Dire Dawa woreda 9 Communication

Dire Dawa woreda 9 Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Dawa woreda 9 Communication, Government Organization, Dire Dawa.

05/03/2026

በድሬዳዋ አስተዳድር ወረዳ 09 ኮሪደር ልማት ስራ
ከአሸዋ እስከ ሼክ ሃቢብ ድረስ

04/03/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ከአጎራባች ወረዳዎች በ08 እና በ09 ወረዳ ልምድ የመለዋወጥ የአመራር አንድነትና ወንድማማችነት የተጠናከረ እንቅስቃሴ ሰው ተኮር ልማትን እያጠናከረ ነው።

ማህበረሰቡ በራሱ ተነሳሽነት በልማት ላይ እየተሳተፈ ነው።
ሀሳብና ልምድ በመጋራት ተግባራዊ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
አንድነት እና ተባብሮ መስራት ልማቱ አከባቢ መንገዶችን የማስዋብ መሠረት ሆኗል።

“ድሬዳዋ ልማት ጊዜዋ ሆነ!” በማለት የተጀመረው ጉዞ በሕዝብ ተሳትፎና በተቀናጀ አመራር ይቀጥላል።

ዛሬ ጥር 21/2018 ዓ.ምበወረዳ 9 አስተዳደር እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት   በገንደ ገራዳ የማህበረሰባችን ጥያቄ  የመንገደ ዳር  መብራት  በብልሽት  ምክንያት አገልግሎት መስጠት ...
29/01/2026

ዛሬ ጥር 21/2018 ዓ.ም
በወረዳ 9 አስተዳደር እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በገንደ ገራዳ የማህበረሰባችን ጥያቄ የመንገደ ዳር መብራት በብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቋረጡትን ማብራቶችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ቱክረት በመስጠት የማህበረሰባችን ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የመጠገን ስራ እየተሰራ ይገኛል።
የጥገናው ስራ ነገም ይቀጥላል

22/01/2026
 #ዜና | የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የድሬዳዋ ሀገረስብከት ምስጋና አቀረበ።   |ጥር 13 ፥ ...
21/01/2026

#ዜና | የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የድሬዳዋ ሀገረስብከት ምስጋና አቀረበ።

|ጥር 13 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ

የእግዚአብሔርአብ ታቦት ከጠምቅተ ባህር ወደ ማደሪያ መንበሩ በታላቅ ድምቀት ተመለሰ።

በኹነቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን የድሬደዋ ሀገር ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርተሎሚዮስ፣ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣የድሬደዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮምሽነር አለሙ መግራ፣እንዲሁም የሀገረስብከቱ ካህናትና አመራሮች ተገኝተዋል።

በኹነቱ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የድሬዳዋ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርተሎሚዮስ ለምእመኑ መልክት አስተላልፈዋል።

ህዝብ ከርስቲያኑ የጥምቀትን በዓል ሲያከብር ለሀገሩ ሰላም እና ደህነት በመፅለይ እና ለስራ በመትጋት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በዓሉ በሰላም እና ያለምንም ፅጥታ እንከን እንዲከበር የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌዴራል ፓሊስ፣የድሬዳዋ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ላደረጉት አስተዋፆም ሊቀ ጳጳሱ ምስጋና አቅርበዋል።

ሰራዊት ተኮላ
ምስል፦እስራኤል ሙሉ


ተጨማሪ ፥ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦

👉ፌስቡክ፡-
ለአማርኛ ፦https://www.facebook.com/diretvamharic
ለአፋን ኦሮሞ ፦https://www.facebook.com/share/1B8KihEAkt/
ለአፍ-ሶማሊ ፦https://www.facebook.com/share/199s1kp4Sr/
👉ዩትዩብ ፦
https://www.youtube.com/live/rkHE_fWNmkE?si=TElgNpYHVPxpB77L
👉በቲክታክ ፦
https://vm.tiktok.com/ZMSwgmLny/
👉በቴሌግራም ፦
https://t.me/+6C5aVWGZeL4wOWM0

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡


ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ዜና | "በወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል" - የ...
21/01/2026

#ዜና | "በወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል" - የወረዳ 09 ነዋሪዎች

| ጥር 13/2018

በድሬዳዋ ወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ አያይዘውም ከኮሪደር ልማቱ በፊት በአካባቢው በስፋት ያረጁ፣ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶች ይገኙ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት ግን ያረጁ ቤቶች ውበት ባላው እና በዘመናዊ መልኩ በአዲስ ተሻሽለው እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ለአካባቢ ገፅታ ሳቢ ያልሆኑ ተለጣፊ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶች እየተነሱ መሆናቸውን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ አካባቢው የንግድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የንግድ ቤቶችን ምቹ በሆነ መልኩ የመገንባት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በቀጣይም አካባቢያቸውን የማሳመርና የማልማት ስራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር የሆኑት ኢንጂነር ኡመር ዱአሌ የወረዳው የኮሪደር ልማት በአራት ምዕራፍ ተከፋፍሎ እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቆሙ ሲሆን በዚህም ከአሸዋ እስከ ክርስትያን መቃብር፣ ከባቡራህማ መስኪድ ከፍ ብሎ አስከ ክርስትያን መቃብር፣ ከሀፍካት ድልድይ እስከ ኮተንና ከክርስትያን መቃብር እስከ ታፍ(ከድሬዳዋ ጅቡቲ የሚያገናኘው) መንገድ ድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በህገ-ወጥ መልኩ የእግረኛ መንገድን የዘጉ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶችን የማንሳት ስራዎች መሰራታቸውን ኢንጂነር ኡመር የገለፁ ሲሆን፤በልማቱ የወረዳውን ገፅታ በመቀየር ፅዱና ውብ ለማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር በጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀሰን ኡመር በበኩላቸው እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ 20 ሜትር ራዲየስ የመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 50 ሜትር ራዲየስ የግልና የመንግስት ተቋማት ዙሪያቸውን እንዲያፀዱ የማድረግ ስራ፣
የዋና ዋና መንገዶች እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በመብራት የማሳመርና የማስጌጥ ተግባራት እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ዳዊት መስፍን

በወረዳ 9 አስተዳደር በኮሪደር ልማት የተሰሩ ስራዎችን የወረዳው ደጋፊ አመራሮች ከወረዳው አመራሮች ጋር በምሽት የመስክ ምልከታ አካሂዷል።
17/01/2026

በወረዳ 9 አስተዳደር በኮሪደር ልማት የተሰሩ ስራዎችን የወረዳው ደጋፊ አመራሮች ከወረዳው አመራሮች ጋር በምሽት የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

በወረዳ 9 አስተዳደር ቀጠና 2 መንደር 1ልዩ ሰሙ ገንደ ጨፌ (ጨርቃጨርቅ) በሚባለው ሰፈር ለረጅም አመታት በነዋሪዎች ዘንድ ይነሳ ለነበረው የውስጥ ለውሰጥ መንገድ ይከፈትልን የመልካም አሰተ...
16/01/2026

በወረዳ 9 አስተዳደር ቀጠና 2 መንደር 1ልዩ ሰሙ ገንደ ጨፌ (ጨርቃጨርቅ) በሚባለው ሰፈር ለረጅም አመታት በነዋሪዎች ዘንድ ይነሳ ለነበረው የውስጥ ለውሰጥ መንገድ ይከፈትልን የመልካም አሰተዳደር ጥያቄ በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 8/5/2018 ዓ.ም የወረዳ 9 መሬት ልማት ማሰተባበሪያ ከሚመለከታቸው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የነዋረዎቹን የውሰጥ ለውስጥ መንገድ ይከፈትልን ጥያቄ በተገቢው ሁኔታ ለመፍታት ተችሏል ።

ዛሬ ጥር 8/2018 ዓ.ምየወረዳ 9 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት  በአደረጃጀት ዘርፍ በአራቱ መሠረታዊ መመሪያዎች ላይ ለአመራሩና ለአባላቱ  የአቅም ግንባታ ስልጠና  ተሰቷል።
16/01/2026

ዛሬ ጥር 8/2018 ዓ.ም
የወረዳ 9 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በአደረጃጀት ዘርፍ በአራቱ መሠረታዊ መመሪያዎች ላይ ለአመራሩና ለአባላቱ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰቷል።

ዛሬ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ምበድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 9 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በመጡት ድጋፋዊ ሱፐ...
29/12/2025

ዛሬ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 9 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በመጡት ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ተግምግሟል።
የፓርቲ ስራ በተመለከተ የፓርቲ እቅድ አፈጻጸም ፣የአደረጃጀት ና የህዝብ ግኑኝነት ስራዎችን በመገምገም ጠንካራ እና ውስነቶችን በማስቀመጥ የአባላት ፣ወጣቶች ና ሴቶች ክንፍ የህብረት እና የቤተሠብ አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ ማስቀጠልና በመጨረሻም ቀጣይ መሠራት ያለባቸውን በመለየት ና አቅጣጫ በማስቀመጥ የዛሬው ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ተጠናቋል።

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa woreda 9 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share