Dire Dawa Environmental Protection Authority

Call Directions Website Contact the organization

Dire Dawa Environmental Protection Authority Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Dawa Environmental Protection Authority, Government Organization, Dire Dawa.

The main objective of the Authority is to ensure that all matters pertaining to the region's social and economic development activities are carried out in a manner that will protect the welfare of human beings.

የድሬዳዋ ከተማን የጎርፍ ተጋላጭነት ለመቀነስ እና የአረንጓዴ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይበልጥ ሊጎለብት እንደሚገባ ተጠቆመ።ከካናዳ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋ...
05/09/2026

የድሬዳዋ ከተማን የጎርፍ ተጋላጭነት ለመቀነስ እና የአረንጓዴ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይበልጥ ሊጎለብት እንደሚገባ ተጠቆመ።

ከካናዳ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በተፈጥሮ ጥበቃ እና በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው የሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት የማጠቃለያ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በደቻቱ ወንዝ ተፋሰስ ዙሪያ የአካባቢ ጥበቃን፣ የደን ሽፋንን ማጎልበትን እና የአፈር መሸርሸርን መከላከልን ዓላማ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የቆየው ይህ ፕሮጀክት፤ ከሁለት የአፍሪካ አገራት እንዲሁም WRI እና IISD ከተሰኙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሲሠራ ቆይቷል።

ፕሮጀክቱ በሐርላ፣ በኢጀአነኒ፣ በአዳዳ እና በለገቢራ ገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም በከተማው የአረንጓዴ ልማት (Greenery) ሥራዎች ላይ ላለፉት 2 ዓመታት ከ6 ወራት ሲተገበር ቆይቶ አሁን ላይ ተጠናቋል።

ከ876 ሺህ ሄክታር በላይ የተጎዳ መሬት እንዲያገግም ያደረገውና 1.4 ሚሊዮን ችግኞች የተከሉበት የዚህ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ መድረክ ላይ የድሬዳዋ ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተገኝተዋል። አቶ ኢብራሂም በሰጡት አስተያየት፤ የድሬዳዋን የጎርፍ ተጋላጭነት ሥጋት በመቀነስ እና የከተማዋን የአረንጓዴ ልማት በማሻሻል ረገድ ፕሮጀክቱ በጥሩ ውጤት ቢደመደምም፣ በቀጣይ የተገኘውን ስኬት አጠናክሮ የማስቀጠል ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው፤ የሰንካሳ ፕሮጀክት በከተሞች አካባቢ ጥበቃ እና በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ላይ ተቋማት በተቀናጀ መልኩ በመሥራት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡበት መሆኑን አብራርተዋል። በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገውን ይህንን ተሞክሮ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ለማስፋፋት በትጋት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

ከ14 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገው ይህ ልማት አገር በቀል ችግኞችን በመትከል እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ በማተኮር የተጎዱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ ማድረጉን የፕሮጀክቱ ማናጀር ዶክተር አዳነ ከበደ ጠቁመው፣ በዘርፉ የተሰማሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በስፋት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የኅብረተሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ይሳቅ ዩሱፍም ተቋማቸው ለፕሮጀክቱ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው፤ የተከናወኑት ሥራዎች የከተማዋን የጎርፍ ሥጋት ከመቀነሳቸው ባለፈ ለኅብረተሰቡ ሰፊ የዕድል በሮችን መክፈታቸውን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በገጠር ቀበሌዎች ላይ የደን ልማትን የማጎልበት (Afforestation)፣ የጥምር እርሻ (Agroforestry)፣ የወንዝ ዳር ልማት (Buffer Zone Development) ሥራዎችን እንዲሁም የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ አሳታፊ ተግባራትን በስኬት ያከናወነ ሲሆን፣ በዕለቱም ይህንን የሚያሳይ አውደ-ርዕይ ቀርቧል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካባቢን በዘላቂነት በመንከባከብ ረገድ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው ተገለፀ፡፡የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ ኮካኮላ ሰራተኞችና አ...
28/08/2026

አምራች ኢንዱስትሪዎች በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካባቢን በዘላቂነት በመንከባከብ ረገድ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው ተገለፀ፡፡
የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ ኮካኮላ ሰራተኞችና አመራሮች በቢዮ አዋሌ ክላስተር በኢጀአነኒ ቀበሌ አሮሬቲ መንደር በሚገኝ ቦታ ላይ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂደዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሆነውና ''ዛፍን ለነገ እንትከል /we are planting for tomorrow/'' በሚል ሀሳብ በተካሄደው በዚህ መርሀ ግብር የድሬደዋ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሀላፊ ተወካይ አቶ ደረጀ አቢቲ በተለይም አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን አምርተው ለገበያ ከማቅረብ ባለፈ በማህበራዊ አገልግሎት መሳተፍ እንደሚገባቸው የገለፁ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ መስኮች መሰል ተግባራትን እንዲያከናውኑ ባለስልጣኑ በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ አመራርና ሰራተኞች የተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ለሌሎች መሰል ተቋማት አርአያ እንደሚሆን አቶ ደረጀ ጨምረው ገልፀዋል።
ተቋሙ ችግኞቹን መትከል ብቻ ሳይሆን በሚገባ ፀድቀው እንዲሆኑ ባለሙያ በመመደብ የመንከባከብ ስራም በዘላቂነት ለማካሄድ ማቀዱን አስረድተዋል።
በአስተዳደሩ በአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር በህዝቡና በመንግስት ተቋማት ከሚደረገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ የግል ተቋማትና ግዙፍ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያደርጉት ተሳትፎ ከአካባቢ ጋር የተጣጣመ የምርት ሂደት እንዲኖራቸው በማስቻል ረገድ ትልቅ አስተዋፆኦ እንደሚያበረክት አቶ ደረጀ አቢቲ አመላክተዋል።

14/08/2026
14/08/2026
14/08/2026
14/08/2026
"ጽዱ ኢትዮጵያን ፤ ጽዱ ድሬዳዋን ለትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ ለሶስት ወራት የሚቆይ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ህዝባዊ ንቅናቄ ተጀመረ።"ጽዱ ኢትዮጵያን ፤ ጽዱ ድሬዳዋን ለትውልድ" በሚ...
13/08/2026

"ጽዱ ኢትዮጵያን ፤ ጽዱ ድሬዳዋን ለትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ ለሶስት ወራት የሚቆይ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ህዝባዊ ንቅናቄ ተጀመረ።
"ጽዱ ኢትዮጵያን ፤ ጽዱ ድሬዳዋን ለትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ በፕላስቲክ ቆሻሻ ፣ በአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም በድምጽ ብክለት ላይ ከሃምሌ እስከ መስከረም ወራት የሚቆይ የህዝብ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ።

በንቅናቄው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እንደተናገሩት ለሶስት ወራት በሚቆየው ንቅናቄ የማህበረሰባችንን አስተሳሰብ በመቀየር እና ግንዛቤን በማሳደግ ከየአካባቢው የሚወጣን ቆሻሻ ደረቅ ፣ እርጥብ እና መልሶ ጥቅም ላይ የሚውልን በመለየት አካባቢያችንን ፅዱ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

በአስተዳደሩ የፅዳት እና አካባቢ ጥበቃ የገፅ ለገፅ ንቅናቄ ስራዎች ከ400ሺ በላይ ዜጎችን ተሳታፊ ማድረግ መቻሉን ገልፀው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣውን አዋጅ የማስከበር ተግባር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው በአየር ንብረት ለውጥ አማካኝነት በተለይ በክረምት ወራት የዝናብ እጥረት እና በአንዳንድ ቦታዎች የጎርፍ አደጋ ፣ የብዝሃ ሕይወት መመናመን እንዲሁም የአካባቢ ብክለት እንደ አለም አቀፍም ሆነ በሀገር ደረጃ የሚታዩ ቀውሶች መሆናቸውን አንስተዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ከሀምሌ እስከ መስከረም ባሉት ሶስት ወራቶች የሚቆየው በዚህ ንቅናቄ ባሳለፍነው ሃምሌ ወር የስስ ፌስታሎችንና ፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ሙሉ በሙሉ ህጉን ማስከበር ላይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በያዝነው የነሃሴ ወርም ጊዜ ያለፈባቸውን ኬሚካል (መድኃኒቶች) እና አደገኛ ቆሻሻ (የኤሌክትሮኒክስ) ምርቶች አወጋገድ ላይ ንቅናቄው እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ከአካባቢ የሚወጣን ድምፅን በተቀመጠው መለኪያ በመቆጣጠር የድምፅ ብክለት ላይ የግንዛቤ ስራዎች በመስከረም ወር እንደሚከናወን ጨምረው አስረድተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሐመድ አባመጋል በንግግራቸው ንፅህና እና ፅዳት ከጓዳ ይጀምራል ያሉ ሲሆን የአስተዳደሩ አመራር እና ህብረተሰቡ በቅንጅት በአካባቢ ጥበቃ ፣ አረንጓዴ አሻራ እና በሌማት ትሩፋት ባከናወኗቸው ሰፋፊ ስራዎች የሚታይ ለውጥ መመዝገቡን አመላክተዋል።

የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የሶስተኛው ዙር ተግባራት ከሃምሌ 2018 እስከ መስከረም 2019 የሚቀጥል ሲሆን "ብክለት ይብቃ ፤ ውበት ይንቃ በሚል መሪ ሃሳብ የመጀመሪያው ዙር እንዲሁም "ጽዱ ኢትዮጵያን እስከ ባህል" በሚል መሪ ሃሳብ ሁለተኛው ዙር ንቅናቄ ባለፉት ሁለት ዓመታት መከናወኑ ይታወሳል።

Address

Dire Dawa

Opening Hours

Monday 07:00 - 17:00
Tuesday 07:00 - 17:00
Wednesday 07:00 - 17:00
Thursday 07:00 - 17:00
Friday 07:00 - 17:00

Telephone

+251251117663

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Environmental Protection Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Environmental Protection Authority:

Shortcuts

Share