Jor Woreda Press Secretariat Office

Jor Woreda Press Secretariat Office Jor Wored is found Gambella Ethiopia

09/03/2024
09/03/2024
09/03/2024
የጆር ወረዳ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ተጀመረ*******************ከጆር ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (የካቲት 30/2016 ዓ.ም)በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን ...
09/03/2024

የጆር ወረዳ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ተጀመረ*******************

ከጆር ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (የካቲት 30/2016 ዓ.ም)

በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን ፤የጆር ወረዳ ምክር ቤት 5ተኛ ዙር የምርጫ ጊዜ 11ኛ የስራ ዘመን 27ተኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ተጀምሯል ::

የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ፤ኡዶል ኡማን ኡምድ፤ጉባኤውን በይፋ ሲከፍቱ እንዳሉት፣ የወረዳው ምክር ቤት አባላት ለመልካም አስተዳደር፣ ልማት፣ ፍትህ መረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በትጋት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የምክር ቤት አባላት የወረዳውን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ሆነው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባና የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሁሉም አካላት ተቀናጅተው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸውም አፈ ጉባኤዋ ጥሪ አቅርበዋል።

ጉባኤው በሚኖረው የሁለት ቀናት ቆይታ የወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ጨምሮ የወረዳው ምክር ቤትና የወረዳው ፍርድ ቤት የግማሽ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት አድምጦ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪም የ2016 ዓ/ም የቀጣይ 6 ወራት የተከለሰ ዕቅድን ጨምሮ ጉባኤው በልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ በመምከር እንደሚያፀድቅ ከወጣው መረሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

በጉባኤው ላይ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የወረዳ አመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

08/03/2024
በአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን፤ የጆር ወረዳ ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ  በቅደሚ ዕለት ይጀምራል ።ከጆር ወረዳ የመንግ/ኮሙኒኬሽን  ጽህፈት ቤት (የካቲት 29/2016 ዓ.ም)የጆር ወረዳ ምክር ...
08/03/2024

በአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን፤ የጆር ወረዳ ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በቅደሚ ዕለት ይጀምራል ።

ከጆር ወረዳ የመንግ/ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት (የካቲት 29/2016 ዓ.ም)

የጆር ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ ዙር የምርጫ ጊዜ 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በቅዳሚ ቀን፡ 30__01/07/2016 ዓ/ም፡፡ ጀምሮ እንደካሄድ፤ የወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አስታወቁ።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ፡ ኡዶል ኡማን ኡምድ፤ እንደገለጹት ፤ ከቅዳሚ ጀምሮ የወረዳ ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ፤
በኡንጎጊ ከተማ ይካሄዳል።

ጉባኤው በሚኖረው የሁለት ቀናት ቆይታ የወረዳ ምክር ቤት ፤ የ2016 ዓ/ም፡፡ የሁለተኛ ሩብ ዓማት ሪፖርት፤ የልማትና መልካም አስተዳደር ዕቅድ፤የወረዳ ፍርድ

ቤት ፤ የስራ ክንውን ሪፖርት አድምጦ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የሰነበተው 11ኛው የመላ ጋምቤላ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ።ጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት የካቲት 24/2016 ዓ/ም*******************በጋምቤላ ከተማ...
03/03/2024

ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የሰነበተው 11ኛው የመላ ጋምቤላ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ።

ጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት
የካቲት 24/2016 ዓ/ም
*******************

በጋምቤላ ከተማ አስተናጋጅነት ከየካቲት 09 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የሰነበተው 11ኛው የመላ ጋምቤላ የወረዳዎች ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቋል፡፡

በጋምቤላ ስታዲየም በተካሄደው የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት ላይ የክልሉና የጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ተሳትፈዋል።

በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ስፖርት በትውልድና በሀገር ግንባታ ሂደት የማይተካ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በቀጣይ የክልሉን ስፖርት ተሳትፎ ለማሳደግ መንግስት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በየዓመቱ የሚካሄደው የመላ ጋምቤላ ስፖርታዊ ጨዋታ ተተኪ ወጣት ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አቶ ኡሞድ አስረድተዋል።

የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኒያል ቶት፥ 11ኛው የመላ ጋምቤላ የስፖርት ውድድር በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የክልሉ መንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ሌላው በውድድሩ መዝጊያ ቀን ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አቶ ጋትሉዋክ ጋች በበኩላቸው ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት ወጣቶችን በስፖርት ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በውድድሩ መዝጊያ ዕለት የወንዶች እግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ በአቦቦ ወረዳ እና በጋምቤላ ወረዳ መካከል ተካሂዷል።

ተመጣጣኝ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ወረዳዎች ጨዋታ በመደበኛው ሰዓት 0 ለ 0 የተለያዩ ሲሆን በመለያ ምት ጋምቤላ ወረዳ 5 ለ 4 በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዷል።

እንዲሁም በአትሌቲክስ ስፖርት ጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በሁለቱም ፆታዎች የ2016 ዓ/ም የመላ ጋምቤላ የስፖርት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

ለ15 ተከታታይ ቀናት በተካሄደው 11ኛው የመላ ጋምቤላ የስፖርት ጨዋታ በአጠቃላይ ድምር ውጤት የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ሆኖ አጠናቋል።

ዲማ ወረዳ ደግሞ በ11ኛው የመላ ጋምቤላ የወረዳዎች የስፖርት ውድድር በመልካም ስነ-ምግባር የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

የውድድሩ አሸናፊዎች እና ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላት የተዘጋጀላቸውን የዋንጫ ሽልማትና የእውቅና የምስክር ወረቀት ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተረክበዋል።

በመጨረሻም ቀጣይ 2017 ዓ.ም የሚደረገውን የመላ ጋምቤላ ስፖርታዊ ጨዋታ ጎደሬ ወረዳ እንዲያዘጋጅ ተመርጦ ውድድሩ ተቋጭቷል።

03/03/2024
128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በማስመልከት የቀረቡ ትርዒቶች በምስል !
02/03/2024

128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በማስመልከት የቀረቡ ትርዒቶች በምስል !

በጆር ወረዳ ምግብ ሰርት- ምግብ ፕሮራም በስቆጣ በጀት በ2016 ዓ/ም ከክልሉ ዉሃና ኢነርጅ/ቢሮ፣ ከመጡ ባለሙያ ጋር በመሆን፣ በኡንጎጊ ከተማ (4) የዉሃ ተቋማት፣ በሸንቶሃ 01 ቀበሌ (2...
02/03/2024

በጆር ወረዳ ምግብ ሰርት- ምግብ ፕሮራም በስቆጣ በጀት በ2016 ዓ/ም ከክልሉ ዉሃና ኢነርጅ/ቢሮ፣ ከመጡ ባለሙያ ጋር በመሆን፣ በኡንጎጊ ከተማ (4) የዉሃ ተቋማት፣ በሸንቶሃ 01 ቀበሌ (2) ሁለት የዉሃ ተቋማት እና በቱዎ ቀበሌ (1) አንድ የዉሃ ተቋማት ጥገና የተደረገውን መሆኑ እገኛል።
የጆር ወረዳ መንግሰት ኮሚኬሼን/ጽ/ቤት የካቲት/23/2016 ዓ/ም።

በዛሬ ዕለት ቀን 23/06/2016ዓ/ም መኸር እርሻ ልማት ትራንፎርሜሼን ዕቅድ(TAG) ዙሪያ ግንዛቤ ለሚፈተር ወደ ሥራ ለማሰገባት ለጆር ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ሳፊ ውይይት ተካሄዷዋል።
02/03/2024

በዛሬ ዕለት ቀን 23/06/2016ዓ/ም መኸር እርሻ ልማት ትራንፎርሜሼን ዕቅድ(TAG) ዙሪያ ግንዛቤ ለሚፈተር ወደ ሥራ ለማሰገባት ለጆር ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ሳፊ ውይይት ተካሄዷዋል።

Address

Gambella Region
Gambela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jor Woreda Press Secretariat Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share