26/05/2026
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር የኢድ አል አደሀ (አረፋ) በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
የተከበራችሁ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች እና መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የሁላችንም የጋራ መኖሪያችን የሆነችውን ድሬዳዋን በማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ የህግ ማውጣትና የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በምክር ቤቱ በተቋቋሙ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት የአስተዳደሩን አስፈጻሚ አካላት የስራ እንቅስቃሴ በመከታተል የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በማከናወን እንዲሁም በህዝብ ውክልና የውይይት መድረኮች የሚነሱ የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እና የተቋማቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ቅንጅታዊ ስራዎችን አጠናክሮ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
የአስተዳደሩ ነዋሪም ለአስተዳደሩ ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስረአት መረጋገጥ ዋነኛ መሳሪያ በሆነው የሀገራዊ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ በመሆን በአስተዳደሩ ዲሞክራሲያዊ የህዝብ አስተዳደር እንዲሁም የተጀመሩ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ እንዲሁም በአሉን በምናከብርበት ወቅት በአካባቢያችን ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖቻችንን በእስልምና አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት ያለንን በማካፈል በአሉን በደስታ እና በፍቅር እንዲያከብሩ እንድናደርግ ጥሪዬን እያቀረብኩ በአሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ