የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ/Dire Dawa Land Development and Management Bureau

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ/Dire Dawa Land Development and Management Bureau

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ/Dire Dawa Land Development and Management Bureau Land Adminsration and Land Related Services

በመሬት ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ለማሳደግ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።በድሬዳዋ አስተዳደር ከመሬት ዘርፍ የሚመነጨውን የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በተሻለ ሁኔታ ለማሰባሰብና የገቢ አፈጻጸምን ለ...
23/08/2026

በመሬት ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ለማሳደግ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

በድሬዳዋ አስተዳደር ከመሬት ዘርፍ የሚመነጨውን የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በተሻለ ሁኔታ ለማሰባሰብና የገቢ አፈጻጸምን ለማሳደግ ያለመ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው በመሬት ዘርፍ የሚመነጩ የገቢ ምንጮችን በአግባቡ መለየት፣ የገቢ አሰባሰብ ሂደትን ማጠናከር፣ የገቢ ግብ አፈጻጸምን በተገቢው መከታተል እና በመሬት አስተዳደር ሥራና በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጓል።

በመድረኩ በተለይም በቦታ ደረጃ የሊዝ መነሻ ዋጋና በስም ዝውውር ወቅት የሚያገለግለውን ወቅታዊ የተመን ዋጋ አሰራር በተመለከተ ለአመራርና ለሠራተኞች ሰፊ ገለጻ ተሰጥቷል።

የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ዳይሬክተር አቶ ረመዳን ሙሳ የመሬት ገቢን ለማሳደግ የአሰራር ማሻሻያዎችን መተግበር፣ የመሬት ልማትና አጠቃቀምን በተቀናጀ ሁኔታ መምራት እና የመሬት ሀብትን በውጤታማነት በመጠቀም ከመሬት የሚገኘውን ገቢ በሙሉ አቅም ማሰባሰብ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በተያዘው በጀት አመት ቢሮው 1.4 ቢልየን ብር ገቢን ለመሰብሰብ በእቅድ መያዙን የገለጹት ዳይሬክተሩ ለዚህም ስኬት መትጋት ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም የመሬት ገቢ አፈጻጸምን በቁጥርና በውጤት መለካት፣ የገቢ ክፍተቶችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፣ የገቢ ምንጮችን ማስፋት እንዲሁም በሥራው ላይ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ቅንጅትን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የተቋም ለውጥ አፈጻጸምና አገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ምዘና ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ አሜ፣ ስልጠናው የመሬት ዘርፍ ገቢን ከከተማዋ የልማት ፍላጎት ጋር በማጣጣም፣ የመሬት ሀብትን በአግባቡ በማስተዳደር ዘላቂ ገቢ ለማመንጨት የሚያስችል አቅም ለመገንባት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ተሳታፊዎችም በመሬት ዘርፍ የገቢ አሰባሰብና አስተዳደር ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት በስራ ላይ እያጋጠሙ የሚገኙ ክፍተቶችን በማንሳት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል።

በመጨረሻም የመሬት ዘርፍ ገቢ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ዋና አካል በመሆኑ፣ የገቢ አሰባሰብ ሥራን በተቀናጀ፣ በግልጽነትና በውጤታማነት ማከናወን የከተማዋን የልማት አቅም ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

ነሃሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

ሌሎችን የመርዳት ኃይል ዙሪያ የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ።በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ “ሌሎችን የመርዳት ኃይል” በሚል ርዕስ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጠ።የቢሮው ምክትል ኃላፊ...
21/08/2026

ሌሎችን የመርዳት ኃይል ዙሪያ የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ።

በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ “ሌሎችን የመርዳት ኃይል” በሚል ርዕስ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጠ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሁሴን ጌዲን በመክፈቻ ንግግራቸው ሌሎችን መርዳት የሰብዓዊነትና የማኅበራዊ ኃላፊነት መገለጫ መሆኑን ገልጸው፣ ሠራተኞች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ይበልጥ እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

ስልጠናውን ያዘጋጁት የሴቶች፣ ወጣቶችና ኤችአይቪ ክፍል ባለሙያ ወ/ሮ እህትአገኘው በቀለ በበኩላቸው ሌሎችን በእኩልነት፣ በክብርና በርኅራኄ መርዳት እንደሚገባ ገልጸው፤ በተለይም ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ መስጠት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አስረድተዋል።

በስልጠናው ሌሎችን የመርዳት ጽነሰ ሃሳቦች፣ የግልና የማኅበራዊ ጥቅሙን እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ድጋፍ ሲደረግ መወሰድ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ስልጠናው የሠራተኞችን የበጎ ፈቃድ መንፈስ በማጠናከር፣ ለሌሎች ያላቸውን የሰብዓዊነት እና ማኅበራዊ ኃላፊነት ስሜት ለማሳደግ ያለመ ነው።

ነሃሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በነዋሪዎች ተሳትፎ እየተከፈቱ ነው።በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ ሁለት በተለምዶ “ገንደ ተስፋ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቢሮው ቀደም ሲል ባመላከተው መሠረት የውስጥ ለው...
20/08/2026

የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በነዋሪዎች ተሳትፎ እየተከፈቱ ነው።

በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ ሁለት በተለምዶ “ገንደ ተስፋ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቢሮው ቀደም ሲል ባመላከተው መሠረት የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በነዋሪዎች ተሳትፎ እየተከፈቱ ይገኛሉ።

የውስጥ ለውስጥ መንገዶቹ ለረጅም ዓመታት የአካባቢው ነዋሪዎች ያነሱት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው ቆይተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮም የነዋሪዎችን ጥያቄ በመመልከት በሽንሸና ፕላን ጥናትና ዝግጅት መሠረት መንገዶቹን የማመላከት ሥራ ተከናውኗል።

የመንገድ ከፈታው ሥራ በቀጥታ ከመጀመሩ በፊትም ቢሮው ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማካሄድ የተመላከቱት መንገዶች በሕግና በፕላን መሠረት እንዲከፈቱ የሚያስፈልገውን ግንዛቤ ፈጥሯል።

ይህንንም ተከትሎ ነዋሪው በተመላከተው መሠረት በጋራ በመረባረብ የውስጥ ለውስጥ መንገዶቹን በራሳቸው እየከፈቱ ይገኛሉ።

በመሬት ይዞታ አስተዳደር ጽ/ቤት የሽንሸና ፕላን ጥናትና ዝግጅት ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም ሙሉጌታ እንደገለጹት በተመላከቱ መንገዶች ላይ ነዋሪዎች በጋራ በመረባረብ መንገዶቹን እየከፈቱ መሆኑ ህብረተሰቡ የራሱን አካባቢ በራሱ ለማሻሻል ያለውን ተሳትፎ፣ ባለቤትነትና የትብብር መንፈስ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመንገድ ከፈታው ሥራ የቢሮውና የነዋሪዎች የጋራ ትብብር ውጤት በመሆኑ በቀጣይም የተመላከቱ መንገዶች እንዲከፈቱ የሁሉም ወገን ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ነዋሪዎችም በቀጣይም የተመላከቱ መንገዶችን በጋራ ለመክፈት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም.

የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የማስተዋወቂያና የመፈራረሚያ መድረክ ተካሄደ።የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና...
20/08/2026

የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የማስተዋወቂያና የመፈራረሚያ መድረክ ተካሄደ።

የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የማስተዋወቂያና የመፈራረሚያ መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በመብት ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሐዲ መሐመድ ቀርቦ፣ በሪፖርቱና በዕቅዱ ላይ ሰፊ ውይይትና ግብዓት ተሰጥቷል።

በውይይቱም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት፣ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራን ከማሳለጥ፣ የአድራሻ ሥርዓትን ከመተግበር እንዲሁም ተደራሽና ዘመናዊ የመሬት አገልግሎት ከመስጠት አንጻር በ2019 በጀት ዓመት ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራት በዝርዝር ተዳስሰዋል።

የኤጀንሲው ሠራተኞችም በግብዓት፣ በአሠራርና ምቹ የሥራ አካባቢ ከመፍጠር አንጻር መሻሻል በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብና አስተያየታቸውን አቅርበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በ2019 በጀት ዓመት ለተገልጋዩ ማኅበረሰብ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በተቀናጀ መልኩ መረባረብ እንደሚገባ ተገልጿል።

የካዳስተር ቅየሳ ዳይሬክተር አቶ ብንያም ግርማ በበኩላቸው፣ ባለሙያዎች ከብልሹ አሠራር ራሳቸውን በማራቅ፣ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣትና ተገልጋዮችን በአግባቡ በማገልገል ግንባር ቀደም መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የሥራ ክፍል ኃላፊዎች የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዳቸውን ከኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ መሐዲ መሐመድ ጋር በመፈራረም የዕቅድ ስምምነት አድርገዋል። በተመሳሳይም የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ከቡድን መሪዎች ጋር የዕቅድ ስምምነት ፊርማ አከናውነዋል።

ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም.

በተቀናጀ የመሬት ዝግጅት፣ ባንክና ማስተላለፍ ሥራ የከተማ ልማትን ማፋጠን እንደሚጠበቅ ተገለጸ።የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የመሬት ልማት፣ ባንክና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት ...
20/08/2026

በተቀናጀ የመሬት ዝግጅት፣ ባንክና ማስተላለፍ ሥራ የከተማ ልማትን ማፋጠን እንደሚጠበቅ ተገለጸ።

የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የመሬት ልማት፣ ባንክና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት የተጠናቀቀውን የበጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር ገምግሟል።

የጽ/ቤቱን የሥራ አፈጻጸምና ዕቅድ ያቀረቡት የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ዳይሬክተር አቶ ረመዳን ሙሳ፣ በሪፖርታቸው የለማ መሬት ዝግጅት፣ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ፣ ከልማት ተነሺዎች ጋር የተያያዙ ሥራዎች፣ የግንባታ ክትትል፣ የመልሶ ማልማት ሥራዎችና ከገቢ አሰባሰብ ጋር የተያያዙ ዕቅዶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

በአግባቡ የተመራና የተቀናጀ የመሬት ዝግጅት፣ ባንክና ማስተላለፍ ሥራ ለከተማው ዘላቂ ልማትና የከተማ እድገትን ለማፋጠን ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል።

በዕቅዱ መሠረትም በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች 60 ሄክታር የለማ መሬት ለማዘጋጀትና ከዚህ ቀደም ባንክ ከገቡ መሬቶች ጋር በማጣመር 80 ሄክታር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዷል።

በተጨማሪም በሂደት ላይ ያሉ የካቢኔ ውሳኔዎችን በተገቢው መፈጸም፣ የመሬት ወረራን መከላከልና ባንክ የተደረጉ መሬቶችን ጥበቃ የዕቅዱ ዋና አቅጣጫዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ለዚህም በተለያዩ አካላት መካከል የተሻለ ቅንጅት በመፍጠር እንደሚሰራ ተመልክቷል።

የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ መረጃዎች በተደራጀ የመረጃ ሥርዓት አለመያዛቸው፣ የልማት ተነሺዎች የካሳና የምትክ ቦታ መረጃዎች በበቂ ሁኔታ አለመደራጀታቸው፣ እንዲሁም ባንክ የሚደረጉና የሚተላለፉ መሬቶች የተሟላ የመረጃ ቋት አለመኖሩ ለተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንስኤ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ዘርፉን ወደ ዘመናዊ አሰራር በማስገባት በመረጃ የተደገፈ የአሰራር ሥርዓት ለማሸጋገር የተጀመረውን ተግባር አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይም የመሬት መረጃን በማደራጀት፣ የአሰራር ሂደቶችን በማቀላጠፍና ግልጽና ተደራሽ አገልግሎትን በማስፋፋት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ከአሰራር፣ ከሕግ ማዕቀፍ፣ ከቅንጅትና ከግብዓት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ነጥቦች አንስተዋል።

በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተግባር ለማሳካት የተቀናጀ አሰራር፣ የተደራጀ የመሬት መረጃና ጠንካራ የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

ነሃሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

ቤት ለቤት ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎች የድጋፍና ጉብኝት መርሃ ግብር ተደረገ።የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች በየወሩ ከደመወዛቸው በተቆረጥ ገንዘብ በችግ...
20/08/2026

ቤት ለቤት ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎች የድጋፍና ጉብኝት መርሃ ግብር ተደረገ።

የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች በየወሩ ከደመወዛቸው በተቆረጥ ገንዘብ በችግር ላይ ላሉ ነዋሪዎች የአልባሳትና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

የቢሮው ሰራተኞችና አመራሮች ድጋፉን በየቤቱ በመድረስ በችግር የሚገኙ ነዋሪዎችን በመጎብኘት፣ ሁኔታቸውን በማዳመጥና የሚያስፈልጋቸውን የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፍ በማቅረብ አከናውነዋል።

በድጋፉ ወቅት የካዳስተር ቅየሳ ዳይሬክተር አቶ ብንያም ግርማ በየቤቱ በመድረስ በችግር ላይ ላሉ ዜጎች ድጋፍ ማድረግ የመተሳሰብና የመረዳዳት እሴትን የሚያጠናክር ሰብዓዊ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ተግባሩ በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን ከመርዳት ባለፈ ሁኔታቸውን ለማዳመጥ፣ ለመጎብኘትና የሞራል ድጋፍ በማድረግ “ከጎናችሁ ነን” የሚል የወገንተኝነት መልዕክትን በተግባር ማሳየት መሆኑን ተናግረዋል።

በቢሮው የባለብዙ ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ እህትአገኘሁ በቀለ በበኩላቸው በየቤቱ የሚደረግ ድጋፍና ጉብኝት በችግር ላይ ላለ ወገን የተስፋ መንገድ የሚከፍት ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ሁላችንም በየአካባቢያችን ላሉ በችግር የተጋለጡ ወገኖች በማበረታታት፣ በማዳመጥና በመጎብኘት ወገን መሆን እንደሚገባን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይም በአመቱ ውስጥ በህክምና ወጪ የተቸገሩ ሁለት ወገኖች ከሰራተኛው የወር ደመወዝ ለያንዳንዳቸው የሀያ ሺህ ብር ድጋፍ በተወካዮቻቸው በኩል ተሰጥቷል።

የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ያከናወኑት ይህ ተግባር የበጎነት፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህልን በማጠናከር በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች ተስፋን የሚያጎለብት ሰብዓዊ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

20/08/2026
የ2019 በጀት ዓመት የዘርፉን እቅድ በጋራ ለመፈጸም የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ።በኢፌዴሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርና በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ መካከ...
19/08/2026

የ2019 በጀት ዓመት የዘርፉን እቅድ በጋራ ለመፈጸም የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ።

በኢፌዴሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርና በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ መካከል የ2019 በጀት ዓመት የዘርፉን እቅድ በቅንጅት ለመፈጸም የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።

ስምምነቱ የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥራዎችን በተቀናጀ አካሄድ ለመፈጸም ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ቢሮው የዘርፉን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በጋራ በመያዝ ለመፈጸም፣ በሥራ አፈጻጸም ላይ የጋራ አቅጣጫ ለመከተልና የሚከሰቱ የአፈጻጸም ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በስምምነቱ መሠረት የሁለቱ ተቋማት ሥራዎች በቅንጅት፣ በትብብርና በመናበብ እንዲመሩ ትኩረት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን በመወከል ከቢሮው ጋር የተፈራረሙ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

በተለይም በመሬት አስተዳደር፣ በመሬት አገልግሎት አሰጣጥና በዘርፉ የሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የተቀናጀ አሠራር በመፍጠር ለከተማ ነዋሪዎች ፈጣን፣ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያግዝ ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ጨምረው ገልጸዋል።

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮን በመወከል የጋራ ስምምነት ሰነዱን የፈረሙት ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ጌዲ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የተፈረመውን ስምምነት በተግባር በማስፈጸም የዘርፉን ተልዕኮዎች በተሳካ ሁኔታ ለማሳካትና ለከተማ ነዋሪዎች የሚሰጠውን የመሬት አገልግሎት በተሻለ ደረጃ ለማድረስ የጋራ ጥረታቸውን እንደሚያጠናክሩ ተገልጿል።

በማጠቃለያውም የሁለቱ ተቋማት የሥራ አመራርና ባለሙያዎች የሚኖራቸውን የመረጃ ልውውጥና የሙያ ትብብር በማጠናከር የዘርፉ ሥራዎች በተመሳሳይ አቅጣጫና በጋራ እቅድ እንዲመሩ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

የስምምነት ሰነዱ መፈረሙን ተከትሎ የ2019 በጀት ዓመት የዘርፉ ዕቅዶች በተቀናጀ አሠራር እንዲፈጸሙ፣ የሥራ አፈጻጸም ተጠያቂነት እንዲጠናከርና የተገልጋዩ ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

ነሃሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የተለያዩ  የሥራ ክፍሎች የተጠናቀቀው በጀት አመት እቅድ የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት አመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።በቢሮው የተቋም ለውጥ አፈጻጸምና...
19/08/2026

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተጠናቀቀው በጀት አመት እቅድ የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት አመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።

በቢሮው የተቋም ለውጥ አፈጻጸምና አገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ምዘና ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታና ግብይት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ የሥራ ዕቅድ በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ የሥራ ክፍሎቹ በዕቅዳቸው መሠረት ያከናወኗቸውን ተግባራት፣ የተመዘገቡ ውጤቶችና በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ተገምግመዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ የሥራ ዘመን ሊሰጡ የሚገባቸው ትኩረት መስኮችና የሥራ አፈጻጸሙን የበለጠ ለማሻሻል የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

በመድረኩ የተለዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን በመሙላት፣ የሥራ ቅንጅትን በማጠናከርና ተግባራትን በውጤታማነት በመፈጸም የመሬት ዘርፉን አገልግሎት የበለጠ ለማሻሻል በቀጣይ የሚወሰዱ እርምጃዎችም ተመላክተዋል።

ነሃሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ገመገመ።በድሬደዋ አስተዳደር የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥ...
18/08/2026

የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ገመገመ።

በድሬደዋ አስተዳደር የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ከፅ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር በጋራ ገምግሟል።

የአፈጻጸም ሪፓርትና እቅዱ በፅ/ቤቱ የሽንሸና ፕላን ጥናትና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የፅ/ቤቱ ኃላፊ ተወካይ በአቶ ኤፍሬም ሙሉጌታ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም የቀበሌ ቤቶች ካርታ አሰጣጥ፣ በተለያዩ አግባቦች የተያዙ ይዞታዎችን ወደ ሥርዓት ማስያዝ፣ የሽንሸና ፕላን ዝግጅት፣ በነዋሪዎች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአፋጣኝ መመለስ እንዲሁም አስፈላጊውን ግብዓት ማሟላትን በተመለከተ የሚከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል።

በመድረኩ የፅ/ቤቱ ሠራተኞችም በአሠራር ሥርዓት፣ በግብዓት አቅርቦትና ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ጋር በተያያዙ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አንስተዋል።

በተጨማሪም የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል ተጨማሪ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችና አስተያየቶች ቀርበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ከውይይቱ የተነሱ ሃሳቦችን በማካተት በዝግጅት ምዕራፍ የታቀዱ ሥራዎች በተቀመጠላቸው የአፈጻጸም ጊዜ እንዲጠናቀቁ እና የትግበራ ወቅት ዕቅዶች በተገቢው መንገድ ተፈጻሚ በማድረግ ሥር ነቀል ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ሠራተኛ ተሳትፎና ኃላፊነት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ባለሙያዎች በመንግሥት የሥራ ሰዓት በሥራ ቦታቸው በመገኘት ለተገልጋዮች አገልግሎትን በአግባቡ፣ በተቀመጠው የሥራ ሂደትና በተገቢው ጊዜ መስጠት እንደሚገባቸው ተገልጿል።

ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

Address

Dire Dawa

Telephone

+251912713204

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ/Dire Dawa Land Development and Management Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ/Dire Dawa Land Development and Management Bureau:

Shortcuts

Share