West Gojjam Zone Prosperity

West Gojjam Zone Prosperity Political Party

አመራሩ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በመገንዘብ ለሠላምና ልማት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ።በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት “ውጫዊ የወረራ ስ...
18/08/2026

አመራሩ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በመገንዘብ ለሠላምና ልማት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት “ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የጽንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሠላምና ልማት እናረጋግጣለን።” በሚል መሪ ሃሳብ ከከተማ አስተዳደሩ ጠቅላላ አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የቡሬ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አንማው ብዙዓየሁ የውይይቱን መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በአቀራረባቸውም የጽንፈኝነትና የጥፋት ኃይሎችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍ፣ የሠላም ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አመራሩ በአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በቅድሚያ በመለየትና በመገንዘብ የሠላም ጥበቃን ከልማት ሥራዎች ጋር በማስተሳሰር በንቃትና በቁርጠኝነት መሳተፍ እንዳለበትም ገልፀዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ አመራሮች በበኩላቸው፣ ማህበረሰቡ የጽንፈኝነትን አስተሳሰብና ድርጊት በመቃወም ሠላምን ለማስፋት እያደረገ ያለው ተሳትፎ እየጎለበተ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ሕግን የማስከበር ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንስተዋል።

ተሳታፊዎቹ አክለውም፣ ሁለንተናዊ የህብረተሰብ ተሳትፎንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሠላምን ማስጠበቅ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን በመግለፅ ሠላም ሲረጋገጥ የልማት ሥራዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ መከናወንና ማህበረሰቡም ከልማቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

አመራሩ የሠላም ጥበቃን በተቀናጀ መልኩ በማጠናከር፣ የጽንፈኝነትንና የጥፋት አስተሳሰቦችን በመቃወም እንዲሁም ማህበረሰቡን በማሳተፍ ለዘላቂ ሠላምና ልማት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አፅንዖት ተሰጥቷል።

West Gojjam Zone Prosperity

የጽንፈኛውን አፍራሽ ቅስቀሳና የባዕዳንን ጦርነት ጉሰማ ለማምከን የተደራጀና የተቀናጀ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራ ማከናወን እንደሚገባ ተገለጸ።በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብል...
18/08/2026

የጽንፈኛውን አፍራሽ ቅስቀሳና የባዕዳንን ጦርነት ጉሰማ ለማምከን የተደራጀና የተቀናጀ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራ ማከናወን እንደሚገባ ተገለጸ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳው አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱ የተገኙት የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ተሻገር የውስጥ ባንዳና የውጭ ባዕዳንን የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ በትጋት መስራት ይገባል።

አገልግሎት አሰጣጥ ከችግር የወጣ መልካም አስተዳደር ለማስፈን መስራት ይገባል።እውነተኛ ሰላምና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡን ተሳታፊና የመፍትሄ ባለቤት ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይዘንጋው ብርሄ እንዳሉት የጽንፈኛውን አፍራሽ ቅስቀሳና የባዕዳንን ጦርነት ጉሰማ ለማምከን የተደራጀና የተቀናጀ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራ ማከናወን ይገባል ብለዋል።

አመራሩ የውስጥ ባንዳና የውጭ ባዕዳንን የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ በትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።

ለችግር የማይበገር ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዩን የተገነዘበ መሪ ሊኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በጽንፈኛው ቡድን ላይ እርምጃ ተወሰደ። ​በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በልዩ ስሙ ኪዳነምህረት ፣ ማሻ እና አከባቢው ሕዝብን ሲያስጨንቅና ሰላም ሲያደፈርስ የነበ...
18/08/2026

በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በጽንፈኛው ቡድን ላይ እርምጃ ተወሰደ።

​በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በልዩ ስሙ ኪዳነምህረት ፣ ማሻ እና አከባቢው ሕዝብን ሲያስጨንቅና ሰላም ሲያደፈርስ የነበረው የጽንፈኛው ቡድን ላይ እርምጃ መወሰዱን በ11ኛ ዕዝ ክፍለ ጦሮች አሥታወቁ።

ክፍለጦሮች በተሰማሩበት የግዳጅ ቀጠና በተቀናጀ መንገድ በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ፣ የፅንፈኛው ቡድን አባላት በርካቶች ተደምስሰዋል፤ ቆስለዋል።

​የኮሩ አዛዥ ኮሎኔል ገዳ በዳዳ እንደገለጹት፤ ክፍለ ጦሮቹ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ቡድኑ ታጥቋቸው የነበሩ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ ተተኳሽ ጥይቶች፣ ወታደራዊ መገናኛ ሬዲዮኖች እና ወታደራዊ መነፀሮች ተማርከዋል።

በህግ ማስከበር ግዳጅ ላይ የሚገኙት ክፍለ ጦር አዛዦች፣ በጽንፈኛው ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሕዝብን ሰላም የማረጋገጥ ቁልፍ ምዕራፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሰላም አማራጭን የማይቀበሉ ተላላኪዎችን ሠራዊቱ እግር በእግር እየተከተለ መምታቱን ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የኮሩ አዛዥ ገልፀዋል። ዘገባው የኮሩ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ነው።

በፅኑ ህዝባዊ ደጀንነትና አንድነት የጠላቶቻችንን ሴራ በማክሸፍ ለዘላቂ ሠላምና ልማት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አስተዳደር "ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ዉስጣ...
18/08/2026

በፅኑ ህዝባዊ ደጀንነትና አንድነት የጠላቶቻችንን ሴራ በማክሸፍ ለዘላቂ ሠላምና ልማት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አስተዳደር "ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ዉስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሠላምና ልማትን እናረጋግጣለን !!" በሚል መሪ ሀሳብ ከ ጠቅላላ አመራሩ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የምክክር መድረክ አካሄደ።

መድረኩ የሀገራችንና የክልላችን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የውስጥ የጽንፈኛውንና የህወሓት የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ አመራሩ ወቅታዊ ሁኔታውን በመገንዘብ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል ነው።

አመራሩ በየደረጃው ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የውጭና የውስጥ ወረራና ፅንፈኝነትን በመጋፈጥ ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማምጣት ኃላፊነቱን በግንባር ቀደምትነት ሊወጣ እንደሚገባ በውይይቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ በፅኑ ህዝባዊ ደጀንነትና አንድነት የጠላቶቻችንን ሴራ በማክሸፍ ለዘላቂ ሠላም እና ልማት መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

በውይይት መድረኩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮንስትራክሽን ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጋሹ የሰከላ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ አዳነ፣ የሰከላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲያቆን አሻግሬ ጌታነህ እና ጠቅላላ የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል።

ሀገራዊ እና ክልላዊ ሰላም እና ልማት ለማስቀጠል ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በጋራ መቆም እንደሚገባ ተገለጸ።በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር "የውጫዊና የውስጣዊ ፅንፈኝነት አ...
18/08/2026

ሀገራዊ እና ክልላዊ ሰላም እና ልማት ለማስቀጠል ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በጋራ መቆም እንደሚገባ ተገለጸ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር "የውጫዊና የውስጣዊ ፅንፈኝነት አስተሳሰብን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል ከከተማና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ማስተዋል ደሴ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የሰላምና ጸጥታ አስመልክቶ የማህበረሰቡን የግንዛቤ ደረጃ ለማሳደግና የህዝቡን ተሳትፎ ለማጠናከር የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባል ብለዋል።

አመራሩም ፅንፈኝነትንና የጥፋት አጀንዳዎችን በመመከት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለበት አሳስበዋል።

ሀገራዊ እና ክልላዊ ሰላም እና ልማት ለማስቀጠል ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በጋራ መቆም እንደሚገባ ተገልጿል።

በመድረኩ የፅንፈኝነት አስተሳሰብን በመቀልበስና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንዲሁም ወደ ልማት ስራዎች መግባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ሞላ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፤ በአካባቢው ሲስተዋል የነበረው ግጭት በማህበረሰቡ ላይ ያደረሰውን ሰብዓዊ፣ ማህበራዊና ቁሳዊ ጉዳት ዳሰዋል። ይህንን የጥፋት አዙሪት በመቀልበስ ረገድ የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ማፋጠን፣ የሰራ እድል ፈጠራን ማስፋፋትና የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፤ ህግን በማክበር፣ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመታገል፣ የህዝብ ጥያቄዎችን በወቅቱ በመመለስና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን በተቋማት አጠናክሮ በመዘርጋት የህዝብን የመንግሥት እምነት መገንባት ይገባል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮችም በየዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ በመለየትና በመመካከር ተግባራዊ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የከተማዋን ሰላም በጋራ በመጠበቅ፣ ልማትን በማፋጠንና መልካም አስተዳደርን በማረጋገጥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት
ሁሉም በባለቤትነት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎የሀገርን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ አመራሩ የሚጠበቅበትንሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ።‎በምዕራብ ጎጃም ዞን በደምበጫ ከተማ አስተዳደር "ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የጽንፈኝነት አደጋ...
18/08/2026

‎የሀገርን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ አመራሩ የሚጠበቅበትን
ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ።

‎በምዕራብ ጎጃም ዞን በደምበጫ ከተማ አስተዳደር "ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የጽንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን"በሚል መሪ ቃል ከከተማ አስተዳደሩ አመራሩ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

​በውይይቱ ላይ የፅንፈኝነትንና የጥፋት ኃይሎችን እኩይ አላማ በማክሸፍ የሀገርን ብሎም የከተማ አስተዳደሩን ሰላም መጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።

የውስጥ ጽንፈኛና የውጭ ጠላቶች ሴራ ለማክሸፍ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የድርሻዉን ለመወጣት አካባቢውን መጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።

​ በክልና በሀገር ደረጃ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተረድተን በመደማመጥ የተጋረጡብንን የውስጥና የውጭ የጠላት አጀንዳዎች በማምከን ሰላምን በማስፈን ብልጽግናን ለማረጋገጥ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

‎በመድረኩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከተማ መሰረተ ልማት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሙሉጌታን ጨምሮ ሁሉም የደምበጫ ከተማና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል።

West Gojjam Zone Prosperity

በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ዙሪያ ወረዳ በወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ከአለፋ ባሲ ቀበሌ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።‎በውይይት መድረኩ ላይ የተ...
18/08/2026

በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ዙሪያ ወረዳ በወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ከአለፋ ባሲ ቀበሌ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ በላቸው መንግሥቴ እንደገለፁት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና በቀበሌው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ስኬታማነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የቀበሌው ማኅበረሰብ ውስጣዊ ፅንፈኝነት በመከላከል ለዘላቂ ሰላምና ልማት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩልም ባለፉት ሦስት አመታት በትምህርት ዘርፍ የገጠሙ ችግሮችን ለማህበረሰቡ ያብራሩት ሃላፊው በትምህርት ዘመኑ ችግሩን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ወላጆች ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየትም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከመንግስት ጎን በመሠለፍ በልዩ ትኩረት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ሁሉም ለሰላም🕊

አመራሩ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በመገንዘብ ለሰላም ጥበቃና ለልማት ስራዎች በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ  ቅርንጫፍ ጽ/ቤ...
18/08/2026

አመራሩ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በመገንዘብ ለሰላም ጥበቃና ለልማት ስራዎች በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳው አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

​በውይይቱ ላይ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይዘንጋው ብርሄ እንዳሉት የፅንፈኝነትንና የጥፋት ኃይሎችን እኩይ አላማ በማክሸፍ ሰላም መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ ይዘንጋው ለመድረኩ ውይይት አመራሩ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በመገንዘብ ለሰላም ጥበቃና ለልማት ስራዎች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።አመራሩ ውጫዊና ውስጣዊ አደጋዎችን በመገንዘብ ለሰላም ጥበቃና ለልማት ስራዎች በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

ማህበረሰቡ የጽንፈኝነት አስተሳሰብ ድርጊት እያወገዘ ነው፤ሰላምን ለማስፋት ተባባሪ እየሆነ ነው ብለዋል።የጠላት እንቅስቃሴና የሰው ሀይል በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስና እንዲበታተን ተደርጓል፤ለዚህም ህግ የማስከበር ስራ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ለሰላም መቆም መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

የሀገራችን ሁለተናዊ ጉዞ ለማደናቀፍ የሚጥሩ የጥፋት ሀይሎች የሚያሴሩትን ነባራዊ ሁኔታ በውል መረዳት ያስፈልጋል ነው ያሉት አቶ ይዘንጋው።

West Gojjam Zone Prosperity

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቋሪት ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳይ  ከወረዳ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው።ውይይቱ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በክልላችን ስር የሰ...
18/08/2026

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቋሪት ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳይ ከወረዳ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው።

ውይይቱ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በክልላችን ስር የሰደዱ ችግሮችን ለመፍታት የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ እነተደረገ ያለውን ጥረት የሚዳስስ ነው።

ባለፉት የለውጥ አመታት ጉዞ እንደ ክልል ሆነ እንደ ሀገር አያሌ ፈተናዎች ቢገጥሙም በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ተጠቁሟል።

በፖለቲካ ሪፎርሙ የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት፣ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ ሰላማዊ ትግሉ በማምጣት ሰፊ ስኬቶች መመዝገብ መቻሉንም በውይይቱ ተነስቷል።

በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልላችን ተከስቶ የቆየው ቀውስ አንጻራዊ በሆነ መልኩ እየተሸሻለ በመምጣቱ የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄ የመመለስና ልማትን የማረጋገጥ መልካም ጅማሮ እየታየ መሆኑንም ተገልጿል።

West Gojjam Zone Prosperity

18/08/2026

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው

ሀገራችን የተሻለ ሆና እንድትቀጥልና ለነገው ትውልድ የምትመች ሀገር ለመገንባት እየተካሄደ ያለው ምክክር ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

ከተመካካሪዎች አንደበት



~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

Address

Finote Selam

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Gojjam Zone Prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share