Central Ethiopia Region Bureau of Agriculture

Central Ethiopia  Region Bureau of Agriculture This is official page Central Ethiopia Region Bureau of agriculture
(1)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ የ2019 ዋና ዋና ግቦች እና  በሚጠበቁ ውጥቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የውል ስምምነት ተፈራረመ።ነሐሴ 29/2018ስምምነቱ በክልሉ ከሚገኙ...
04/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ የ2019 ዋና ዋና ግቦች እና በሚጠበቁ ውጥቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የውል ስምምነት ተፈራረመ።

ነሐሴ 29/2018

ስምምነቱ በክልሉ ከሚገኙ ዞኖችና የልዩ ወረዳ ህብረት ሥራ መዋቅሮች ጋር የተደረገ ነው።

ስምምነቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጎዴቦ ከዞንና ከልዩ ወረዳ ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል።

ይህም በ2018 የተገኙ ስኬቶችን በ2019 በተሻለ መንገድ አስፍቶና አልቆ ለማስቀጠል ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ተሰጠበክልሉ በሀገራዊና ክልላዊ ፈተናዎች ከፍተኛ ጤት ላስመዘገቡ፣በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ...
04/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ተሰጠ

በክልሉ በሀገራዊና ክልላዊ ፈተናዎች ከፍተኛ ጤት ላስመዘገቡ፣በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ የትምህርት ስራ ዎች የላቀ ውጤት ላመጡ ለዞኖች እና ለልዩ ወረዳዎች፣ ለአዳሪ ትሞህርት ቤቶች፣ ለ2ኛ ደረጃ ፣ለአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

04/09/2026
በኢትዮጵያ የኢትዮሼፕ የጃፓን የሥራ ኃላፊዎች በከምባታ ዞን አዲሎ ወረዳ ሀሚዶ ጎፎሮ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር የመስክ ምልከታ አደረጉ።ነሐሴ/2018የመስክ ምልከታው በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ ...
04/09/2026

በኢትዮጵያ የኢትዮሼፕ የጃፓን የሥራ ኃላፊዎች በከምባታ ዞን አዲሎ ወረዳ ሀሚዶ ጎፎሮ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር የመስክ ምልከታ አደረጉ።

ነሐሴ/2018

የመስክ ምልከታው በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የፕሮግራሙ ዓመታዊ አፈጻጸም በክልሉ ዱራሜ ከተማ ከተገመገመ በኋላ የተካሄደ ነው።

የመስክ ምልከታውን የመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ በመስክ ምልከታው ለሥራ ኃላፊዎቹ ገለጻ አድርገዋል።

ግብርናን ከተለመደው የምርት አቀራረብ በማሻገር ገበያ ተኮር፣ ቴክኖሎጂ ተኮርና ውሃ ተኮር ግብርና እንዲሆን በተለይም “ምን ይመረታል? ለማን ይመረታል? መቼ ይመረታል?” በሚሉ ቁልፍ ጥያቄዎች ላይ ተመሥርቶ መሥራትን ትኩረት አድርጎ በመሥራት በአጭር ጊዜ ውጤት የመጣበት አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

በወጣቱ ሞዴል አርሶ አደር አብነት ዲላሞ የተሠራውን ሥራ አረንጓዴው ቡቲክ ያሉት አቶ ኡስማን ሱሩር፣ ተግባሩ አዳዲስ ልምምዶች እንዲፈጠሩ ስለማድረጉ ገልጸዋል።

በተለይም በአጭር ጊዜ በፍራፍሬ፣ በቡናና ቅመማ ቅመም ሥራዎች ከክልል አልፎ ለተለያዩ አካባቢዎች ተሞክሮ መቀየር የሚያስችል ስለመሆኑ ኃላፊው ገልጸዋል።

ይህ የወጣት አብነት ትጋት በግለሰቦች ጥረት አካባቢን መቀየር እንደሚያስችል የሚያረጋግጥ እውነተኛ ማሳያ ከመሆን አልፎ ጠንካራ አስተማሪ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።

በመስክ ምልከታው ወቅት አስተያየት የሰጡት የኢትዮሼፕ የኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪ ያሱዩዩኪ ዩሲሙራ፣ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የተለያዩ ቦታዎችን የመስክ ምልከታ ማድረጋቸውንና በገጠር ደረጃ በዚህ ልክ ጥራት ያላቸው ሥራዎችን ሌሎችም አካባቢዎች እንዲማሩባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ወጣት አርሶአደር አብነት ዲላሞ በበኩሉ የተሻለ ነገር ሰርቶ በግብርናው ዘርፍ ተጠቃሚ መሆንና የተቀናጀ የግብርና ልማትን ውጤታማ በማድረግ ድህነት ማሸነፍ እንደሚቻል ሃገራዊ ምሳሌ ለመሆን እየተጋ እንደሚገኝ ገልጿል።

በመስክ ምልከታው የፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ አስተባባሪዎች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፕሮግራምና ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኅብረት ሥራ ልማት ኤጄንሲ በ2018 በጀት ዓመት   ውጤታማ ለሆኑ መዋቅሮች እውቅና ሰጠ።******************ነሐሴ 29/2018እውቅናውን የማዕከላዊ ኢትዮጵ...
04/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኅብረት ሥራ ልማት ኤጄንሲ በ2018 በጀት ዓመት ውጤታማ ለሆኑ መዋቅሮች እውቅና ሰጠ።
******************
ነሐሴ 29/2018

እውቅናውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጎዴቦ ተቀብለዋል።

በዚህም መሰረት

1ኛ. ስልጤ ዞን ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት፦ የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ

2ኛ. ጉራጌ ዞን ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት :- የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ

3ኛ. ምስራቅ ጉራጌ ዞን ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት:- የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ

በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች በዓመቱ በህብረት ስራ ሪፎርም፣ በቁጠባና ካፒታል ማሳደግ ፣ ከሰንበት እሰከ ሰንበት ገበያ በማሳተፍ እንዲሁም በሌሎችም አፈፃፀሞች ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉት ጥረት ሁሉም መዋቅሮች ከህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ የእውቅና ሰርቲፊኬት ተሰጥቷቸዋል።

Address

Durame

Telephone

+251935490375

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region Bureau of Agriculture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share