27/10/2025
Asaakih Ayro Kaxxa garabluk 17/02/2018 I.ll Qafar Rakakayih Dooltak Awsi Rasuk Dubte Daqaarih Majlis Gexiseh tan koboxul Sanat 2017 I.ll mizaniyat sanatih taama Gabbaqu Kee 2018 I.ll sanat mizaniyyat inki xongol faaticesen.
በዛሬው ዕለት 17/02/2018 ዓ.ም
የዱብቲ ወረዳ ምክር ቤት የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፓርት እና የ2018 በጀት ዓ.ም የሰራ እቅድና በጀት ለማፅደቅ በዛሬው ዕለት የተካሄደው መደበኛ ጉባዔ የ2018 ዓ.ም እቅድ ማስፈፀሚያ አጠቅላይ 184,791,385 ብር በማፅደቅ ጉባኤው ተጠናቋል ።
ጉባኤውን አሰመልክቶ የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ አቶ አሊ መሀመድ አሊ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት ሲሆን የ2017 በጀት አመት የእቅድ ክንውን ሪፓርት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወል አብዱ ኢሴ ለምክር ቤቱ አቅርቦ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተዋል ። ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች የወረዳው ካቢኔ አባላት እና በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ አወል አብዱ ኢሴ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጣቸው የቀረበውን ረፖርት እና እቅድ የምክር ቤቱ አባለት በሙሉ አፅድቋል ።
በመጨረሻም የዱብቲ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቴ አሊ መሀመድ የ2018 ዓ.ም ረቂቅ በጀት በዝርዝር ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ፦
➢ ለሠራተኞች ደመወዝ = 152, 322, 777.76
➢ ለስራ ማስኬጃ = 10, 468, 607.24
➢ ለካፒታል በጀት = 22, 000,000.00
በአጠቃላይ = 184, 791, 385, 00
==============
የተደለደለ ሲሆን የ2018 በጀት ከ2017 በጀት ጋር ሲነፃፀር በብዙ መመዘኛ የተሻለ ነው ያሉት አቶ ሀቴ አሊ በ2018 በጀት በወረዳው በዚህ አመት ይሰራል ተብሎ ለታቀደው የልማትና የፀጥታ ስራዎችን ለማሳለጥ በካፒታል በጀት የሚሰሩ ልማት ስራዎች ላይም ተይዟል ብለዋል ። አያያዘውም ከተበጀተው በጀት ውሰጥ ከወረዳው የሚሰበሰብ በገቢ የሚሸፍን በመሆኑ ከወትሮው በተሻለ መንገድ የገቢ ሰራ ላይ መረባረብ አለብን ብለዋል ።
በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አሰተያየት ያነሱ ሲሆን ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች የወረዳው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቴ አሊ መሀመድ እና የወረዳው ዋና አሰተዳደር አቶ አወል አብዱ ኢሴ ምላሽና ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን በጀት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።