27/08/2026
ከሐምሌ 1/2018 እስከ ነሐሴ 21/2018
➚ መደበኛ = 66,968,115.44
➚ አገ/ት = 17,345,451.84 በድምሩ 84,313,567.28 ተሰበሰበ ለምን ካላችሁ ይኸው ስታድየሙ ዙሪያ በከፈልነው ግብር የሚሠሩ መንገዶች፣ የጎርፍ ማፋሰሻዎች ወዘተ ልማቶች ሲሠሩ ማየት እንዴት ደስ ይላል፣ ስለዚህ ግብር ለሀገር ክብር ማለት ይህ ነው። ስለዚህ የደረጃ "ለ" ፣ የአከራይ ተከራይ፣ የወፍጮና የተሽከርካሪ ግብር ከፋዮቻችን ABoR የሚል ቴክስት ከመጣላችሁ እሱ የምትከፍሉት ግብር ስለሆነ ከፍታችሁ በማየት እስከ ነሐሴ 30/2018 ከፍላችሁ አጠናቁ። በተጨማሪም በከተማችን የምትገኙ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ግብይታችሁን በደረሰኝ እንድታከናውኑ አደራ፣ አደራ አዲስ የወጣው የታክስ አስተዳድር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ደረሰኝ አሳትሞ እየሠራ ያለ ግብር ከፋይ ደረሰኝ ሳይሰጥ ሽያጭ ሲያከናውን ከተገኘ ደረሰኝ ባልቆረጠበት እያንዳንዱ ግብይት 100ሺህ ብር አንዲቀጣ በሚል ወጥቷል። ስለዚህ ደረሰኝ መስጠት ስልጡንነት ነው የሚለውን እንተግብረው።
የፍ/ሠላም ከተማ አስ/ገቢዎች ጽ/ቤት