Dubte Daqaarak Meqem kabaan kattaatih goli የዱብቲ ወረዳ የስነምግባር መከታተያ ክፍል

  • Home
  • Ethiopia
  • Dubti
  • Dubte Daqaarak Meqem kabaan kattaatih goli የዱብቲ ወረዳ የስነምግባር መከታተያ ክፍል

Dubte Daqaarak Meqem kabaan kattaatih goli የዱብቲ ወረዳ የስነምግባር መከታተያ ክፍል ሙስናን በጋራ እንከላከል

የዱብቲ ወረዳ የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በወረዳ ስር ከሚገኙ  ቀበሌዎች እና የመንግስት ሰራተኛች የብልፅግና ሕብረት የኮሚሽን አባላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ...
13/08/2026

የዱብቲ ወረዳ የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በወረዳ ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች እና የመንግስት ሰራተኛች የብልፅግና ሕብረት የኮሚሽን አባላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ አካሄደ።

በመድረኩም በአራቱ የትኩረት መስኮች ማለትም "በፓርቲ ፖለቲካዊ ጤንነት አጠባበቅ"፣ "በፓርቲ አባላት መብት አከበባር"፣ "በፓርቲ ሀብት አጠባበቅ" እና "በኮሚሽን ተቋማዊ አቅም ግንባታ" ስር የተካተቱ ግቦችና ዝርዝር ተግባራትንና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች እንዲሁም የግምገማና የሪፖርት ስርአቶች ላይ ገለፃ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም የዱብቲ ወረዳ የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ አቶ ሀሰን መሀመድ አይዳሂስ እንደተናገሩት በቀረበው ዓመታዊ ዕቅድ ግቦችና ተግባራት ዙሪያ ከኮሚሽንና ከፖርቲ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት የኮሚሽን ተቋማዊ አቅምን በሚገነባና የአንድ አቅድ፣ አንድ ሪፖርትና አንድ ምዘና መርህን በመከተል የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለመፈፀም መረባረበብ እንደሚገባ በማስገንዘብ ከቀበሌ ኮሚሽን ጋር የእቅድ ስምምነት ፊርማ በመከነወን የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።

!!
Dubte Daqaarak Leeda Partik Inispekshin kee meqem kaban Koomishin

13/08/2026
09/08/2026

#ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን፤ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም፤ ማንም ላይ ቢያርፍም ግን ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እንሰራለን!

**************

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!🏆 የላቀ አፈፃፀም እና እውቅና!የዱብቲ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ‐ምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ባሳየው የላቀ የስራ...
09/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

🏆 የላቀ አፈፃፀም እና እውቅና!

የዱብቲ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ‐ምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ባሳየው የላቀ የስራ አፈፃፀም፣ አርአያነት ያለው አገልግሎት እና የስነ-ምግባር መርሆችን በጥብቅ በመከተሉ በአውሲ ረሱ ዞን ደረጃ ከ12ቱም ወረዳ እና ከተማ መሰተዳድር ኮሚሽን #1ኛ ደረጃ በመውጣት የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

ይህ ሽልማት የመላው ኮሚሽን አመራሮችና አባላት ላሳዩት ያልተቋረጠ ጥረት፣ የተቀናጀ የአመራር ብቃት እና የስራ ቁርጠኝነት የተሰጠ የሚገባ እውቅና ሲሆን፤ በቀጣይም ለበለጠ ስራ እና አገልግሎት ትልቅ ብርታት የሚሆን ነው።

ለዱብቲ ወረዳ ኮሚሽን አመራሮች፣ አባላት እና ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

Hassen Mohammed Aydahis

"ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን፤ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም፤ ማንም ላይ ቢያርፍም ግን ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እንሰራለን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"Garqiinol Diggale Maqatta Beeno, woh Elle bahtam miyya kinni Maadiga. Faxe Maral Bahtu Nanu Diggale Taamomi taamitenno."

"ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን፤ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም፤ ማንም ላይ ቢያርፍም ግን ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እንሰራለን"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

09/08/2026
 #የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ ወደተሻለ ምዕራፍ እየተሻገረ ይገኛል!*********************አንዱ እና ዋናው ማሳያ፣ ሕዝቡ ሙስና አስከፊ መሆኑን እያጋጠመው ካለው ተጨባጭ...
09/08/2026

#የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ ወደተሻለ ምዕራፍ እየተሻገረ ይገኛል!

*********************

አንዱ እና ዋናው ማሳያ፣ ሕዝቡ ሙስና አስከፊ መሆኑን እያጋጠመው ካለው ተጨባጭ ችግር በመነሳት፣ መንግስት መፍትሔ እንዲሰጥ በሁሉም አቅጣጫ ጥያቄ አቅርቧል። ይህ መነቃቃት ለፀረ-ሙስና ትግል አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።

በመንግሥት በኩል ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለፀረ-ሙስና ትግል አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥሩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛል። ተቀዳሚው እርምጃ ዜጎችን ስለሙስና አስከፊነት እንዲሁም ሥነምግባራዊነት በተከታታይ ማስተማር፣ ማሰልጠን እና ማስገንዘብ ላይ እየተሰራበት ቆይቷል። ይህ እርምጃ መሠረታዊ እና ተገቢ በመሆኑ የሚቀጥል ይሆናል።

ሌለው እርምጃ፣ የሙስና ቅድመ-መከላከል እርምጃዎችን በርካታ የሙስና ወንጀሎችን አስቀድሞ የመከላከል እና ከምንጩ የማምከን ነው። ይህም፣ በሚገኝ እውነተኛ መረጃ እና ማስረጃ ልክ ውጤታማ የሆነ የተግባር እርምጃ ነው። በዚህ መስክ የሚወሰድ እርምጃ እና ውጤቱ በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እየተደረገ መሄድ አለበት። ይህ ደግሞ የሙስና ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ ከሚወሰድ እርምጃ በእጅጉ የተሻለ እና ሀብት ሳይባክን የመከላከል ትክክለኛ መፍትሔ ነው። የዚህ ውጤታማነት የሚረጋገጠው በዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ ነው።

የሙስና ወንጀል ሊፈጸም በሂደት ላይ እያለ በዜጎች ንቁ ተሳትፎ መረጃ እና ማስረጃ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለኮሚሽኑ በማቅረብ የሚወሰድ ቅንጅታዊ እርምጃ ነው። በዚህ ትግል አርዓያ የሆኑ ዜጎች ይመሰገናሉ። ሶስተኛ፣ የሙስና ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ በሚገኝ መረጃ እና ማስረጃ ልክ የሚወሰድ የሕግ ማስከበር የባለድርሻዎች፣ የዜጎች እና የኮሚሽኑ ቅንጅታዊ እርምጃ ነው።

በዚህ ተልዕኮ የኮሚሽኑ ሚና፣ በባለድርሻ ተቋማት የሚከናወነው የሙስና ወንጀል ምርመራ፣ ክስ፣ የፍርድ ውሳኔ እና የተመዘበረ ሀብት አመላለስ አሰራር ሥርዓት የግልጽነት፣ የተጠያቂነት እና የውጤታማነት ደረጃ መመዘን ሪፖርት ማዘጋጀት እና ለሚመለከተው ይፋ ማድረግ ነው። ሶስቱም ዋና ዋና የፀረ-ሙስና ትግል ምሶሶዎች የተቀናጁ፣ የተናበቡ፣ ህዝባዊ እና ተቋማዊ መሠረት የሚኖራቸው የማይነጣጠሉ እርምጃዎች ናቸው።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሕጎች፣ በፖሊሲ፣ በሙስና ወንጀል መረጃ ቅበላ እና ሀብት ምዝገባ ሥራዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማጎልበት እንዲሁም የባለድርሻዎች ትብብር እና ትስስር የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር መልካም ጅምሮች መሆናቸው ታይቷል። አሁን ላይ፣ ኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ አገራዊ አንገብጋቢ አጀንዳ መሆኑን በማመን በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተመረጡት ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች አንዱ በመደረጉ ለፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ በዋና ዋና መሠረታዊ መርሆዎች አገራዊ መግባባት እና በጋራ መቆም ከሁሉም ባለድርሻዎች የሚጠበቅ ብሔራዊ ቁልፍ አጀንዳ ነው። ስለሆነም፣ ከተለመደው አዋጭ ያልሆነ አካሄድ የምንላቀቅበት ጊዜ በጉጉት ይጠበቃል። በደካማ የፀረ-ሙስና ሥርዓት፣ የሰለም፣ ልማት እና ዲሞክራሲ ግንባታ ከሚደናቀፍ፣ ሁሉም ባለድርሻዎች ትርጉም ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት ሁሉንአቀፍ የመፍትሔ አቅጣጫ መከተል ይገባናል።

"ሲሾም ያልበላ፣ ሲሻር ይቆጨዋል" ከሚል አባባል ወጥተን.......! ሲሉ የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒ.ኤች.ዲ) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

09/08/2026

#የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ ወደተሻለ ምዕራፍ እየተሻገረ ይገኛል!

*********************

አንዱ እና ዋናው ማሳያ፣ ሕዝቡ ሙስና አስከፊ መሆኑን እያጋጠመው ካለው ተጨባጭ ችግር በመነሳት፣ መንግስት መፍትሔ እንዲሰጥ በሁሉም አቅጣጫ ጥያቄ አቅርቧል። ይህ መነቃቃት ለፀረ-ሙስና ትግል አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።

በመንግሥት በኩል ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለፀረ-ሙስና ትግል አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥሩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛል። ተቀዳሚው እርምጃ ዜጎችን ስለሙስና አስከፊነት እንዲሁም ሥነምግባራዊነት በተከታታይ ማስተማር፣ ማሰልጠን እና ማስገንዘብ ላይ እየተሰራበት ቆይቷል። ይህ እርምጃ መሠረታዊ እና ተገቢ በመሆኑ የሚቀጥል ይሆናል።

ሌለው እርምጃ፣ የሙስና ቅድመ-መከላከል እርምጃዎችን በርካታ የሙስና ወንጀሎችን አስቀድሞ የመከላከል እና ከምንጩ የማምከን ነው። ይህም፣ በሚገኝ እውነተኛ መረጃ እና ማስረጃ ልክ ውጤታማ የሆነ የተግባር እርምጃ ነው። በዚህ መስክ የሚወሰድ እርምጃ እና ውጤቱ በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እየተደረገ መሄድ አለበት። ይህ ደግሞ የሙስና ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ ከሚወሰድ እርምጃ በእጅጉ የተሻለ እና ሀብት ሳይባክን የመከላከል ትክክለኛ መፍትሔ ነው። የዚህ ውጤታማነት የሚረጋገጠው በዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ ነው።

የሙስና ወንጀል ሊፈጸም በሂደት ላይ እያለ በዜጎች ንቁ ተሳትፎ መረጃ እና ማስረጃ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለኮሚሽኑ በማቅረብ የሚወሰድ ቅንጅታዊ እርምጃ ነው። በዚህ ትግል አርዓያ የሆኑ ዜጎች ይመሰገናሉ። ሶስተኛ፣ የሙስና ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ በሚገኝ መረጃ እና ማስረጃ ልክ የሚወሰድ የሕግ ማስከበር የባለድርሻዎች፣ የዜጎች እና የኮሚሽኑ ቅንጅታዊ እርምጃ ነው።

በዚህ ተልዕኮ የኮሚሽኑ ሚና፣ በባለድርሻ ተቋማት የሚከናወነው የሙስና ወንጀል ምርመራ፣ ክስ፣ የፍርድ ውሳኔ እና የተመዘበረ ሀብት አመላለስ አሰራር ሥርዓት የግልጽነት፣ የተጠያቂነት እና የውጤታማነት ደረጃ መመዘን ሪፖርት ማዘጋጀት እና ለሚመለከተው ይፋ ማድረግ ነው። ሶስቱም ዋና ዋና የፀረ-ሙስና ትግል ምሶሶዎች የተቀናጁ፣ የተናበቡ፣ ህዝባዊ እና ተቋማዊ መሠረት የሚኖራቸው የማይነጣጠሉ እርምጃዎች ናቸው።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሕጎች፣ በፖሊሲ፣ በሙስና ወንጀል መረጃ ቅበላ እና ሀብት ምዝገባ ሥራዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማጎልበት እንዲሁም የባለድርሻዎች ትብብር እና ትስስር የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር መልካም ጅምሮች መሆናቸው ታይቷል። አሁን ላይ፣ ኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ አገራዊ አንገብጋቢ አጀንዳ መሆኑን በማመን በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተመረጡት ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች አንዱ በመደረጉ ለፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ በዋና ዋና መሠረታዊ መርሆዎች አገራዊ መግባባት እና በጋራ መቆም ከሁሉም ባለድርሻዎች የሚጠበቅ ብሔራዊ ቁልፍ አጀንዳ ነው። ስለሆነም፣ ከተለመደው አዋጭ ያልሆነ አካሄድ የምንላቀቅበት ጊዜ በጉጉት ይጠበቃል። በደካማ የፀረ-ሙስና ሥርዓት፣ የሰለም፣ ልማት እና ዲሞክራሲ ግንባታ ከሚደናቀፍ፣ ሁሉም ባለድርሻዎች ትርጉም ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት ሁሉንአቀፍ የመፍትሔ አቅጣጫ መከተል ይገባናል።

"ሲሾም ያልበላ፣ ሲሻር ይቆጨዋል" ከሚል አባባል ወጥተን.......! ሲሉ የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒ.ኤች.ዲ) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Address

Dubti

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dubte Daqaarak Meqem kabaan kattaatih goli የዱብቲ ወረዳ የስነምግባር መከታተያ ክፍል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dubte Daqaarak Meqem kabaan kattaatih goli የዱብቲ ወረዳ የስነምግባር መከታተያ ክፍል:

Shortcuts

Share