Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau

Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau ፆታዊ ጥቃት ይቁም!
(1)

"የጸዳችና የበለጸገች ድሬዳዋ በሴቶች በጎነትና ቁርጠኝነት" በሚል ርዕስ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ
24/08/2026

"የጸዳችና የበለጸገች ድሬዳዋ በሴቶች በጎነትና ቁርጠኝነት" በሚል ርዕስ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

ሀገራዊ ምክክር መድረኩ ተጠናቀቀኢትዮጵያ የኃይልና የግጭት ፖለቲካን በቃ በማለት ልዩነቶቿን በሰለጠነ የምክክር መድረክ ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ፣ የሀገራችንን የፖለቲካ ምህዳር በአዲስ መሠ...
22/08/2026

ሀገራዊ ምክክር መድረኩ ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ የኃይልና የግጭት ፖለቲካን በቃ በማለት ልዩነቶቿን በሰለጠነ የምክክር መድረክ ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ፣ የሀገራችንን የፖለቲካ ምህዳር በአዲስ መሠረት ላይ የጣለ ታሪካዊ ድል ሆኗል ። በኢትዮጵያ የጥቂት ልሂቃን የጥቅም ድርድር የነበሩ የዝግ በር ልማዶችን የቀየረና፣ ሰፊውን ሕዝብ የውሳኔው ቀጥተኛ ባለቤት ያደረገ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።

ዜጎች ለዘመናት ያጋጠሟቸውን ታሪካዊ ስብራቶች፣ ጥልቅ አለመግባባቶችና የሐሳብ ልዩነቶች በኃይል ሳይሆን በመደማመጥና በጋራ ጥበብ መፍታት እንደሚችሉ በተግባር አስመስክረዋል።

በሁሉም ክልልሎች ከቀበሌ እስከ ፌደራል በተወከሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አርሶ/አርብቶ አደሮች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የብሔር-ብሔረሰቦችና እምነቶች ተወካዮች እንዲሁም ምሁራንና ሊቃውንት በስምንት አጀንዳዎች ላይ ባደረጉት ሁሉን አቀፍ ውይይት የ130 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ድምፅ አድምጠዋል። በዚህም ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው በንግግር ብቻ መሆኑን ፍጹም አካታች በሆነ አርአያነት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከባንዳዎቸ ጋር ተጣምረው በዲጂታል ሚዲያ የሐሰት መረጃ ና ውዥንብር ለመፍጠር ቢሞክሩም፣ የምክክር ኮሚሽኑ ተቋማዊ ገለልተኝነቱን በጥብቅ ዲስፕሊን በመመራት በጽናት አስከብሯል። ከ54 በላይ የሚዲያ ተቋማትና 461 ጋዜጠኞች ሂደቱን በቀጥታ ሽፋን በመስጠት ትክክለኛ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ችለዋል ።
በልጆቿ ፍጹማዊ ፅናት በተከናወነው በዚህ ታሪካዊ ክንውን፣ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በገዛ እጇ መወሰን እንደምትችል በተግባር አሳይታለች!ኢትዮጵያዊያን መከሩ ኢትዮጵያም አሸነፈች ሲል ኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ዘግቧል።

የበጎ ፍቃድ ተግባራት የትውልድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ህፃናትን እናሳትፍ! "ተስፋን እንትከል!" ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ- የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
21/08/2026

የበጎ ፍቃድ ተግባራት የትውልድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ህፃናትን እናሳትፍ! "ተስፋን እንትከል!"

ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ- የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

በቢሮው ባለድርሻ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ"ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮች ሰራተኞችና ...
21/08/2026

በቢሮው ባለድርሻ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ

"ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮች ሰራተኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂደዋል

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ በመርሀ ግብሩ እንደገለጹት በቢሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በታቀደው መሰረት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ተስፋን እንትከል በሚል ችግኞችን በምንተክልበት ጊዜ፣ ተግባራቱ ባህል ሆኖ ለወደፊትም ቀጣይነት እንዲኖረው የነገ ተስፋ የሆኑ ህፃናት ይህንን የበጎ ፈቃድ ስራ ውስጥ በመሳተፋቸው መርሀ ግብሩን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ለምግብና አረንጓዴነት የሚያገለግሉ ችግኞች በአስተዳደሩ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት እንክብካቤ ማዕከል፣ በሴቶች ተሃድሶ ማዕከልና በቢሮው እና IOM የሚተዳደር የስደት ተመላሾች ተሃድሶ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ የተተከለ ሲሆን፤

የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የሴት ህፃናት ክበባት አባላትና በማዕከሉ የሚገኙ ሰራተኞች በችግኝ ተከላው መርሀ ግብር ለይ ተሳትፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች አፍላ ወጣት ልጃገረዶች ራሳቸውን ችለው የተሻለ የወደፊት ህይወት እንዲገነቡ ያግዛቸዋልየድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመ...
16/08/2026

የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች አፍላ ወጣት ልጃገረዶች ራሳቸውን ችለው የተሻለ የወደፊት ህይወት እንዲገነቡ ያግዛቸዋል

የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር ከትምህርት ገበታ ውጭ ለሆኑ አፍላ ልጃገረዶች ለሚሰጠው የህይወት ክህሎት ስልጠናን ለሚያስተባብሩ ቮለንተሮች ስልጠና ሰጠ

አፍላ ወጣትነት አዲስ የህይወት ልምምዶች የሚጀመርበት እና የሚታይበት የእድሜ ክልል በመሆኑ ተጋላጭነትን እና የአቻ ተፅኖን ለመቀነስ የባህሪ ለውጥ ትምህርት ስልጠና የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው።

በዚህም ከትምህርት ገበታ ውጪ ለሆኑ አፍላ ወጣት ሴቶች የተለያዩ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን ለሚሰጡ ከአስተዳደሩ ወረዳ 1 እና 2 ለተወጣጡ በጎ ወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷል።

አፍላ ወጣቶች ከትምህርት ውጭ መሆን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቀውሶችን እንደሚያስከትል ይታሰባል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊን ወክለው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ መሀመድያሲን አብዱላሂ ልጃገረዶች የወደፊት ህይወታቸውን በራሳቸው እጅ እንዲቀርፁ እና በዚህ ስልጠና በሚገኘው ግንዛቤ ራሳቸውን መለወጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በአቻ መማማር ፣ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የራሱን ልምድና እውቀት ለሌሎች ለማካፈል እና ከሌሎች ለመማር የሚረዳ በመሆኑ አፍላ ወጣቶች ለጉዳይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሰልጣኝ ታገል ተሾመ አስገንዝበዋል።

የህይወት ክህሎት ሰዎች የእለት ተለት ኑሯቸው የሚያስፈልጋቸውን ፍላጎት ለማሟላትና የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በአወንታዊ መልኩ ለመፍታት የሚጠቀሙበት እውቀትና ብቃት እንደሆነም ከነበረው ስልጠና ለመረዳት ተችሏል።

ለአመቻቾችና አስተባባሪዎቹ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዩኒሴፍ እና ኬር ኢትዮጵያ ጋር በጋራ ያዘጋጁት ከ 10-14 እንዲሁም ከ 15-19 እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ አፍላ ወጣት ሴቶች የተዘጋጀው የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰነድ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ተሰጥቷል።

በቀጣይም ከአስተዳደሩ ወረዳ 1 እና 2 የተመረጡ 100 ልጃገረዶች በቀጣይ የሚሰጥ ሲሆን አላማውም ሴቶች ተግባራዊ ክህሎቶችን በመስጠት ራሳቸውን ችለው የተሻለ የወደፊት ህይወት እንዲገነቡ ማገዝ ነው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ፎቶግራፍ 📸 : ድሬ ቴቪ
ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም

16/08/2026
"ማዕከሉ በትውልድ ግንባታ ላይ መስራቱ የህፃናትን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመቅረጽ መሰረት ነው" —የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ​የአሲያ ጀማል ፋውንዴሽን የህፃናትና አረጋ...
15/08/2026

"ማዕከሉ በትውልድ ግንባታ ላይ መስራቱ የህፃናትን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመቅረጽ መሰረት ነው" —የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ

​የአሲያ ጀማል ፋውንዴሽን የህፃናትና አረጋውያን ሁለገብ ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሄደ።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማዕከሉ በትውልድ ግንባታ ላይ መስራቱ የህፃናትን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመቅረጽ፣ ነገን ለመወሰንና ብሩህ ተስፋን ለመሰነቅ ያለውን የጎላ ማህበራዊ ፋይዳ አብራርተዋል።

​ፋውንዴሽኑ ወደዚህ ግንባታ ከመግባቱ አስቀድሞ በከተማዋ የሚገኘውን የድሬዳዋ ህፃናት ማዕከል በመጎብኘትና ህፃናትን በመውሰድ የጀመረውን ተግባራዊ እንክብካቤ ያነሱት ምክትል ከንቲባው፤ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑትን ህፃናት በስነ-ምግባር ማነፅ የትውልድ እጣ ፈንታን የማቅናት ስራ በመሆኑ፣ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

​የፋውንዴሽኑ መስራች ወ/ሮ አሲያ ጀማል በበኩላቸው፤ ማዕከሉ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ህፃናትና አረጋውያን መጠለያና ሁለገብ እንክብካቤ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ ከጅማሮው አንስቶ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና ያቀረቡት መስራችዋ፤ ማዕከሉ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር ድረስ የሁሉም አካላት የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

​አቅመ-ደካሞችን መርዳትና ህፃናትን በስነ-ምግባር ኮትኩቶ ማሳደግ የሞራልም ሆነ የሃይማኖት ግዴታ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ናቸው። ማህበረሰቡ መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎችን በባለቤትነት ስሜት ሊደግፍ እንደሚገባ የጠቆሙት ኡስታዝ አቡበከር፤ ማዕከሉ የሰላም፣ የፍቅርና የጋራ መረዳዳት እሴቶች በተግባር የሚገለጡበት ታላቅ የትውልድ ግንባታ መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

​በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ለነበረው መልካም ጅማሮ የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

ለድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሰራተኞች በሪፎርም ጽንስ ሀሳብ እና አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ በአስተዳደራችን ደረጃ የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳ...
13/08/2026

ለድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሰራተኞች በሪፎርም ጽንስ ሀሳብ እና አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

በአስተዳደራችን ደረጃ የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች በብቃትና በውጤታማነት የሚፈጽሙ አሠራራቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በማዘመን ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ መንግስታዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም ተቋማትን ብቁ ማድረግ የሪፎርም ዓላማ መሆኑ ስልጠናውን የሰጡ ከአስተዳደሩ ሲቪል ሰርቪስ የመጡ ተጋባዥ ባለሞያ ለሰራተኞቹ አብራርተዋል።

ስልጠናው ቢሮው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የአሰረር ስርአትን በመዘርጋት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን የሪፎርም አተገባበር ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ እንደሆነም ተገልጿል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ልማት ማህበር በአስተዳደሩ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ስር ለሚገኙ ህፃናት የአልባሳት፣ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገየድሬዳዋ ልማት ማህበር በአስተዳደሩ ሴቶች...
08/08/2026

የድሬዳዋ ልማት ማህበር በአስተዳደሩ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ስር ለሚገኙ ህፃናት የአልባሳት፣ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

የድሬዳዋ ልማት ማህበር በአስተዳደሩ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር ባለው የህፃናት ማቆያ ማዕከል ለሚገኙ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ላጡ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት የሚውል የአልባሳት፣ የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

በህፃናት ማቆያ ማዕከሉ ተገኝተው ድጋፎቹን ያበረከቱት የድሬዳዋ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ከተማ ተሰማ እንደገለፁት ማህበሩ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን መደገፍ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ የሚገኙ ህፃናት የሁላችንም ልጆች ናቸው ያሉት አቶ ከተማ እነሱን መደገፍ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ሰው ኃላፊነት ብቻ አለመሆኑን ተረድተን ሁላችንም በተቻለን አቅም ከጎናቸው መቆም ይገባናል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት ልማትና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳፊያ ዮሱፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ፤ በተለይም የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች በስፋት በሚከናወኑበት በዚህ ወቅት ህፃናቱን በመደገፍ ረገድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ብለዋል።

ወ/ሮ ሳፊያ አያይዘውም ለህፃናቱ የሚደረገው ድጋፍ በተቋሙ ብቻ ሊሸፈን የሚችል ባለመሆኑ በዚህ የበጎ ፈቃድ ወቅት ግለሰቦች ፣ ተቋማትና የተለያዩ አካላት ለህፃናቱ በተቻላቸው መጠን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የህፃናቱን ኑሮ ለማሻሻል እና የእኔ የሚሉት ቤተሰብ እንዲኖራቸው አቅም ያለው ዜጋ ሁሉ በጉዲፈቻ እና በአደራ ቤተሰብ ወስዶ በማሳደግ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ጨምረው ገልፀዋል።

የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች የሚተገበሩበት ይህ ወቅት በተለይም ወላጆቻቸውን ላጡና ተጋላጭ ህፃናትን በመደገፍ የበጎነትና የሰብዓዊነት እሴቶችን በተግባር ለማሳየት የሚያስችል ወሳኝ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል።

Address

Dire Dawa

Telephone

+251251113634

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau:

Shortcuts

Share