Central Ethiopia Regional state OCAA

Central Ethiopia Regional state OCAA Official page of Central Ethiopia Regional State Education and Training Quality Regulation Authority(CERS ETQRA)

በትምህርት ስርዓት ውስጥ የመምህራን ሙያዊ ብቃት ማደግ ያለው አበርክቶበትምህርት ስርዓት ውስጥ የመምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት ማደግ ለትምህርት ጥራት መረጋ...
03/09/2026

በትምህርት ስርዓት ውስጥ የመምህራን ሙያዊ ብቃት ማደግ ያለው አበርክቶ

በትምህርት ስርዓት ውስጥ የመምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት ማደግ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ዋናው መሠረት ነው::

የዚህን ተልዕኮ ስኬት ለማረጋገጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት 3 ዓመት ጊዜያት በርካታ ተግባራትን በማከናወን ተስፋ ሰጪ ለውጦችን አስመዝግቧል::

⭕️የአካባቢ ቋንቋዎችን ማበልጸግ እና ብዝሃነትን ማጎልበት

የቋንቋ እና የባህል ብዝሃነትን ከትምህርት ስርዓቱ ጋር ለማቀናጀት በተደረገው ጥረት በሆሳዕና ኮሌጅ የየምሳ፣ ሀላቢሳ፣ ጠምባሪሳ፣ ጉራጊኛ እና ማረቆኛ አፍ መፍቻ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍሎች ተከፍተው ስራ ጀምረዋል::

ይህም መምህራን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተሰልጥነው ተካኪ ትውልድን በብቃት እንዲያፈሩ ትልቅ እድል ፈጥሯል::

⭕️የስልጠና ፕሮግራሞች ማስፋፊያ እና አቅም ግንባታ

የትምህርት ሽፋንን ለማሳደግ በሆሳዕና፣ ዱራሜ፣ ወራቤ እና ወልቂጤ የሳምንት መጨረሻ (Week-end) ፕሮግራሞች በመከፈታቸው የቅድመ-አንደኛ መምህራን ሽፋን ከ27.5% ወደ 29.5% ማደግ ችሏል::

ከዚህ በተጨማሪ በክረምት ወቅት 1,200 የቅድመ-አንደኛ መምህራን ስልጠናቸውን አጠናቀዋል::

⭕️የመምህራን እና አመራሮችን ክፍተት ለመሙላት ከተከናወኑት አቅም ግንባታዎች መካከል፡

የ2ኛ ደረጃ ተፈጥሮ ሳይንስ መምህራንልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣የማህበራዊ ሳይንስ መምህራን ስልጠና እና የትምህርት ቤት አመራሮችየአመራርነት ብቃት ማጎልበቻ ስልጠና ተጠቃሽ ናቸው።

በዘርፉ እየተደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ርብርብ የክልሉን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ያፋጥነዋል::

አደረጃጀት ክልላዊና ሀገራዊ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ፣የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሳሪያ ነው፦ አቶ ይግለጡ አብዛ‎‎የፓርቲ ስነ ምግባር ጠብቆ በመንቀሳቀስና ስራዎችን በአደረጃጀት በመፈጸም የ...
03/09/2026

አደረጃጀት ክልላዊና ሀገራዊ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ፣የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሳሪያ ነው፦ አቶ ይግለጡ አብዛ

‎የፓርቲ ስነ ምግባር ጠብቆ በመንቀሳቀስና ስራዎችን በአደረጃጀት በመፈጸም የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ አሳሰበ።

‎ዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና አፈጻጸሞቹን
‎፣የተገኙ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ነው።

‎መድረኩን የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አደረጃጀቶቹን በመጠቀም ትላልቅ ክልላዊና ሀገራዊ ስራዎችን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።

‎ተደራጅቶና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ ክልልንም ሆነ ሀገርን ለማሻገር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው፣
‎በመመሪያና በአሰራር ስርዓት ተደግፎ ስራን መስራት የላቀ ውጤት ለማምጣት እንደሚያስችልም አመላክተዋል።

‎የአደረጃጀት ዘርፉን ችግሮች መፍታት ከተቻለ ሌሎች ችግሮችን በወሳኝ ደረጃ መፍታት እንደሚቻልና ለዚህም የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ለተሰጣቸው ተልዕኮ በልዩ ቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱም አቶ ይግለጡ አሳስበዋል።

‎የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት፣የመሬት ወረራን ለመከላከል፣
‎ሌብነትና ጎሰኝነትን ለመዋጋት፣በአጠቃላይም የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አደረጃጀቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያብራሩት አቶ ይግለጡ አብዛ፣የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በዚህ ልክ በመገንዘብ ጥራት ያለው አደረጃጀት በመገንባትና ወደ ስራ በማስገባቱ ሂደት ላይ ሰፊ ርብርብ እንዲያደርጉም መመሪያ ሰጥተዋል።

‎አደረጃጀት ክልላዊና ሀገራዊ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ፣የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሳሪያ
‎፣ድህነትን በማሸነፍ ብልጽግናን ማረጋገጫ አይነተኛ መሳሪያ መሆኑንም አመላክተው፣ህጎችን ደንቦችንና መመሪያዎችን ጠብቆ መስራት የአዲሱ በጀት ዓመት ቁልፍ አጀንዳ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

‎በአዲሱ በጀት ዓመት የመረጃ መጣረስና መዛባት ችግሮችን ለመፍታት፣ስራዎችን በለሆሳስ ሳይሆን በትግልና በቁርጠኝነት ለመምራት፣የግለሰብን ሳይሆን የብልጽግናን ገጽታ ለመገንባት ብርቱ ርብርብ በየደረጃው መካሄድ እንዳለበትም ያሳሰቡት አቶ ይግለጡ፣ያሉትን ጠንካራ መመሪያዎች ወደ መሬት በማውረድና በመተግበር ውጤት ለማምጣት በቂ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ደምሴ የዘርፉን አፈጻጸምና የትኩረት አቅጣጫ ሪፖርት ሲያቀርቡ እንደገለጹት፣በክልሉ የሚገኙ አደረጃጀቶች ባደረጉት ርብርብ በየዘርፉ የተሻለ ውጤት እንዲገኝ ማድረግ ችለዋል።

‎በዘርፉ ወጥነት ያለው ስራ ያለመስራት፣የአሰራርና የመመሪያ ጥሰት፣የአደረጃጀቶቹ አፈጻጸም ያለመመጣጠን፣የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ውስንነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች በዘርፉ መታየታቸውን አቶ ሀብታሙ አብራርተው፣የ2019 ዋናው ትኩረት ጥራት ያለውና ተልዕኮውን በአግባቡ መወጣት የሚችል አደረጃጀት መገንባትና ማጠናከር እንደሆነም አሳውቀዋል።

‎የፓርቲን የመሪነት ሚና ከፍ ማድረግ ፣የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ስራዎችን ማጎልበት፣ዘርፉን ወደ ዲጂታላይዜሽን ማስገባት፣በፓርቲ መርህ ከላይ እስከታች ተግባራትን መፈጸም ወሳኝ ጉዳዮችና ተልዕኮዎች መሆናቸውንም አቶ ሀብታሙ ደምሴ አብራርተዋል።

‎ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ ከአፈጻጸምና ከቀጣይ ዕቅድ ውይይት በተጨማሪ ዘርፉን ለማሻገር የላቀ እገዛ በሚሰጠው ዲጂታላይዜሽን ላይ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥም ተመላክቷል።

_ብልፅግና

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አምስት ዓመታት የከተሞ...
03/09/2026

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አምስት ዓመታት የከተሞችን እድገት ማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ የከተሞች እድገት በቀጣይ ዓመታት እየተሻሻለ መምጣት እንዳለበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የጋራ ተግባቦት መፈጠሩን ተናግረዋል።

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

ከተሞች ለኑሮ፣ለንግድ እና ለኢንቬስትመንት ተመራጭ በማድረግ ሂደት ያልተሟሉ ጉዳዮች መኖራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ባለፉት ዓመታት ከተሞችን ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ነገር ግን በሚፈለገው ደረጃ የተሟላ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በቀጣዩ አምስት ዓመታት ሰባት ዋና ዋና ከተሞች ሊተገበሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር አስፈላጊ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በሚቀጥሉት ዓምስት አመታት በከተሞች እድገት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት አስቀድሞ ማቀድ አስፈላጊ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የአምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ምክክር እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።

የትምህርት ቤት ምግባ" ለትምህርት ጥራትና ለተስፋ የተዘረጋ እጅየትምህርት ጥራትና የወደፊት ተስፋ የሚጀምረው ከተማሪዎች ደህንነት ነው። ባዶ ሆድ የማሰብ፣ የመረዳትና የማስታወስ አቅምን ያዳክ...
03/09/2026

የትምህርት ቤት ምግባ" ለትምህርት ጥራትና ለተስፋ የተዘረጋ እጅ

የትምህርት ጥራትና የወደፊት ተስፋ የሚጀምረው ከተማሪዎች ደህንነት ነው። ባዶ ሆድ የማሰብ፣ የመረዳትና የማስታወስ አቅምን ያዳክማል።

በተቃራኒው ደግሞ የተመጣጠነ ምግብ ያገኘ ተማሪ አእምሮው ይነቃል፣ ትኩረቱ ይጨምራል፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርገው ጉዞም ደስ የሚል ይሆንለታል።

በመሆኑም የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተራ የምግብ ድጋፍ ሳይሆን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ የሚያስችል ወሳኝ መርሃ-ግብር ነው።

በተለይም ከኢኮኖሚ አቅም አንፃር ዝቅተኛ ከሆኑ ቤተሰቦች የሚመጡና ለድርቅ አደጋ በተጋለጡ አካባቢዎች የሚገኙ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይሰናከሉ ማድረግ የፍትሃዊነት ጥያቄ ነው።

ይህንን እውነታ በመገንዘብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት (ከ2016 - 2018 ዓ.ም) በተከናወኑት ስራዎች በርካታ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

⭕️ የበጀት እና የማህበረሰብ አስተዋፅኦ እድገት
የመንግስት በጀት ከ2016 ዓ.ም ከነበረበት 16.4 ሚሊዮን ብር በ2017 ዓ.ም ወደ 20 ሚሊዮን ብር፣ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ወደ 22 ሚሊዮን ብር አድጓል።
በ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አስተዋፅኦ ያልነበረ ቢሆንም፣ በ2017 ዓ.ም 90.85 ሚሊዮን ብር በላይ፣ በ2018 ዓ.ም ደግሞ 92.24 ሚሊዮን ብር በላይ በማስመዝገብ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል። ይህም የህዝቡን የባለቤትነት ስሜት እና የደገፋውን አስፈላጊነት ያመላክታል።

⭕️ የተጠቃሚ ትምህርት ቤቶች ስፋት

በ2016 ዓ.ም የተጠቃሚ ትምህርት ቤቶች ብዛት 66 ብቻ የነበረ ሲሆን፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 329 አድጓል (70 በመንግስት እና 259 በማህበረሰብ የተሸፈኑ) ናቸው።

በ2018 ዓ.ም የማህበረሰቡ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ በማደጉ የተጠቃሚ ትምህርት ቤቶች ብዛት 735 ደርሷል (70 በመንግስት እና 665 በማህበረሰብ የተሸፈኑ) ናቸው።

⭕️ የተጠቃሚ ተማሪዎች ቁጥር እና የሴቶች ተሳትፎ
አጠቃላይ የተማሪዎች ብዛት በ2016 ዓ.ም ከነበረበት 54,671 ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 117,960፣ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ወደ 247,722 አድጓል።
የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ በ2017 ዓ.ም ከተጠቀሙት ተማሪዎች መካከል 55,782 ሴቶች ሲሆኑ፣ በ2018 ዓ.ም ይህ ቁጥር ወደ 123,299 አድጓል። ይህም ፕሮግራሙ ለፆታ ፍትሃዊነት ያበረከተውን አስተዋፅኦ ያሳያል።

⭕️ የህዝብ ተሳትፎና ያመጣው ውጤት

ከዓመት ወደ ዓመት በመንግስት የተመደበው በጀት እየጨመረ ከመሄዱም ባሻገር፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ያደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የፕሮግራሙን ተደራሽነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል፤ በተለይም በ2018 ዓ.ም የህዝቡ ተሳትፎ ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ በማድረስ የመገበባቸውን ትምህርት ቤቶች ብዛት 735 ማድረስ ተችሏል።

ይህ ጥረት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ የትምህርት አቀባበላቸው እንዲሻሻልና የትምህርት ብክነት (ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ) በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል።

በትምህርት ቤት ምገባ የተዘረጋው እጅ የዛሬ ህፃናትን ሆድ ብቻ ሳይሆን የነገዋን ሀገር ተስፋ የሚገነባ መሆኑን ባለፉት ሶስት ዓመታት የታዩት ፍሬዎች ምስክሮች ናቸው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ላለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን የልማት ጉዞዎች አስመልክቶ በሚያደርገው የምክክር መድረክ 3ኛ ቀን ውሎ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳ...
02/09/2026

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ላለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን የልማት ጉዞዎች አስመልክቶ በሚያደርገው የምክክር መድረክ 3ኛ ቀን ውሎ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል

የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል የቢሮ ኃላፊዎች እንድሁም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም ባከናወናቸው የመዋቅር፣ የፖሊሲና የአሠራር ሪፎርሞች ከ20.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገለጸ።

በዚህም አጠቃላይ የሥራ ዕድል ውስጥ ከ19 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን የገለጹ ስሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ደግሞ በሕጋዊ መንገድ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውንም አንስተዋል ።

ይህ አፈጻጸም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በዘርፉ ያካሄዳቸው ዘመናዊ አሠራሮችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ውጤት ማምጣታቸውን የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

​በተጨማሪም የኢንተርፕራይዞችን ዕድገትና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት ሁለገብ ድጋፎች መደረጉም ተገልጿል።

በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት 166 ቢሊዮን ብር ብድር በማቅረብ ከ900 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ 295 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የገበያ ትስስር በመፍጠርም ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ኢንተርፕራይዞች የድጋፉ ተጠቃሚ መሆናቸውን ፤ ከመሬትና መሠረተ ልማት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተከናወኑት ሥራዎችም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉንም አንስተዋል።

በተጨማሪም የህግ ማዕቀፎች ማሻሻላቸው፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እስከ አንድ ማዕከል የተናበበ መዋቅር መዘርጋቱ፣አዳዲስ እሳቤዎችና ዘረ-መሎች መዘጋጀታቸውና ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚደረጉ ጥረቶች ተቋሙ እያደረገ ያለዉን ጉዞ ከማሳለጥ አንፃር ጉልህ ሚና እንደነበርም ተገልጿል።

ከአዲሶቹ እሳቤዎች አንዱ ተቋማቱን «ኢንተርፕረነሪያል» ማድረግ እንደመሆኑ ተቋማት የኢንተርፕረነርሽፕ እሳቤን በመተግበር በዜጎች ተጠቃሚነትና በሀገር እድገት ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ እድል እንደሰጣቸው ውይይቱ ላይ በስፋት ተነስቷል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል  ዘመናትን የተሻገረ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተ...
02/09/2026

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል ዘመናትን የተሻገረ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በጽ/ቤታቸው አቀባበል አደረጉ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የረጅም ዘመናት ታሪክ አለው ብለዋል።

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ሂደት ዘመናትን የተሻገረ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በአድዋ ታሪክ ወጣቶች እና ሴቶች ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።

ሴቶች ቀለብ ማዘጋጀት ወጣቶች ደግሞ በአርበኝነት ሀገርን የማዳን ትግል ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

ወጣቶች ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ በማድረግ በሀገር እድገት ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

ወጣቶች ለህዝቦች አንድነት እና ትስስር በጋራ መስራት እንዳለባቸው የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጉዞ ማጠናከር ይጠበቃል ሲሉም አብራርተዋል።

ክልሉ በአጭር ጊዜ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባ ወዲህ በርካታ አብነታዊ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ስራ ማስጀመር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት በስድስት ወራት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እያደገ ስለመምጣቱም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ በበኩላቸው "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ "እየተካሄ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በህዝቦች መካከል ጠንካራ አንድነት እና ትስስር ይፈጥራል ብለዋል።

የዘንድሮውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልዩ የሚያደርገው ኢትዮጵያ በልማት፣በሰላም በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በላቀ ከፍታ ለመሻገር በምታደርገው ማዕቀፍ ውስጥ በሆነችበት ጊዜ መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ወጣቶችን በማቀናጀት አካባቢን ከመቀየር ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ወዳጅነትን እንደሚያጠናክር ኃላፊው አስታውቀዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ወጣቶች ድንበር ተሻግረው እንዲሰሩ ማድረግ በመቻሉ የወጣቶችን አቅም ከማሳደጉም ባሻገር አህጉራዊ አንድነትና ትስስር እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።

ወጣቶች ከተለያዩ የአለም አቀፍ ክፍሎች ተንቀሳቅሰው በማህበረሰብ ልማት በአካባቢ ጥበቃ እና በትምህርት ዘርፍ አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች ጉዳይ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽነር ማርቆስ ማቲዎስ እንደገለጹት በክልሉ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል ።

የክልሉ መንግስት ወደ ቀድሞ ቤታችን ሲልከን በደም የተጋመደ አንድነታችንን ይበልጥ እንድናጠናክር ነው ብለዋል።

ከወንድሞቻችን ጋር በደም ልገሳ፣ማዕድ ማጋራት ችግኝ ተከላ እና በሌሎችም የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ወጣቶቻችንን ሀብት ከማዳን ባለፈ ለወገኖቻችን በነጻ የምንሰጠው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትን በማጠናከር ረገድ የጎላ አበርክቶ አለው ብለዋል።

የክልሉ ወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ እንደገለጸው በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በማጠናከር በሁሉም ዘርፍ የላቀ ውጤት ተመዝግቧል ብሏል።

በክልሉ ለተመዘገበው የላቀ ውጤት የአመራር ቁርጠኝነት እና የስራ ባህል ለውጥ መሆኑን ወጣት አብዱ አስረድቷል።

"በዕውቀት በዳበሩና በአስተሳሰብ በበለጸጉ መዛኞቻችን ትጋት የዜጎችን የሙያ ብቃት በመመዘን፤ ለሥራ ገበያው ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን እናፈራለን።"               ክቡር አቶ ራመቶ ...
02/09/2026

"በዕውቀት በዳበሩና በአስተሳሰብ በበለጸጉ መዛኞቻችን ትጋት የዜጎችን የሙያ ብቃት በመመዘን፤ ለሥራ ገበያው ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን እናፈራለን።"

ክቡር አቶ ራመቶ ቦካ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር

የጤናው ሴክተር በክልሉ የልማት ስትራቴጂ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ነው:- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ "ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት" በ...
01/09/2026

የጤናው ሴክተር በክልሉ የልማት ስትራቴጂ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ነው:- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ

"ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ሀሳብ በወልቂጤ ከተማ የጤና ሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለጹት ጤና የእድገታችን ፣የብልጽግናችን እና የማህበራዊ እድገታችን መሰረት ነው ብለዋል።

ጤናማ ህብረተሰብ መገንባት የጠንካራ ኢኮኖሚ፣ጥራት ያለው ትምህርት፣የተረጋጋ ማህበራዊ ህይወት ፣ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሁም ጠንካራ ሀገር መፍጠር ያስችላል ሲሉም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

የጤናው ሴክተር በክልሉ የልማት ስትራቴጂ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ተቋም ስለመሆኑም አቶ አንተነህ ጠቁመዋል።

በጉባኤው ባለፈው አመት የታዩ መልካም ልምዶችን ለማስቀጠል፣በአፈጻጸም ረገድ የተስተዋሉ ውስንነቶችን ለማረም እና ቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ አቅጣጫ ማስቀመጥ የሚያስችል መድረክ መሆኑን አመላክተዋል።

በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት የጤና ተቋማትን ተደራሽነት እና የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የእናቶችን እና የህጻናትን ሞት ለመቀነስ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

በዘርፉ የተመዘገበው ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው፣ ህብረተሰቡ የራሱን ጤና መጠበቅ እንዲችል የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ላይ ትኩረት መደረጉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።

በተለይም የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ በማድረግ ለህብረተሰቡ በቅርበት አገልግሎት እየተሰጠ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

በዚህም ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር አቅም ለማሳደግ፣የህክምና ግብአቶችን እና መድሀኒቶችን ለማረጋገጥ ጥረት መደረጉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በክልሉ በጤና አገልግሎት ዘርፉ የህብረተሰቡን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማሟላት አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው በሀገሪቱ በጤናው ሴክተር በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በጤናው መስክ በመከላከል እና በህክምና ረገድ በተከናወኑ ስራዎች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደገለጹት ክልሉ በይፋ ተመስርቶ ስራ ከጀመረ ወዲህ በጤናው ዘርፍ የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ የቅድመ ዝግጅት ስራ በማጠናቀቅ የጤናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ በንቅናቄ መምራት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ወደ ተግባር መገባቱን አመላክተዋል።

በንቅናቄው ጤና ኬላዎች፣ጤና ጣቢያዎች ሆስፒታሎች በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮች በባለቤትነት ዘርፉን የማይመሩበት አሰራር እንደነበር አቶ ሳሙኤል አስታውሰዋል።

በተለይ በጤና ኬላዎች የሚሰጠው አገልግሎት ከ25 በመቶ በላይ እንዳልነበርም ጠቅሰዋል።

በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር በጥናት በመለየት የንቅናቄ ስራው መጀመሩን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በክልሉ በ2018 በጀት አመት በጤናው ዘርፍ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ስለመቻሉም አቶ ሳሙኤል አብራርተዋል።

በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን፣በበሽታዎች ወረርሽኝ፣በጤና ኤክስቴንሽን እና በሌሎችም መስኮች የተጠናከረ የንቅናቄ ስራ ተግባራዊ መደረጉን ኃላፊው ተናግረዋል።

በጤናው ዘርፍ በሚያጋጥሙ ህገወጥ አሰራሮች ላይ የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ ተግባራዊ መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው በተለይ የግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማት በባለቤትነት እንዲሰራ መደረጉን አስታውሰዋል።

Address

Central Ethiopia Region
Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Regional state OCAA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share