የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Gambela
  • የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Government Organization

መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል።ነሐሴ 28/2018 ዓ.ምመንግሥት አገራዊ ሪፎርሞችን በመተግበር የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ...
03/09/2026

መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል።

ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

መንግሥት አገራዊ ሪፎርሞችን በመተግበር የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገባውን ቃል ወደ ተግባር እየለወጠ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥና የዜጎቿን ሕይወት ከፍ ለማድረግ በምታደርገው ያልተቋረጠ ርብርብ፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያበስሩ ታሪካዊ ምዕራፎች እውን እየሆኑ ይገኛሉ።

መንግሥት ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስልታዊ ፖሊሲዎችን በመንደፍና በመተግበር በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

በክቡር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት የዚህ አበይት ርዕይ አንዱ ማሳያ ነው።

በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የሚቋቋመውና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ያካተተው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ፣ በባንክ ዘርፍ ያለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን በመቅረፍ ለዜጎች አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ይፈጥራል።

ይህ ታሪካዊ ስምምነት መንግሥት በተመጣጣኝ ዋጋ የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ ያስቀመጠውን ግብ በግንባር ቀደምትነት የሚያሳካ ነው።

ስምምነቱ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ፍላጎት እውን በማድረግ ረገድ የሚታዩ ማነቆዎችን በመስበር፣ የበርካቶችን የዕለት ተዕለት ሕይወትና ማኅበራዊ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያሻሽል የመንግሥት ቁርጠኝነትን ያረጋገጠ ቁልፍ እርምጃ ነው።

ይህ ስኬት ብቻውን የቆመ አይደለም፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሜጋ ፕሮጀክቶች የተመዘገቡት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ድሎች ቀጣይ ምዕራፍ አካል ነው።

የመደመር መንግሥት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በስፋት በማካተትና የገበያ ሥርዓቱን በማዘመን አገራዊ የኢኮኖሚ አቅምን ማጠናከር የልማት ጉዞው መሠረት አድርጎ ቀጥሏል።

እንደ ሀገር እየተመዘገበ ካለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የዋጋ ግሽበት አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሰውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ መንግሥት በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት በመመደብ በነዳጅ፣ በመሠረታዊ ፍጆታዎች እና በግብርና ግብአቶች ላይ ከፍተኛ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።

ከዚህ የዕለት ኑሮ ማቃለያ ሥራ ባሻገር የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ማሻሻልና ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎል። በዚህም ቃል በተግባር እየተለወጠ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ የመገንባት ጽኑ ፍላጎቱ በሁሉም መስክ በተግባር እየተፈጸመ ቀጥሏል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ +++++++++++++ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ...
03/09/2026

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
+++++++++++++

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑ የደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተገልጻል።

ኢንስቲትዩቱ ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

በመጪዎቹ አሥር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የጠቆመው ኢንስቲትዩቱ፤ በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አመላክቷል።

በወሩ የመጨረሻ ሳምንት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች እየተዳከሙ እንደሚመጡ በመግለጽ፤ አብዛኞቹ የሰሜን ምሥራቅ፣ መካከለኛውና ምሥራቅ አካባቢዎች በበጋው ደረቅ የአየር ጠባይ ተፅዕኖ ሥር መሆን እንደሚጀምሩ ተጠቅሷል።

በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ምዕራባዊ አጋማሽ ላይ የክረምቱ ዝናብ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥልም መግለጫው ያመላክታል።

የምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ የሶማሌ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ ክፍል፣ ከኦሮሚያ ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምሥራቅ ባሌ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የሲዳማና የአፋር ደቡባዊ ክፍል ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኦሮሚያ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምሥራቅ ቦረና ዞኖች፣ እንዲሁም የደቡብ ሶማሌ አካባቢዎች ከወሩ አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።



የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ -ምግባር ለማሻሻል እንዲሁም ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የትምህርት ዘርፉን በቅንጅት መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ...
03/09/2026

የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ -ምግባር ለማሻሻል እንዲሁም ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የትምህርት ዘርፉን በቅንጅት መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ።

የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ-ምግባር ለመሻሻል ከሜጢ ከተማ እና ከጎደሬ ወረዳ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ጋር የ2019 የትምህርት ዘመን የንቅናቄ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ብቁ፣ አዋቂ እና ተወዳዳሪ ዜጋ በመቅረጽ ረገድ የትምህርት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የትምህርት ዘርፉን በባለቤትነት ስሜትና በቅንጅት መደገፍ ይገባል ተብሏል

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ህጻናትን ለተሻለ እውቀት ለማብቃት ከወዲሁ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ፣ ትምህርት ቤቶችን የማፅዳት እና ለመማር ማስተማሩ ስራ ምቹ ሁኔታን መፈጠር እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል።

በተለይም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መላክ የመንግሥት አካላት ብቻ ሳይሆኑ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ኃላፊነት መሆኑንም አፅንኦት ተሰጥቶበታል።

የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ኤትሰን ጀመኮይ እንደተናገሩት ትምህርት የነገን ትውልድ አሻጋሪ የልማት ምሰሶ መሆኑን ገልጸው፣ የትምህርት ቤቶችን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማስቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተናበበ እና የተጠናከረ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሜጢ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ናሆም ይማም እና የጎደሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ ክብረት እንዳስታወቁት የነገ ሀገር ተረካቢዎችን በስነ-ምግባር እና በዕውቀት ታንጸው እንዲወጡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የፓርቲው መዋቅር እና አመራር ሁልጊዜም ከጎን እንደሚሰለፍ ገልጸው፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ማህበራዊ አጠቃላይ ንቅናቄዎች ላይ ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አመራሮች እና የትምህርት ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ከማሻሻል አንጻር የሚደረጉ ስራዎችን በባለቤትነት ስሜት እንደሚደግፉ ገልጸው፤ የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተናበበና ጠንካራ ርብርብ ለማድረግ ያላቸውን ጽኑ ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም አዲሱ የትምህርት ዘመን የተሳካ እንዲሆን እና ህብረተሰቡ ለልጆቹ ትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ ቀርቧል።

03/09/2026
በዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ምደባ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ሊዘረጋ ነውበዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች ምደባና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት...
03/09/2026

በዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ምደባ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ሊዘረጋ ነው

በዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች ምደባና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ዩኒቨርሲቲዎች የሙያና የሥነ ምግባር እሴቶች የሚገነቡባቸው የአካዳሚክና የምርምር ተቋማት ናቸው፡፡

የሕብረተሰቡ የሞራልና የእውቀት መሪዎች በመሆናቸው የሙያ ሥነ ምግባርንና የሞራል እሴቶችን በመላበስ ማህበረሰቡን በእውቀትና በሙያ ሊደግፉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስብጥር ብዝሃነትን ባካተተ፣ መተዋወቅን፣ መከባበርን፣ መቻቻልንና ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች ምደባና ዝውውር ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ሥርዓት እንደሚዘረጋ ገልጸዋል።

ከበጀት አጠቃቀም ረገድም ተቋማቱ የተመደበላቸውን በጀት ለታቀደለት ዓላማ ብቻ በቁጠባና በተጠያቂነት መንፈስ ማዋል እንዳለባቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ዩኒቨርሲቲዎች ሀገርን የሚያሻግሩ የእውቀት ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚገባ አጽንኦት መስጠታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሜጢ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።የሜጢ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ...
03/09/2026

የሜጢ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።

የሜጢ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ዙሪያ የመፍትሔ ሀሳቦችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ሰፊ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በዚህ የውይይትና የንቅናቄ መድረክ ላይ የቀበሌ ሊቀመንበሮች፣ የትምህርት ወላጅ መምህር ህብረት የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በውይይቱ እንደተገለፀው ባለፉት ተከታታይ ሦስት ዓመታት ውጤት ማስመዝገብና የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ማሳደግ ያልቻሉ ፣ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ ባልተወጡ ርዕሰ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ከቦታ የማንሳትና የማሸጋሸግ ስር መሰራቱ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል የ2018 የትምህርት ዘመን የፈተና ውጤት አፈጻጸም የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቧል።

በቀረበው ሪፖርት መሰረት ባለፈው የትምህርት ዘመን በተማሪዎች ውጤት ላይ ማሽቆልቆል መታየታቸው እና ለውጤቱ ማሽቆልቆል የተማሪዎችና የወላጆች ተሳትፎ ማነስ፣ ተማሪዎች ኬኖ ቤት መዋል እና በሜጢ ከተማ ቁማር ቤቶች መስፋፋት ፣ ተማሪዎች ስልክ ላይ ብቻ ማተኮር፣ የመምህራ ዝግጅት ማነስ እና የክትትል ክፍተቶች ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸው በጥናት ተመላክቷል።

የውይይቱን መድረክ የመሩት የሜጢ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ተረፈ እና የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘሪሁን በልሁ እንደተናገሩት በባለፈው ዓመት የታየው የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካል ከወዲሁ የተናበበና ጠንካራ ርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረቡትን ችግሮች አቅጣጫ ባስቀመጠ መልኩ የመፍትሔ ሀሳቦች ሰንዝረዋል።

በመሆኑም በቀጣይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ወላጆች ከትምህርት ቤቶች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር እንዳለባቸው፣ መምህራን ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በላቀ ቁርጠኝነት ሊወጡ እንደሚገባ፣ እንዲሁም የቀበሌ አስተዳደሮችና የህብረተሰቡ ክፍሎች ለትምህርት ቤቶች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ተስማምተዋል።

በጋምቤላ ክልል ከተረጅነት ለመላቀቅ በሚሰራው ስራ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት ከተረጅነት ለመላቀቅ የተሰራው ስራ  በሰብዓዊ ድጋፍ ሀብት ማሰ...
03/09/2026

በጋምቤላ ክልል ከተረጅነት ለመላቀቅ በሚሰራው ስራ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት ከተረጅነት ለመላቀቅ የተሰራው ስራ በሰብዓዊ ድጋፍ ሀብት ማሰባሰብ ዙሪያ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ተካሂዷል።

በዉይይቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸኒ አስቲንና የክልሉና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በመስኖና በዉሃ ሸሸ ዙሪያ፣ በሰባዊ ድጋፍ ሀብት ማሰባሰብ ዙሪያ የመወዪያ ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በዉይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት ህብረተሰቡን ከተረጅነት ለማላቀቅ ተረጅዉ አካል ማን ነዉ፣ ከየትኛዉ ቀበሌ ነዉ የሚለዉን የመለየት ስራ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ህዝቡ የተረጅነት አስተሳሰብን በማስወገድ በራሱ አቅም የራሱን ገቢ መፍጠር እንዲችል ግንዛቤ በመፍጠርና ወደ ስራ እንዲገባ በማድረግ በኩል አመራሩ ሚናዉን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዘበዋል።

በክልሉ ባሉት የተፈጥሮ ሀብቶችላይ፣ በዉሃ ሸሽና በመስኖ ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ ከተሰራና ህዝቡ እርዳታ የሚለዉን አስተሳሰብ ከአይምሮዉ ካወጣ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከተረጅነት ማላቀቅ ይቻላል ብለዋል።

ተቋማት የተጣለባቸዉን የአይነትም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ በአግባቡ በመሰብሰብ ለታለመለት አላማ እንዲዉል በማድረግ በኩል የበኩላቸዉን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት እንደ ሀገር ኢትዮጵያ ክብሯን የምታስጠብቅበት ፕሮግራም ተነድፎ ከተረጅነት ለመላቀቅ በራስ አቅም ሀብት ማሰባሰብና ምርታማነት ላይ ትኩረት ተደርጎ የንቅናቄ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ከተረጅነት ለመላቀቅ በመስኖና በዉሃ ሸሽ ላይ ጊዜ ሳይሰጠዉ ወደታች ወርዶ ለመስራት የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አቶ አሸኔ አክለዉም ከተረጅነት ለመላቀቅ የተሰሩ ስራዎችን በአግባቡ ለመሰብሰብ ቅንጅታዊ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ሀብት በመሰብሰብ በቀጥታ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ተረጂዎች በመለየት ለቀጣይ ማሸጋገር በሚቻልበት ደረጃ ሊደገፉ ይገባልም ብለዋል።

ተቋማት የተጣለባቸዉን የገንዘብ ድጋፍ ከስራቸው የሚገኙ ባለሞያዎች በማስተባበር በተባለበት ጊዜ የሚፈለገዉን የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

በውይይቱ ላይ ከተለያዩ ሴክተር ቢሮዎች የተወጣጡ አብይ ኮሚቴና ቴክኒክ ኮሚቴ ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።

#ጋምቤላ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን

የማጃንግ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በሜጢ ከተማ የተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።የማጃንግ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በዞኑ የሚገኙ የ...
03/09/2026

የማጃንግ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በሜጢ ከተማ የተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

የማጃንግ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በዞኑ የሚገኙ የሞተር ሳይክል፣ የባጃጅ እና የቅጥቅጥ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ቶማስ የማሎ በቦታው ተገኝተው እንደተናገሩት ምርመራው የትራንስፖርት አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል፣ የተሽከርካሪዎችን ቴክኒካዊ ብቃት ለማረጋገጥ እና ለተጠቃሚዎች አስተማማኝ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አሸብር ለገሰ በበኩላቸው በዞኑ የሚገኙ የሞተር ሳይክል፣ የባጃጅ እና የቅጥቅጥ ተሽከርካሪ ባለቤቶቸና አሽከርካሪዎች ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በፊት ሜጢ ከተማ ስታዲዮም በመገኘት አስፈላጊውን ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀላፊው አክለው እንደገለፁት ከተጠቀሰው ጊዜ ውጭ የሚገኙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑንም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ የብዝሃ ብሔረሰቦች፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶች እና ባህሎች ሀገር እንደ መሆኗ መጠን፣ የብሔረሰቦችን መብቶችና ነፃነቶች በሕገ-መንግሥቱ አረጋግጣለች።የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን መንግስት ኮም...
03/09/2026

ኢትዮጵያ የብዝሃ ብሔረሰቦች፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶች እና ባህሎች ሀገር እንደ መሆኗ መጠን፣ የብሔረሰቦችን መብቶችና ነፃነቶች በሕገ-መንግሥቱ አረጋግጣለች።

የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት (ነሃሴ 28/2018 ዓ/ም)

የለውጡ መንግሥት የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት፣ እያንዳንዱ ብሔረሰብ ቋንቋውን እንዲጠቀም፣ ባህሉን እንዲያዳብር እና በሀገር አስተዳደር ውስጥ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲኖረው በርካታ ተግባራትን አከናውኗል።

ከእነዚህም መካከል አንዱ የሆነው የማጃንግ ብሔረሰብ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በንቃት በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

የብሔረሰቡን አብሮነትና ወንድማማችነት ይበልጥ ለማጠናከር ከምሁራን እና ከባህል አባቶች ጋር በመመካከር፣ በ2018 ዓ.ም በቴፒ ከተማ በተካሄደው ሲምፖዚየም፣ የማጃንግ አዲስ ዓመት መለወጫ በዓል «ዴንከ» (Deŋke) ተብሎ እንዲጠራና በየዓመቱ በጥር ወር የመጀመሪያ ሳምንት እንዲከበር ተወስኗል።

ይህንን ታሪካዊ በዓል በድምቀት ለማክበር እና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ለማዘጋጀት፣ የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን፣ የወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ትሁት ሐዋርያት በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የዴንከ በዓል መከበር የብሔረሰባችንን ማንነት፣ ታሪክ እና ባህላዊ እሴቶች ከማዳበር ባለፈ፣ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር ያለንን ማህበራዊ ትስስርና አብሮነት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ ሁሉም አካል በባለቤትነት መንፈስ ተቀናጅቶ ሊሰራ ይገባል» ብለዋል።

በዓሉ ለአካባቢ ሰላም፣ ለልማት፣ ለባህላዊ እሴቶች ዕድገት እና ከጎረቤት ሕዝቦች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ፣ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር በስኬት እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።

Address

Metti
Gambela

Telephone

+251973738532

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share