23/04/2026
የምዕ/ጎጃም ዞን እንስሳትና ዓሳ ሀብት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።
በዞኑ ውሰጥ ባሉት በሰባት የገጠር የወረዳዎችና በሁለት የከተማ አሰተዳድሮች አስፈፃሚ አባላትን ወይም ማኔጅመንት ቡድኑን በማካተት 9ወር የአፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።
በግመገማ ሂደቱ እስካሁን በበጀት ዓመቱ በእንስሳት አርባታ እና በእንስሳት ጤና የተፈፀሙ ተግባራትን በመያዝ በመፈፀምና ባለመፈፀም ያሉበትን ቁመና በማሳዬት በቀጣይ የአፈፃፀም ልዩነትን የማጥበብ ሥራ መሥራትና ቀሪ ተግባራትን በመለዬት በያዝነው ሩብ ዓመት መጣናቀቅ እንዳለባቸውና ትኩረት እንዲሰጥባቸው ጭምር ተደረጓል።