ከህገ-ወጥ ግንባታ ነጻ የማድረግ ስራ:: #የልዩ...
14/12/2023

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን በጅምሩ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
በአሰሊሶ ወረዳ ስር በሚገኙ የከተማ አዋሳኝ ቀበሌዎች የተወረሩ መሬቶችን ከህገ-ወጥ ግንባታ ነጻ የማድረግ ስራ::
#የልዩ ኦፕሬሽን የደንብ አስከባሪ አባላት ከመልካጀብዱ ፖሊስ ጋር እየተሰራ የሚገኝ ጥሩ ስራ::

የመንገድ ላይ/የመንገድ ዳር ጥቃቅን ህገ-ወጥ ንግዶችን የመከላከል ስራ ሰፊ የማስተካኪያና የእርምት እርምጃ የተወሰደበት ዘርፍ ነው:: ሆኖም ከዘርፉ ባህሪና ከሚያስከትለው ችግር አንጻር በየእ...
14/12/2023

የመንገድ ላይ/የመንገድ ዳር ጥቃቅን ህገ-ወጥ ንግዶችን የመከላከል ስራ ሰፊ የማስተካኪያና የእርምት እርምጃ የተወሰደበት ዘርፍ ነው:: ሆኖም ከዘርፉ ባህሪና ከሚያስከትለው ችግር አንጻር በየእለት በተመረጡ ቦታዎች በትኩረት የመከላከል ስራ እየተሠራ ይገኛል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የማህበረሰባችንን ግንዛቤ የማሳደግ ተግባር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ በቅርቡ ወደ ተግባር የምንገባ ይሆናል::

ለአረንጓዴ ልማት የተለዩ የከተማ ቦታዎችን በማልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ከወሰዱ ብኃላ በህገ-ወጥ ግንባታ መውረርና ለንግድ አገልግሎት ማዋል በከተማ ደንብ የተከለከለና የሚያስጠይቅ ነው::...
13/12/2023

ለአረንጓዴ ልማት የተለዩ የከተማ ቦታዎችን በማልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ከወሰዱ ብኃላ በህገ-ወጥ ግንባታ መውረርና ለንግድ አገልግሎት ማዋል በከተማ ደንብ የተከለከለና የሚያስጠይቅ ነው:: በከተማችን ወረዳ 3 ነምበርዋን አካባቢ የባቡር ሀዲዱን ተከትሎ ባለው ክፍት ቦታ አጠቃቀሙን በተመለከተ የሚታየውን ክፍተት የማስተካከል ስራ እየተሰራ ይገኛል::

የአስተዳደሩ ውስን ሀብት የሆነውን መሬት ከስግብግብ ደላሎችና ከህገ-ወጥ ወረራ የመከላከል ስራ በጠንካራ ቅንጅት እየተከናወነ ይገኛል:: የከተማ ማስፋፊያ በሆኑ የገጠር ቀበሌዎች የአርሶ አርብ...
13/12/2023

የአስተዳደሩ ውስን ሀብት የሆነውን መሬት ከስግብግብ ደላሎችና ከህገ-ወጥ ወረራ የመከላከል ስራ በጠንካራ ቅንጅት እየተከናወነ ይገኛል::
የከተማ ማስፋፊያ በሆኑ የገጠር ቀበሌዎች የአርሶ አርብቶ አደሩን እርሻና የግጦሽ መሬት በህገ-ወጥ መንገድ በመውረር እየተገነቡ የሚገኙ የተለያዩ ህገ-ወጥ ግንባታዎችን ላይ እርምጃ ተወስዷል:: ይህን ስራችን ከፖሊስና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አጠናክረን የምንቀጥል ሲሆን አርሶ አርብቶ አደራችን እንዲሁም አጠቃላይ ነዋሪ በአጭበርባሪ ደላሎች እንዳይታለል ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን::

በከተማችን እየተከነወኑ የሚገኙ መጠን ሰፊ የኢንቨስትመንት ልማት ስራዎች የሚገኙ ቢሆንም የግንባታ ግብዓቶችንና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በመንገድ መሠረተ ልማቶች: በተሸከርካሪዎችና በማህበረሰ...
04/12/2023

በከተማችን እየተከነወኑ የሚገኙ መጠን ሰፊ የኢንቨስትመንት ልማት ስራዎች የሚገኙ ቢሆንም የግንባታ ግብዓቶችንና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በመንገድ መሠረተ ልማቶች: በተሸከርካሪዎችና በማህበረሰቡ ጉዳት በማይስከትሉበት አግባብ መያዝና መጠቀም እንዲሁም የከተማው ጽዳትና ውበት/ገጽታ ላይ ችግር በማያስከትሉበት አግባብ መጠቀም ይገባል:: የደንብ ማስከበር ጽ/ቤትና የግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን በቅንጅት ወደ ስራ በመግባት የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የግንዛቤና የክትትል ስራ በወረዳ 03 የተጀመረ ሲሆን ግንዛቤ አግኝተው በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ማስተካኪያ በማያደርጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ በከተማው ደንብ የመወሰድ ስራም እየተከናወነ ይገኛል::
ስራው በሌሎች ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው ወረዳዎችም የሚቀጥል ይሆናል::

የከተማችንን ጽዱ: ውብና አረንጓዴ ለማድረግ በከተማው ደንብ መሰረት የ20/50 መመሪያ አተገባበር እንደቀጠለ ነው:: ቀደም ብለን ስመ ገናናዋ የከዚራ መንደር የሚገኙትን የንግድ ተቋማት በዚህ...
20/09/2023

የከተማችንን ጽዱ: ውብና አረንጓዴ ለማድረግ በከተማው ደንብ መሰረት የ20/50 መመሪያ አተገባበር እንደቀጠለ ነው:: ቀደም ብለን ስመ ገናናዋ የከዚራ መንደር የሚገኙትን የንግድ ተቋማት በዚህ አሰራር መሠረት ውል አስገብተን የነበረ ሲሆን አሁን በተጨባጭ ወደ ተግባር አስገብተን ጽዱ: ውብና ማራኪ እንዲሆን ተደርጓል:: ይህ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::

የአገልጋይነት ቀን በድምቀት አክብረናል::Guyyaa tajaajilamtoota haala miidhagaa taheen kabajn!
07/09/2023

የአገልጋይነት ቀን በድምቀት አክብረናል::
Guyyaa tajaajilamtoota haala miidhagaa taheen kabajn!

በቀበሌ 02 የሀሎሌ መንደር አካባቢ በዋና አስፓልት ላይ የእግረኛ መንገድን በመዝጋት ለንግድ ያዋሉ እርምጃ በመውሰድ የማስተካከል ስራ ተከናውኗል:: ሁሉም ነጋዴዎችና ሌላው ነዋሪ ከህጋዊ ይዞ...
22/08/2023

በቀበሌ 02 የሀሎሌ መንደር አካባቢ በዋና አስፓልት ላይ የእግረኛ መንገድን በመዝጋት ለንግድ ያዋሉ እርምጃ በመውሰድ የማስተካከል ስራ ተከናውኗል::
ሁሉም ነጋዴዎችና ሌላው ነዋሪ ከህጋዊ ይዞታቸው ውጪ ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳይሰጣቸው የግንባታ ግብዓት: ተረፈ-ምርት: በሸራ ወይም በቆርቆሮ ቅጥያዎችን መስራትና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማስቀመጥ ለግል ጥቅማቸው ማዋል የተከለከለና የሚያስቀጣ መሆኑን እናሳስባለን::

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Adm. Code Enforcement Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share