04/09/2026
በአዲሎ ከተማ የኮሪደር ልማት የወሰን ማስከበር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ
አዲሎ፣ ነሐሴ 29/2018/መንግስት ኮሙኒኬሽን/
በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ አዲሎ ከተማ የኮሪደር ልማት የወሰን ማስከበር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
በሥፍራው የተገኙት የአዲሎ ዙሪያ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ብርሃኑ አበጌ እና የአዲሎ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግነት አብርሃም እንደገለጹት በከተማው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱን በተሳካ ሁኔታ ለማስቀጠል በፕላኑ መሠረት ተለክቶ በኮሪደሩ ወሰን ውስጥ የገቡ አጥሮችን፣ ቤቶችንና የተለያዩ እንጨቶችን በቀለም የመለየት ተግባር እየተከናወነ ይገኛል።
በተጀመረው የመንገድ ዳር ወሰን ልየታ ስራው በቀለም ምልክት የተደረገባቸውን ንብረቶች ባለቤቶቹ እያነሱት እንደሚገኙ የጠቀሱት ኃላፊዎች ህብረተሰቡ ለልማቱ እያደረገ ላለው በጎ ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
የተጀመረው ልማት በተያዘለት ፍጥነት እንዲከናወን በኮሪደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ ንብረቶችን ህብረተሰቡ በፍጥነት እንዲያነሳም ጥሪ አቅርበዋል።
ከነዋሪዎችም መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት የወሰን ልየታ የተጀመረባቸዉ ቦታዎች የመንገዱ ስፋት ለከተማው ከአሁኑ ተጨማሪ ውበት እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰዉ የተጀመረዉ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡