Dire Dawa Environment, Forest and Climate Change Authority

Dire Dawa Environment, Forest and Climate Change Authority Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Dawa Environment, Forest and Climate Change Authority, Government Organization, Dire Dawa.

The main objective of the Authority is to ensure that all matters pertaining to the region's social and economic development activities are carried out in a manner that will protect the welfare of human beings.

12/07/2026
12/07/2026
የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን የ EAC ፕሮጀክት መጪውን የክረምት ወራት በማስመልከት፣ ኅብረተሰቡ ሊተገብራቸው በሚገቡ የቅድመ መከላከልና የጥንቃቄ መር...
12/07/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን የ EAC ፕሮጀክት መጪውን የክረምት ወራት በማስመልከት፣ ኅብረተሰቡ ሊተገብራቸው በሚገቡ የቅድመ መከላከልና የጥንቃቄ መርሆዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄደ

የአየር ንብረት ለውጥ በማኅበረሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽዕኖ ለማቃለልና የጎርፍ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በስፋት በንቅናቄ መልክ ለመተግበር ታቅዷል። ለዚህም ስኬት ከኅብረተሰቡ የተወከሉ የሕዝብ ተወካዮችና ከጤና ዘርፍ የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል። በጥናታዊ መድረኩ ላይ በጎርፍ ተጋላጭነትና በመፍትሔ ሐሳቦች ዙሪያ የተዘጋጁ ጽሑፎች ለውድድር የቀረቡ ሲሆን፤ ተሳታፊዎቹ የጎርፍ አደጋን በተግባር እንዴት መከላከል እንደሚቻል የሚያመላክት ዕቅድ አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሐመድ፤ ሀገር በቀል ዕውቀትን በሥራ ላይ በማዋል የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቆጣጠር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። ድሬዳዋ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኗ የችግሩ መጠን ሰፊና ጥልቅ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ የአካባቢ ጥበቃ፣ የአፈርና ደን እንክብካቤ እንዲሁም የጎርፍ ቅድመ መከላከል ሥራዎች በስፋትና በጥራት ሊከናወኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የባለሥልጣኑ የ EAC ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ በላይነህ ደስታ በበኩላቸው፤ ማኅበረሰቡን በስፋት ለመድረስና ግንዛቤውን ለማሳደግ ይህን መሰሉ መድረክ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በአስተዳደሩ ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭነት እንዳለባቸው በተለዩት ወረዳ 06 እና ወረዳ 09 መካከል ክረምት ከመግባቱ በፊት የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ የጤና ባለሙያዎች ስላላቸው አስተዋጽዖ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል። በዚህም የወረዳ 06 የጤና ባለሙያዎች የተሻለና ተግባራዊ የመፍትሔ አቅጣጫ በማመላከታቸው የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ተሸልመዋል። ከኅብረተሰቡ የተወከሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈው ውድድር ደግሞ የወረዳ 09 ተወካዮች የተሻለ የቅድመ መከላከል ሐሳብ በማቅረብ አሸናፊ መሆን ችለዋል።

በተያያዘም በኢፍቲን እና በጃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መካከል በጎርፍ ተጋላጭነት ዙሪያ በተካሄደው ተመሳሳይ የዕውቀት ውድድር፤ የጃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የበላይነቱን በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር የ 2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግ...
26/06/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር የ 2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በቢያአዋሌ ክላስተር፣ ቢሻን በሄ ገጠር ቀበሌ በይፋ ተካሂዷል።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 48 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ በቀጣይም ይህንን ቁጥር 65 ቢሊዮን ለማድረስ በዕቅድ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት ብቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ መያዙንም ከንቲባው ጠቁመዋል።

በዘንድሮው መርሃ-ግብር ደግሞ በአስተዳደሩ 5 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የጠቆሙት ክቡር ከንቲባው፣ መላው ማህበረሰብ በየአካባቢው ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል።

ክቡር ከንቲባው አያይዘውም የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት የማይተካ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ይህ ተግባር የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከማስጠራት ባለፈ፣ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመስጠትና ልምድ በማካፈል ለቀጠናዊ እድገትና የጋራ ትስስር አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ በመከናወኑ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በተለይም የአፈር ሀብት እንዳይሸረሸር በማድረግ፣ የአካባቢውን ስነ-ምህዳር በመጠበቅ፣ ለአርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ መርሃ-ግብሩ የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል።

ዘንድሮም በአስተዳደሩ ከአካባቢው ስነ-ምህዳር ጋር ተስማሚ የሆኑ ችግኞች በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ እንደሚተከሉ ኃላፊው ገልጸው፤ በዘንድሮው መርሃ-ግብር ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ (የፍራፍሬ) ሲሆኑ፣ ቀሪው 40 በመቶ ደግሞ ለጥላና ለውበት የሚውሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይህ አሰራር የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የገለጹት አቶ ኑረዲን፤ እንደ አስተዳደር የፓፓያ ክላስተር ልማትን በስፋት ለማስፋፋት ዛሬ የሚተከለው ችግኝ ዘላቂ ጠቀሜታ እንዳለው አስገንዝበዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን EAC ፕሮጀክት ለወረዳ 06 እና 09  የተለያዩ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገየድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደን ና አየር ንብረት...
26/06/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን EAC ፕሮጀክት ለወረዳ 06 እና 09 የተለያዩ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደን ና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን EAC ፕሮጀክት ከሚተገብራቸው ስራዎች አንዱ የተቋማትን አቅም መገንባት መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚገኘው EAC ፕሮጀክት ለሁለቱም ወረዳዋች አንድ አንድ ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች እና ፕሪንተሮች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዓለም የአካባቢ ቀን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ ​የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስል...
05/06/2026

የዓለም የአካባቢ ቀን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

​የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ53ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም የአካባቢ ቀን "በተፈጥሮ ተመስጦ፤ ለአየር ንብረት፤ ለወደፊታችን" ወይም "Climate Action" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት በጋራ በድምቀት አክብረዋል።

​የተዘጋጀው ፓናል ውይይት ዋና ዓላማ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ስለ አካባቢ ጥበቃ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠርና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረገውን ዘላቂ ጥረት በተግባር ማጠናከር እንደሆነ ተገልጿል።

​በበዓሉ በተዘጋጀው ፓናል ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ አብዱ መሐመድ የአየር ንብረት ለውጥ በአሁኑ ወቅት ለዓለማችንም ሆነ ለሀገራችን ትልቅ ስጋት እየሆነ መምጣቱን አስገንዝበዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ “የችግሩ ምንጭ እኛው ራሳችን እንደሆንን ሁሉ፣ መፍትሄውም በእጃችን ነው” ሲሉ የአካባቢ ጥበቃ የግልና የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የድርሻዋን በቁርጠኝነት እየተወጣች መሆኗን የጠቆሙት አቶ አብዱ፣ በተለይም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸውና የደን ሽፋኑ ማደጉ ለዚህ ትልቅ ማረጋገጫ መሆኑን በምሳሌነት አንስተዋል።

​የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ እና የአካባቢ ጥናት ክፍል መምህር የሆኑት ዶክተር ዮናስ ታደሰ በበኩላቸው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከ1972 ጀምሮ ስለ አካባቢ ጥበቃ በተለያዩ መድረኮች ሲወያይ ቢቆይም ዛሬ ላይ የምንገኝበት የአየር ንብረት ቀውስ ግን መፍትሄውን ከቃላት ባለፈ ወደ ተግባር በፍጥነት እንድንቀይር የሚያስገድድ መሆኑን ገልጸዋል።

​ዶክተር ዮናስ አክለውም ዛሬ የምናከብረው የአለም የአካባቢ ቀን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምናደርገውን ተጋድሎ በተግባራዊና በሳይንሳዊ መሰረት ላይ እንድንገነባ የሚያስታውስን መድረክ ነው ብለዋል።

​በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን አመራሮችና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በክረምት ወቅቱ በሚካሄዱ የችግኝ ተከላና ሌሎች ዘመቻዎች ብቻ ተወስነው መቅረት እንደሌለባቸው ገልጸዋል። ከዘመቻ ባለፈ እያንዳንዱ ግለሰብ በመኖሪያ አካባቢውና በየተሰማራበት የስራ መስክ በተግባር የተደገፈ ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋል።

​በዕለቱ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የዩኒቨርሲቲው የጂኦግራፊ እና የአካባቢ ጥናት ክፍል ከድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጋር በምርምርና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በቅርበት እየሰራ መሆኑ በሰፊው ተነስቷል።

ዩኒቨርሲቲው ከአካዳሚክ ማስተማር ስራው በዘለለ፣ ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂና ሳይንሳዊ መፍትሄዎችን ለማምጣት የሚያስችሉ ተግባራዊ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተመልክቷል።

​በፓናል ውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ባስተላለፉት መልእክት ዩኒቨርሲቲው መሰል የፓናል ውይይቶችን በማዘጋጀት እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ በተግባር የተደገፉ ስራዎችን ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን በጥናትና ምርምር እንደሚያከናውንና በመግለጽ የፓናል ውይይቱ ተጠናቋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በድሬዳዋ  የበልግ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ የሀርላ ቀበሌ ነዋሪዎችን በማስተባበር  በሀርላ ቀበሌ ችግኝ ተከላ እያካሄደ ይ...
30/03/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በድሬዳዋ የበልግ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ የሀርላ ቀበሌ ነዋሪዎችን በማስተባበር በሀርላ ቀበሌ ችግኝ ተከላ እያካሄደ ይገኛል ፡፡

የድሬዳዋ  አስተዳደር  የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ከአስተዳደሩ ደንብ አስከባሪና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በወረዳ 2 ሳቢያን አካባቢ በዋናነት መርመርሳና ሰባተኛ ...
27/03/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ከአስተዳደሩ ደንብ አስከባሪና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በወረዳ 2 ሳቢያን አካባቢ በዋናነት መርመርሳና ሰባተኛ ዙሪያ፣ በወረዳ 4 ገንደቆሬ አካባቢ እና በወረዳ 7 ሩዝ ተራና አላይበዴ አካባቢ በቅርቡ በጸደቀውና ወደ ትግበራ በገባው በአዲሱ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 ዓ/ም መሰረት ለማምረት እና ለመጠቀም የተከለከለውን የፕላስቲክ ከረጢቶችን እየተጠቀሙ በሚገኙ ከ1000 በላይ የፍራፍሬ ሻጮች፣ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮች፣ ኩድራ ሻጮችና እና አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ የድንገተኛ ክትትልና ቁጥጥር ስራ ተሰርቷል።

በተደረገው በዚህ ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ከ500 በላይ ግለሰቦች የተከለከለውን ፌስታል ሲጠቀሙ እጅ ከፍንጅ በመያዝ ባጠቃላይ 10 ኩንታል ፌስታሎችንና 10 የፕላስቲክ ጥቅሎችን ከመውረስ ባለፈ 100 ግለሰቦችን ለጥፋታቸው በህጉ መሰረት እያንዳንዳቸውን 2000 ብር (ሁለት ሺህ ብር) የተቀጡ ሲሆን የተቀሩትን ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የማስተማር ስራ ተሰርቷል።

በመጨረሻም ለዚህ የተቀናጀ ስራ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን የወረዳ 2፣ 4 እና 7 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እና ፖሊስ ጣቢያን ባለስልጣኑ ከልብ የመነጨ ምስጋናን እያቀረበ በቀጣይ ይህ አበረታች የቅንጅት ስራ በሌሎች ወረዳዎችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለስልጣኑ ያሳስባል።

20/03/2026
የድሬዳዋ  አስተዳደር  የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ከአስተዳደሩ ደንብ አስከባሪና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በወረዳ 2 ሳቢያን አካባቢ በዋናነት ሰኢዶና መስቀለኛ ዙ...
19/03/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ከአስተዳደሩ ደንብ አስከባሪና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በወረዳ 2 ሳቢያን አካባቢ በዋናነት ሰኢዶና መስቀለኛ ዙሪያ በቅርቡ በጸደቀውና ወደትግበራ በገባው በአዲሱ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 ዓ/ም መሰረት ለማምረት እና ለመጠቀም የተከለከለውን የፕላስቲክ ከረጢቶችን እየተጠቀሙ በሚገኙ ከ100 በላይ የፍራፍሬ ሻጮች፣ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮች፣ ኩድራ ሻጮችና እና አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ የድንገተኛ ክትትልና ቁጥጥር ስራ ተሰርቷል።

በተደረገው በዚህ ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ከ50 በላይ ግለሰቦች የተከለከለውን ፌስታል ሲጠቀሙ እጅ ከፍንጅ በመያዝ ፌስታሎችን ከመውረስ ባለፈ 15 ግለሰቦችን ለጥፋታቸው በህጉ መሰረት እያንዳንዳቸውን 2000 ብር (ሁለት ሺህ ብር) የተቀጡ ሲሆን የተቀሩትን ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የማስተማር ስራ ተሰርቷል።

በተመሳሳይ ሁኔታም በተደረገው በዚሁ የክትትልና ቁጥጥር ስራ በኮኔል አካባቢ በሚገኝ ትልቅ መጋዘን ውስጥ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው የፕላስቲክ ከረጢቶችን አከማችቶ ሲያከፋፍል የነበረ አብዱልዋሲ ኢብራሒም የተባለ ግለሰብ ከወረዳ 7 የደንብ አስከባሪዎች በደረሰን ጥቆማ መሰረት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ በመጋዘኑ ውስጥ በተደረገ ፍተቫ ባጠቃላይ 33 ኩንታል የፕላስቲክ ከረጢቶችን እና 3 ትልልቅ የፕላስቲክ ጥቅሎችን ሙሉ በሙሉ ለመውረስ ተችሏል።

በተጨማሪም ግለሰቡ ለፈጸመው ከፍተኛ ወንጀል በአዋጁ መሰረት 100,000 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር) በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ተደርጓል።

በመጨረሻም ለዚህ የተቀናጀ ስራ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን የወረዳ 7 የደንብ ማስከበር እና የወረዳ 7 ፖሊስ ጣቢያን ባለስልጣኑ ከልብ የመነጨ ምስጋናን እያቀረበ በቀጣይ ይህ አበረታች የቅንጅት ስራ በሌሎች ወረዳዎችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለስልጣኑ ያሳስባል።

Address

Dire Dawa

Opening Hours

Monday 07:00 - 17:00
Tuesday 07:00 - 17:00
Wednesday 07:00 - 17:00
Thursday 07:00 - 17:00
Friday 07:00 - 17:00

Telephone

+251251117663

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Environment, Forest and Climate Change Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Environment, Forest and Climate Change Authority:

Shortcuts

Share