28/08/2026
ዜና | የአምስቱ ተጎራባች ክልሎች የወጣቶች የምክክር መድረክ በመጪው ረቡዕ በድሬዳዋ መካሄድ ይጀምራል ::
| ነሐሴ 22 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
የአምስቱ ተጎራባች ክልሎች ማለትም የድሬዳዋ አስተዳደር፣ የሐረሪ፣ የአፋር፣ የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የምክክር መድረክ በመጪው ረቡዕ በድሬዳዋ ከተማ መካሄድ እንደሚጀምር ተገለጸ።
ይህ የተገለጸው መድረኩን በስኬት ለማጠናቀቅ በተደረገ የመጨረሻው ምዕራፍ ዝግጅትና መርሃ-ግብር አፈጻጸም ዙሪያ በተካሄደ ውይይት ላይ ነው።
የድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኻሊድ መሐመድ እንደገለጹት፤ የምክክር መድረኩ ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልካም ተግባቦት በማስተሳሰር ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለቀጠናው ሰላምና አብሮነት አያሌ ጠቀሜታዎችን ያበረክታል።
ወጣቶቹ በድሬዳዋ በሚኖራቸው ቆይታ ከምክክር መድረኩ በተጨማሪ፡
የችግኝ ተከላ እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ይሳተፋሉ፤
በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ።
በመጨረሻም የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ፤ ለተጋባዥ ወጣቶች ከሚደረገው አቀባበል ጀምሮ በድሬዳዋ በሚኖራቸው አጠቃላይ ቆይታ ዙሪያ ለተዋቀረው አስተባባሪ ኮሚቴ አስፈላጊውን አቅጣጫ ሰጥተዋል።