27/08/2026
ነሐሴ 21/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
የቢሮውን የህዝብ ክንፍና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ኡመር ዱአሌ ናቸው፡፡ የቢሮው ሃላፊም በመክፈቻ ንግገራቸው ያስተላለፉት መልዕክት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከርና ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት መስራት የተቋማትን ውጤታማነት ከማረጋገጡም በላይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ለአስተዳደሩም ሆነ ለአገራችን ልማት መፋጠን የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል የሚል ነው፡፡ የተቋሙን የህዝብ ክንፍ በማሳተፍ የልማት ሥራዎችን መሥራት ለውጤት የሚያበቃ መሆኑን ተናገሩት ሃላፊው በቀጣይም የተቋሙንና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር የሚያጠናክሩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡
የቢሮው የ2018 የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2019 የቁልፍና የአበይት ተግባራት ዕቅድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቀጣይ በጀት ዓመት 600 የጋራ መኖሪ ቤቶች ለመገንባት የሚያስችሉ ቅድመ ተግባራት መከናዎናቸው ታውቋል፡፡