Dire Dawa Administration City Manager

Dire Dawa Administration City Manager ይህ ገጽ የከተማዋን መሰረተ ልማትና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶ የሚያሳይ ነው�

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ድሬዳዋየድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉ...
05/09/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

1ኛ፦ ካቢኔው በመሬት እና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

መሬትን በፕላንና በሕግ አግባብ ማስተዳደር የከተማዋን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ያፋጥናል። ይህም መሬት ለታለመላቸው የኢንቨስትመንት፣ የኢንዱስትሪ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ብቻ እንዲውል በማስቻል ረገድ ሚናው የጎላ ነው። አሠራሩ ኅብረተሰቡ ከመሬት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ፣ በግልጽነትና ከብልሹ አሠራር በጸዳ መልኩ ማግኘት እንዲችል በማድረግ ረገድም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

2ኛ፦ ካቢኔው በአስተዳደሩ የልማት ሥራዎች እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ!

05/09/2026

ለተቋሙ አመራሮች የስትራቴጂክ ሥራ አመራር ሥልጠና መድረክ ተዘጋጀ

በድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማስፈጸም አቅም ግንባታና ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን አማካኝነት ለተቋሙ አመራሮች የተዘጋጀ የሥራ አመራር (Strategic Management) ሥልጠና መድረክ ተዘጋጀ።

የሥልጠናው ዋና ዓላማ የተቋሙን አመራሮች የሥራ አመራር ክህሎት ማጎልበት፣ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን ማዳበር እና ተቋማዊ ዕቅዶችን በተግባር በብቃት ለማስፈጸም የሚያስችል አቅም መገንባት መሆኑ ተገልጿል።

በከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማስፈጸም አቅም ግንባታና ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይለማርያም በርጋ እንደገለጹት፣ ሥልጠናው አመራሮች የተቋሙን ዓላማና ግቦች በግልጽ በመረዳት ሥራዎችን በዕቅድ፣ በቅንጅትና በውጤታማነት እንዲመሩ የሚያግዝ ነው።

አቶ ሀይለማርያም አክለውም፣ የተቋሙን አፈጻጸም ለማሻሻል ብቁና ውጤታማ አመራር ወሳኝ በመሆኑ አመራሮች የስትራቴጂክ ሥራ አመራር እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በተግባር ማዋል እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

በሥልጠናው የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም፣ የሥራ አመራር መርሆዎች፣ ውሳኔ አሰጣጥ፣ የቡድን አመራር፣ የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ እንዲሁም የተቋም ውጤታማነትን ማሳደግ ዙሪያ ሥልጠናዎችና ውይይቶች እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል።

ሥልጠናው አመራሮች በሥራቸው የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡና የተቋሙን አጠቃላይ ውጤታማነት እንዲያሳድጉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

04/09/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስተናጋጅነት፣ በመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ የተዘጋጀ የስልጠናና የውይይት መድረክ ተጀመረ።

መድረኩ የተጀመረው በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነው

03/09/2026

ድሬዳዋ አሰተዳደር የከተማ ሥራ አስኪያጅና ተጠሪ ተቋማት የ2016–2018 የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 መሪ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ

የድሬዳዋ አሰተዳደር ከተማ ሥራ አስኪያጅና ተጠሪ ተቋማት ያለፉትን ሦስት ዓመታት (2016–2018) የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም፣ የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ አስፈጻሚ አካላት፣ የሴክተር መሥሪያ ቤቶች አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የወረዳ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ኮንትራክተሮች እና የመንገድ ሥራ ተቋራጮች ተገኝተዋል።

በውይይቱም ያለፉት ሦስት ዓመታት የዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የተገጠሙ ችግሮችና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። በተጨማሪም የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በተቀናጀና በተጠናከረ አሠራር ለመፈጸም የሚያስችሉ የትብብርና የቅንጅት ሥራዎች ተመላክተዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የከተማ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ለቀረቡ አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

በመድረኩ መጠናቀቂያም በተለያዩ የሥራ መስኮች ለተቋማቱ የሥራ አፈጻጸም አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።

ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም በዚህ ወቅት በከተማ ሥራ አስኪያጅና ተጠሪ ተቋማት ስም ለእውቅና ለተመረጡ አካላት ላደረጉት ቀና ትብብርና የቅንጅት ሥራ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም በቀጣይ የከተማዋን የልማት ሥራዎች በተሻለ ደረጃ ለማስፈጸም በተለይም በተቋማትና በባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር በጋራ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ባለ 700DN የውሃ ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቋል።በወረዳ 09 ሻም ሆቴል አከባቢ በመንገድ ስራ ምከንያት ባለ 700DN የውሃ ማስተላለፊያ መስመር የመጠገን ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል...
03/09/2026

ባለ 700DN የውሃ ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቋል።
በወረዳ 09 ሻም ሆቴል አከባቢ በመንገድ ስራ ምከንያት ባለ 700DN የውሃ ማስተላለፊያ መስመር የመጠገን ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በዚህ መስመር መሰበር ምከንያት የውሃ ስርጭት አገልግሎት ተቋርጠውባቸው የነበሩ አከባቢዎች በተለመደው ፈረቃቸው አገልግሎት የሚያገኙ መሆኑን እናስታውቃለን።

ድሬደዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን!

03/09/2026

ድሬዳዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

የውይይቱ ዋና ዓላማ በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን በጋራ መገምገም፣ በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን መለየት እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።

በውይይቱ ላይ የአካባቢ ልማትና ህብረተሰብ ተሳትፎ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ረሂማ አወል፣ ህብረተሰቡ በአካባቢው ተደራጅቶ በልማትና በመልካም አስተዳደር ሥራዎች ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ፣ ተጠቃሚና ባለቤት እንዲሆን ኤጀንሲው ከአስተዳደሩና ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ኤጀንሲው በዘጠኙም ወረዳዎች የተደራጁ የብሎክ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ህብረተሰቡ በአካባቢው የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ እያስተባበረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ህገወጥ የመስመር ውሃ አጠቃቀምን ለመከላከል በየወረዳው ከሚገኙ የብሎክ አደረጃጀት ተወካዮችና ከፎረም አባላት ጋር በመቀናጀት ለመስራት ዕቅድ መያዙን ወ/ሮ ረሂማ አወል ገልጸዋል።

የውሃ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም፣ ህገወጥ የውሃ ግንኙነቶችን መከላከልና የውሃ ብክነትን መቀነስ በቀጣይ የሚሰሩ ሥራዎች መካከል ዋነኛ ትኩረት እንደሚሆኑም ተመላክቷል።

ውይይቱ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀምን በመገምገም የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለ2019 ዓ.ም ሥራዎች ለማስፋትና ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ጠንካራ የትብብር አቅጣጫ ለመያዝ ያለመ ነው።

የመንገድ መሠረተ ልማትን በማበላሸትና አካባቢን በመበከል የተገኙ ገራጆች ላይ የቅጣት እርምጃ ተወሰደነሐሴ 29/2018 ዓ.ም | ድሬዳዋየድሬዳዋ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የከተማዋን ...
03/09/2026

የመንገድ መሠረተ ልማትን በማበላሸትና አካባቢን በመበከል የተገኙ ገራጆች ላይ የቅጣት እርምጃ ተወሰደ

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የከተማዋን ጽዳት፣ ውበት፣ የሕዝብ ጤና እና የመንገድ መሠረተ ልማት ለመጠበቅ በሚያካሂደው የደንብ ማስከበር ሥራ በወረዳ 04 ገንደ ቆሬ አካባቢ በደንብ ጥሰት የተገኙ ገራጆች ላይ የማሸግ ቅጣትና የማስጠንቀቂያ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

በአካባቢው እግረኛ መንገድን በመዝጋት፣ የኮብልስቶን መንገድ መሠረተ ልማትን በማበላሸት እና ፈሳሽ የያዘ ቆሻሻን ወደ መንገድ በመልቀቅ አካባቢን በመበከል የተገኙ ገራጆች ላይ እርምጃው መወሰዱን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

የደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ እንዳስታወቀው፣ ማንኛውም ተቋምም ሆነ ግለሰብ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የአካባቢንና የመንገድ መሠረተ ልማትን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።

በመሆኑም የከተማዋን ደንብና መመሪያ በሚጥሱ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጽ/ቤቱ አስገንዝቧል።

በተጨማሪም ሕብረተሰቡ በከተማዋ የሚፈጸሙ የደንብ ጥሰቶችን ሲመለከት ለደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ በአካል በመቅረብ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

የውሃ ብክነትን ለመቀነስ የማህበረሰብ ብሎክ አደረጃጀቶች የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባልድሬዳዋ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ምየድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገ...
02/09/2026

የውሃ ብክነትን ለመቀነስ የማህበረሰብ ብሎክ አደረጃጀቶች የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል

ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 የሥራ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያካሂደው የውይይት መድረክ ተጀምሯል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም፣ ውሃ የሰው ልጅ መሠረታዊ የኑሮ ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰው፣ በአስተዳደሩ የሚስተዋለውን የውሃ ብክነት ለመቀነስ በአየር ንብረት ለውጥና በውሃ ጥበቃ ላይ በተለይ ትኩረት ተደርጎ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የድሬዳዋ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሐመድ ሙሴ ባቀረቡት የሥራ ሪፖርት፣ ባለፉት ዓመታት ከውሃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚከሰተው የውሃ ብክነት 45 በመቶ አካባቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የውሃ ብክነቱ በዋናነት ከሕገወጥ የውሃ ግንኙነቶችና በተለያዩ አካባቢዎች የውሃ ቧንቧዎች መበላሸት ጋር የተያያዘ መሆኑን ኢንጂነር መሐመድ ገልጸው፣ በተወሰዱ ርምጃዎች የውሃ ብክነቱን በ2 በመቶ መቀነስ መቻሉን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ከተማዋን ከቆሻሻና ከፍሳሽ ለማጽዳት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን የጠቆሙት ኢንጂነር መሐመድ፣ ለሥራው ማስፈጸሚያ ከተለያዩ ተቋማት በተገኘ የተሽከርካሪ ድጋፍ ሥራዎቹን ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የመልካ ጀብዱ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በበጀት ችግር ምክንያት ሳይጠናቀቅ መቆየቱን የጠቆሙት ኢንጂነር መሐመድ፣ ፕሮጀክቱን በ2019 በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

በመድረኩ መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሐርቢ ቡህ፣ የማህበረሰብ ብሎክ አደረጃጀቶች የውሃ ብክነትን በመከላከል የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሐርቢ ቡህ በተጨማሪም በድሬዳዋ ከተማ የውሃ አቅርቦትን ከ45 በመቶ የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ በትኩረትና በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በውይይቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የማህበረሰብ ብሎክ አደረጃጀቶች ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መድረኩ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናትም በመቀጠል የ2018 የሥራ አፈጻጸምና የ2019 የሥራ ዕቅድ ላይ የጋራ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የድሬዳዋ አሰተዳደር ከተማ ሰራ አስኪያጅ ኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኝነት

ድረ ገጽ
https://www.facebook.com /Dire Dawa Administration City Manager Dire Dawa

ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/1BgJQS6taB/

ቴሌግራም https://t.me/citysammanager

ትክቶኪ https://www.tiktok.com/

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግነዋለን

02/09/2026

ድሬዳዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

የውይይቱ ዓላማ የተቋሙን የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም በጋራ መገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ችግሮችን መለየት እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።

በዚሁ መሠረት የመጀመሪያ ዙር የደንበኞች ፎረም፣ ከብሎክ አደረጃጀት መሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚካሄደው የጋራ ውይይት ዛሬና ነገ ይካሄዳል።

ውይይቱ በውሃ አቅርቦት፣ በፍሳሽ አገልግሎት፣ በደንበኞች እርካታና በተቋሙ አጠቃላይ የአገልግሎት ጥራት ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በጋራ ለመዳሰስና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የድሬዳዋ አሰተዳደር ከተማ ሰራ አስኪያጅ ኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኝነት

ድረ ገጽ
https://www.facebook.com /Dire Dawa Administration City Manager Dire Dawa

ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/1BgJQS6taB/

ቴሌግራም https://t.me/citysammanager

ትክቶኪ https://www.tiktok.com/

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግነዋለን

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Administration City Manager posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share