በድሬዳዋ አ/የአስሊሶ ክላስተር ብልፅግና የኢንስፔክሽና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • በድሬዳዋ አ/የአስሊሶ ክላስተር ብልፅግና የኢንስፔክሽና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

በድሬዳዋ አ/የአስሊሶ ክላስተር ብልፅግና

የኢንስፔክሽና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን

ቅ/ጽ/ቤት -> ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ

01/09/2026
በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኮሚሽን መዋቅሮች እውቅና ተሰጠ!  ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን...
01/09/2026

በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኮሚሽን መዋቅሮች እውቅና ተሰጠ!

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ በአስተዳደሩ ውስጥ ለሚገኙ የከተማ ወረዳዎች፣ የገጠር ክላስተሮችና የሴክተር ተቋማት የኮሚሽን መዋቅሮች እውቅና ሰጥቷል።

በተጨማሪም ከከተማ ወረዳዎች፣ ከገጠር ክላስተሮችና ከሴክተር ተቋማት የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን መዋቅሮች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ግብ ስምምነት ተካሂዷል።

👏 ላስመዘገባችሁት የላቀ አፈፃፀም እንኳን ደስ አላችሁ! በ2019 በጀት ዓመትም የበለጠ ውጤት እንድታስመዘግቡ መልካም ምኞት እናቀርባለን።

#እውቅና

Bara Bajataa 2018tti Raawwii Olaanaa Galmeessaniif Beekamtiin Kenname!

Hagayya 26, 2018 Bulchiinsa Dirree Dhawaa

Komishiniin Inspeekshinii fi Naamusa Badhaadhinaa Bulchiinsa Dirree Dhawaa, caasaalee Komishinii Inspeekshinii fi Naamusa Magaalota, Kilaastaroota Baadiyaa fi Dhaabbilee Dameelee Bulchiinsichaa keessatti argamaniif, raawwii hojii olaanaa bara bajataa 2018 galmeessaniif beekamtii kenneera.

Dabalataanis, caasaalee Komishinii Inspeekshinii fi Naamusa Magaalota Kilaastaroota Baadiyaa fi Dhaabbilee Dameelee waliin ta’uun galma karoora bara bajataa 2019 irratti waliigaltee karooraa gaggeesseera.

👏 Raawwii olaanaa galmeessitaniif baga gammaddan! Bara bajataa 2019 keessattis bu’aa fi raawwii caalmaa akka galmeessitan hawwii gaarii isiniif qabna.



Aqoonsi la siiyay qaab-dhismeedyadii Komishanka ee waxqabadka sare ka sameeyay sannad-miisaaniyadeedka 2018!

26-ka Agoosto 2018 Maamulka Diredhabe

Komishanka Kormeerka iyo Anshaxa Barwaaqo ee Maamulka Dire Dawa ayaa aqoonsi siiyay guddoomiyeyaasha qaab-dhismeedyada Komishanka Kormeerka iyo Anshaxa ee degmooyinka magaalada, kooxaha miyiga iyo hay’adaha waaxyaha maamulka, kuwaas oo sannad-miisaaniyadeedka 2018 ka sameeyay waxqabad heer sare ah.

Sidoo kale, Komishanku wuxuu la yeeshay qaab-dhismeedyada Komishanka ee degmooyinka magaalada, kooxaha miyiga iyo hay’adaha waaxyaha heshiis ku saabsan yoolalka qorshaha sannad-miisaaniyadeedka 2019.

👏 Hambalyo dhammaan kuwii muujiyay waxqabadka sare! Waxaan idiin rajaynaynaa in sannad-miisaaniyadeedka 2019 aad gaartaan guulo iyo waxqabad ka sarreeya kii h**e.

01/09/2026
01/09/2026
30/08/2026

“የመደመር መንግሥት ታሪክ ከማውራት ይልቅ ታሪክን በመሥራት ራሱን መግለጥ የሚሻ ነው”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የሙስና ባህሪያት፦🌿🌿🌿🌿🌿ሙስና ሀገርንና ማህበረሰብን የሚጎዳ፣ ፍትሕንና እኩልነትን የሚያዛባ አደገኛ ድርጊት ነው። እንደ ዓይነቱና እንደየሁኔታው ቢለያይም፣ ዋና ዋና የሙስና ባህሪያት ተመላክ...
30/08/2026

የሙስና ባህሪያት፦
🌿🌿🌿🌿🌿

ሙስና ሀገርንና ማህበረሰብን የሚጎዳ፣ ፍትሕንና እኩልነትን የሚያዛባ አደገኛ ድርጊት ነው። እንደ ዓይነቱና እንደየሁኔታው ቢለያይም፣ ዋና ዋና የሙስና ባህሪያት ተመላክተዋል።

✔️ስውርነት እና ድብቅነት፦
ሙስና አብዛኛውን ጊዜ በህቡዕ እና በግለሰቦች ምስጢራዊ ስምምነት የሚፈጸም በመሆኑ በቀላሉ ለማወቅና ለመያዝ አስቸጋሪ ነው።

✔️ሥልጣንን ለግል ጥቅም ማዋል፦
የተሰጠን የሕዝብ ወይም የድርጅት ኃላፊነት፣ ውክልና እና የውሳኔ መስጠት ሥልጣን ለራስ፣ ለቤተሰብ ወይም ለጥቅም ተሳስሪዎች ማዋል ነው።

✔️ሕገ-ወጥነትና ደንብ መጣስ፦
የተዘረጉ አሰራሮችን፣ መመሪያዎችን፣ የሕግ ድንጋጌዎችን እና የሥነ-ምግባር ደንቦችን ሆን ብሎ መጣስ ወይም ማዞርን ያካትታል።

✔️የጋራ ህገ ወጥ ጥቅም መኖር፦
በተቀባዩ እና በሰጪው (ወይም በጥቅም ተሳሳሪዎች) መካከል የጋራ ህገ-ወጥ ጥቅም መለዋወጥ አለ።

✔️ግልጽነትና ተጠያቂነት ማጣት፦
አሰራሮች ለሕዝብ ግልጽ እንዳይሆኑ ማድረግ እና ለተፈጸሙ ስህተቶችና ውሳኔዎች ተጠያቂነትን መሸሽ።

✔️ፍትሐዊነትን ማሳጣት፦
አገልግሎትን ወይም ጥቅምን በችሎታ፣ በሕግና በቅደም-ተከተል ሳይሆን በጉቦ፣ በዘመድ አዝማድ (ዝምድና) ወይም በቡድን አደረጃጀት መስጠት።

✔️ተላላፊነት እና ተስፋፊነት፦
ከተወሰኑ ግለሰቦች አልፎ በኪራይ ሰብሳቢነትና በብልሹ አሰራር ሥርዓታዊ በመሆን ወደ ተቋማዊ ባህል የመለወጥ አዝማሚያ አለው።

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በድሬዳዋ አ/የአስሊሶ ክላስተር ብልፅግና የኢንስፔክሽና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በድሬዳዋ አ/የአስሊሶ ክላስተር ብልፅግና የኢንስፔክሽና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share