Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau

Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau page
(20)

Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau is a Government office Established in Dire Dawa. የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በድሬዳዋ የተቋቋመ መንግስታዊ ቢሮ ነው.

03/08/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ እቅዱን 114 በመቶ በማሳካት በከፍተኛ ድል መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ሚስራ አብደላ አመሻሹን ከOBN ጋር በነበራቸው ቆይታ ገለጹ

03/08/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ እቅዱን 114 በመቶ በማሳካት በከፍተኛ ድል መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ገለጹ

በኤደን ሳሙኤል
ምስል:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ

 #ዜና | የድሬዳዋ አስተዳደር የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ እቅዱን 114 በመቶ በማሳካት በድል አጠናቀቀ  | ሐምሌ 27/2018በመላው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ የተካሄደው የአንድ...
03/08/2026

#ዜና | የድሬዳዋ አስተዳደር የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ እቅዱን 114 በመቶ በማሳካት በድል አጠናቀቀ

| ሐምሌ 27/2018

በመላው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ የተካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ ታላቅ ስኬት አስመዝግቧል።

ይህንን ሀገራዊ ጥሪና ስኬት ተከትሎም የድሬዳዋ አስተዳደር ከተቀመጠለት እቅድ በላይ 114 ፐርሰንት በማሳካት የድርሻውን በታላቅ ድምቀት መወጣቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ገለጹ።

ሀገሪቱ በአንድ ጀምበር ያስመዘገበችው የአረንጓዴ አሻራ ስኬት በድሬዳዋ መስተዳደርም በተመሳሳይ መልኩ በደመቀ ሁኔታ መተግበሩን ም/ሀላፊዋ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ የዛሬው የአንድ ጀምበር ተከላ በጣም ስኬታማ በሆነ መልኩ የተከናወነ ሲሆን፣ ከታቀደው እቅድ 114 ፐርሰንት ሊሳካ የቻለውም በማህበረሰቡ ጥንካሬ መሆኑን አብራርተዋል።

በዕለቱ በተከናወነው ታሪካዊ መርሃ ግብር ላይ ወደ 61 ሺህ የሚጠጋ ከፍተኛ የማህበረሰብ ክፍል በንቃትና በጥሩ ሁኔታ ሲሳተፍ መዋሉን ወ/ሮ ሚስራ ጠቁመዋል።

በዚህም ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና ሁሉም የፀጥታ አካላት በሙሉ በተቀናጀ መልኩ የበኩላቸውን የላቀ ሚና መወጣታቸውን በዝርዝር አስረድተዋል።

ይህ የዛሬው ደማቅ ተሳትፎም ቀደም ሲል ከአረንጓዴ አሻራ ከተገኙት መልካም ቱሩፋቶች መካከል አንዱና ዛሬም በስኬት የተደገመበት መሆኑን ም/ሀላፊዋ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ጥሪውን በነቂስ ለወጣው መላው የድሬዳዋ ማህበረሰብ፣ ለመንግስት ሰራተኞችና ለፀጥታ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሰላም አበበ

03/08/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ከ800 ሺህ በላይ ችግኞች የሚተከሉበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአሰሊሶ ክላስተር አሶሊሶ ቀበሌ ገደንሰር መንደር ተካሄደ።

​“ተስፋን መትከል” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው አገር አቀፍ መርሐ ግብር መሠረት፣ በድሬዳዋ አስተዳደርም ከ800 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ያለመ ህዝባዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ተካሂዷል።

የድሮን ምስል (ቀረፃ) እና ቅንብር: ኢዮብ ረታ

 #ምስጋና | የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሃር የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ  | ሐምሌ 27/2018...
03/08/2026

#ምስጋና | የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሃር የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

| ሐምሌ 27/2018

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ተስፋን መትከል” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሙሉ በሙሉ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ዛሬ ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል ታላቅ ታሪክ በመፃፏ እንኳን ደስ አለን ያሉት ክቡር ከንቲባው፤ መላው የድሬዳዋ ሕዝብም ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ማታው 12 ሰዓት ድረስ በነቂስ በመውጣት፣ ከ800 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል የተያዘውን ታላቅ ዕቅድ በስኬት ማጠናቀቁን አብራርተዋል።

ለዚህ ታሪካዊ ቀን ስኬት ግንባር ቀደም በመሆን አሻራቸውን ላኖሩ ብርቱዎች ወጣቶች፣ ውድ እናቶችና ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ህጻናት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞችና የጸጥታ አካላት በሙሉ ክቡር ከንቲባው በራሳቸውና በአስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች በመሆናቸው ለምግብ ዋስትና ትልቅ መሠረት የጣሉ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 40 በመቶ ደግሞ ለጥላና ለውበት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ክቡር ከንቲባው በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና የማጽደቅ ተግባርን በተመሳሳይ የአንድነት መንፈስ ማሳካት እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ*********************ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር...
03/08/2026

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

*********************

ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው።

መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል።

ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው።

ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል።

ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል ።

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ዛሬ ኢትዮጵያ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል ታላቅ ታሪክ መፃፏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋ...
03/08/2026

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ ኢትዮጵያ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል ታላቅ ታሪክ መፃፏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋል።

03/08/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ከ800 ሺህ በላይ ችግኞች የሚተከሉበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዛሬው እለት የተጀመረ ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ EBC ከብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ከሆኑት ከክቡር ኢብራሂም ዩሱፍ ጋር የነበራውን ቆይታ እንደሚከተለው ዘግቧል ...

03/08/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር በዘጠኙም የከተማ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በነቂስ በመውጣት ታሪካዊ አሻራቸውን አሳረፉ

በኤደን ሳሙኤል
ምስል:-ሙሉዓለም ደሴ

03/08/2026

Bulchiinsi Dirree Dhawaa Sagantaa Dhaabbii Biqiltuu Ishaara Magariisaa Kuma 800 gaggeeyfameeti jira.

Sagantaan dhaabbii biqiltuu Ashaara magariisaa mata duree "Abdii gadhaabuu" jedhuun Akka Biyyaatti Aduu Tokkotti Biqiltuu Miliyoona 800 akka bulchinsaattimmoo biqiltuuwwan Kuma 800 dhaabuu har'a Kilaastara Waaheel, Araddaa koorisootti gaggeeffame

Muktaar Ahammadiin
Suuuraa: Salaam Abbabaa

Address

Dire Dawa
3000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share