Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office

Gambella Regional Gov’t  Press Secretariat Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office, Government Organization, Gambella.

የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚያደርገውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማጠናከር በጋምቤላ ከተማ 04 ቀበሌ ለምትገኝ አንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት የመሥራ...
05/09/2026

የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚያደርገውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማጠናከር በጋምቤላ ከተማ 04 ቀበሌ ለምትገኝ አንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት የመሥራት ሥራ ጀመረ።

ቢሮው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተቸገሩ ወገኖችን ለመደገፍ ያቀደው መርሃ ግብር፣ በከተማው በሚገኙ አምስቱም ቀበሌዎች በየስድስት ወሩ አንድ አንድ ቤት በመሥራት ተጠቃሚዎችን ለመደገፍ ያለመ ነው።

የቤት ግንባታ ፕሮግራሙ የቢሮው ሰራተኞች በበጎ ፈቃድ በሚያደርጉት አስተዋጽኦ የሚከናወን ሲሆን፣ በዚህም በተጨማሪ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ተጨባጭ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ የመረዳዳትና የመተባበር ባህልን ለማጠናከር ያግዛል።

በዛሬው ዕለት በ04 ቀበሌ የተጀመረው የቤት ግንባታ ሥራም የዚሁ መርሃ ግብር አካል ሲሆን፣ ቢሮው በቀጣይም በአምስቱም ቀበሌዎች በተያዘው ዕቅድ መሠረት ተግባሩን እንደሚያስፋፋ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አሪያት ኡጁሉ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ችግረኛና አቅመ ደካማ ወገኖችን በመደገፍ የማህበረሰቡን የመረዳዳት መንፈስ የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

ወይዘሮ አሪያት እንዳሉት፣ የቢሮው ሰራተኞች በጋራ በመሆን በየስድስት ወሩ አንድ ቤት ለመሥራት ያቀደው ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ በእውነተኛ የበጎ ፈቃድ ሥራ ለተቸገሩ ወገኖች የሚደርሰውን ድጋፍ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የቢሮው የሴቶች ግንዛቤ ንቅናቄ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ገ/የሱስ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የበጎ ፈቃድ ሥራ እንደ ተቋም ብቻ ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ ሊጎለብት የሚገባ እሴት መሆኑን ጠቁመው፣ ሰራተኞችና ሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎች በዚህ መልካም ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ቢሮው ከቤት ግንባታ በተጨማሪ በአዲሱ ዓመት እስከ 500 ለሚደርሱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እንዲሁም ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ አቅዷል።

እንዲሁም ለአዲሱ ዓመት የመዓድ ማጋራት መርሃ ግብር በማካሄድ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመካፈል የበዓል ደስታን በጋራ ለማጣጣም የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ለመፈጸም መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በዚህም ቢሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በማጠናከር አቅመ ደካማ ወገኖችን መደገፍ፣ የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ማጎልበት እና ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በተገቢው ሁኔታ እንዲያገኙ ማገዝ የሚያስችሉ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ እያከናወነ መሆኑ ተመልክቷል።

የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነትና የጽናት መልዕክትን ይዘው የሚንቀሳቀሱት ፓስተር ፖች ኦክዌር እና የሰላም ጉዞ እንግዳ የሆኑት አምባሳደር ፓስተር ኢዮብ ከተለያዩ ሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማ...
05/09/2026

የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነትና የጽናት መልዕክትን ይዘው የሚንቀሳቀሱት ፓስተር ፖች ኦክዌር እና የሰላም ጉዞ እንግዳ የሆኑት አምባሳደር ፓስተር ኢዮብ ከተለያዩ ሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋምቤላ ከተማ ውይይት አድርገዋል።

የሰላም አምባሳደር ፓስተር ኢዮብ ባስተላለፉት መልዕክት ይቅርታ ያለፉትን ቁስሎች እና በግጭት የተፈጠሩ በደሎችን በይቅርታ በመሻገር ወደፊት ለመራመድ በር የሚከፍት እና በህዝቦች መካከል ያለውን አለመግባባት በማስወገድ እርስ በርስ የመደጋገፍ ባህልን ያጠናክራል።

የሰላም ጉዞው በክልሉ ህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማስረፅ እና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረውም ጠቁሟል።

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ቆይታ በኋላ ወደ ትውልድ ቀዬው የተመለሰው ፓስተር ፖች ኡኩዌር፣ አባቱን ፕሪስት ኦክዌርን ጨምሮ በቤተሰቡና በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ጉዳት በልቡ ይዞ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ይህንን የግልና የቤተሰብ ሐዘን ወደ በቀል ሳይቀይር፣ ይቅርታን፣ እርቅን፣ አንድነትንና ሰላምን መምረጡን በተግባር እያሳየ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት የአባቱንና ሌሎች የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ የቤተሰብ አባላትን መቃብር በመጎብኘት ጸሎት ያደረገው ፓስተር ፖች፣ የሰላምና የይቅርታ መልዕክትም አስተላልፏል።

ይህ የሰላም ጉዞ በCommunity Peace, Reconciliation, Unity and Development Association (CPRDA) በኩል የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነትና የጽናት መልዕክትን ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።

አምባሳደር ፓስተር ኢዮብ በጋምቤላ የሚያደርጉት የሰላም ጉዞ፣ በማህበረሰቡ መካከል የመተሳሰብ፣ የይቅርታና የእርቅ እሴቶችን ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

የፓስተር ፖች ኦክዌር የሰላም ጉዞ ከበቀል ይልቅ ይቅርታን፣ ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን፣ ከጥላቻ ይልቅ ሰላምን መምረጥ የሚቻል መሆኑን የሚያሳይ የተግባር ምስክር ሆኗል።

የጋምቤላ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ኡቶር ኡኩጉ በወቅቱ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ አለመግባባቶችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና አወንታዊ ሰላምን የማስፈን ሥራዎችን ለማምጣት ያግዛል ተብለዋል።

ምክትል ከንቲባው አክለውም የአይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የራሳቸውን ዕውቅና በመጠቀም በሰላም ዙሪያ በየእምነታቸው ስለ ሰላም ጥቅም በመናገር የራሳቸውን ሃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የኩሚ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች የህክምና አገልግሎትና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።የኩሚ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የክረምት የበጎ ፍቃድ አ...
05/09/2026

የኩሚ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች የህክምና አገልግሎትና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኩሚ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነ በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች የህክምና አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ለሴት ታራሚዎችም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኩሚ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን በማረሚያ ቤቱ ተገኝተው የታራሚዎችን የጤና ሁኔታ በመረመር ነጻ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭ ሊሆኑ ለሚችሉ የማረሚያ ቤቱ ታራሚዎችን ተገቢውን የህክምና ምክርና ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችንም ጭምር ለታካሚዎች ሰጥተዋል።

የኩሚ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አለኝታ ጌታቸው እንደተናገሩት ማረሚያ ቤት መገኘት ማለት ከህብረተሰብ ተነጥሎ መኖር ማለት አይደለም ታራሚዎችም የዚህ ማህበረሰብ አካል እንደመሆናቸው መጠን ተገቢውን የጤና እንክብካቤ እና ሰብአዊ ድጋፍ የማግኘት መብት እንዳላቸው ተናግረዋል።

በመሆኑም ሆስፒታላችን በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር አቅማችን የፈቀደውን ያህል ድጋፍ በማድረግ የዜግነት ኃላፊነታችንን ለመወጣት በመገኘታችን ደስተኞች ነን ስለሆነም መሰል የድጋፍ እና የእንክብካቤ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የሆስፒታሉ ከፍተኛ ባለሙያ እና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ፍስሀ መንግስቴ በበኩላቸው በክረምት ወራት የሚከናወኑ እንደነዚህ ያሉ የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሮች የታራሚዎችን ሰብአዊ መብት ከማክበር ባለፈ፣ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጤንነታቸውን በመጠበቅ ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ሰፊ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመዋል

ስለሆነም በማረሚያ ቤቱ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት የደም ግፊት ምርመራ እና ህክምና የስኳር በሽታ ምርመራ እና ህክምና ፣ የልብ ምትና የአልትራሳውንድ ምርመራ ፣ የኤች አይ ቪ ምርመራ እና ህክምና ፣ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ እና ህክምና እንዲሁም የጤና ትምህርትና ምክር እና ሌሎችም አገልግሎት መሰጠቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪ ለሴት ታራሚዎች የሚሆን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረ መሆኑን እና ድጋፉ በሴቶች ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለማቃለል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አቶ ፍስሀ አመላክተዋል።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ታራሚዎች በበኩላቸው ወደ እኛ መጥታችሁ ነጻ ሕክምና በማድረጋችሁ እና ያጋጠመንን የቁሳቁስ እጥረት በመረዳት ድጋፍ በመስጠታችሁ የተሰማንን ልባዊ ምስጋና እያቀረብን በስነ-ልቦና ትልቅ ጥንካሬ እና እንክብካቤ እንዳለን እንዲሰማን ስላደረጋችሁን የተሰማንን ጥልቅ ደስታና ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።

#ጎደሬ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

ኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም 15ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱን በማካሄድ በተለያዩ የትምህርትና ሙያ መስኮች የሰለጠኑ 159 ተማሪዎችን አስመርቋል።ከተመራቂዎቹ መካከል 155 ተማሪዎ...
05/09/2026

ኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም 15ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱን በማካሄድ በተለያዩ የትምህርትና ሙያ መስኮች የሰለጠኑ 159 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 155 ተማሪዎች በደረጃ አራት፣ አራቱ ተማሪዎች ደግሞ በደረጃ ሦስት ትምህርታቸውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀው ምስክር ወረቀታቸውን ተቀብለዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጋምቤላ ክልል ሥራና ክህሎት ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰናይ አኩዎር፣ የተመራቂ ተማሪዎች የዛሬ ስኬት ምስክር ወረቀት ማግኘት ብቻ ሳይሆን የጥረታቸውና የተስፋቸው ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሰናይ አክለውም፣ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ውስጥ ዕውቀትን ብቻ ማግኘት ሳይሆን እጅ ላይ ሥራ የሚፈጥር ክህሎት አዳብሮ መውጣት ዋና ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ ባገኙት ሙያና ክህሎት መሠረት ራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ አቶ ሰናይ አሳስበዋል። ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለሀገር ልማትና እድገት ያለው አስተዋጽኦም ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ተመራቂዎቹ ከዛሬ ጀምሮ በተማሩት ሙያና ባገኙት ክህሎት በመታገዝ፣ በጥሩ ሥነ-ምግባርና ችሎታቸውን በአግባቡ በመጠቀም የማኅበረሰቡን ችግር ፈቺ በሆኑ ሥራዎች እንዲሰማሩና የሕዝብ አገልጋይ እንዲሆኑም አስገንዝበዋል።

የኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ኤሊያስ ያዕቆብ በበኩላቸው፣ 15ኛው ዙር የተማሪዎች ምረቃ ልዩ የሚያደርገው ኢትዮጵያ በራሷ የሰው ኃይል፣ በዕውቀትና በክህሎት የሀገር ግንባታ በምታካሂድበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች በግንባታ፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በመረጃ ቴክኖሎጂና በሌሎች የሥራ መስኮች ያገኙትን ክህሎት በአግባቡ በመጠቀም ሀገራቸውን ወደምትፈልገው የብልጽግና ጉዞ ማሻገር እንደሚችሉም አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል።

ተመራቂዎቹ ሥራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች በመሆን፣ በሙያቸው ያሉ ችግሮችን በመለየት ተግባራዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ፣ አዳዲስ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁና ሀሳቦቻቸውን ወደ ምርትና አገልግሎት እንዲቀይሩ ዋና ዲኑ አሳስበዋል።

ኮሌጁ ባለፉት አራት ዓመታት ሥልጠናውን የተከታተሉ 159 ሰልጣኞችን ማስመረቁን የተገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህም 40 ወንዶች እና 119 ሴቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ባለፉት አራት ዓመታት ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።

የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር (LLRP-II) የ2018 ዓ.ም የዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት ለሁ...
05/09/2026

የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር (LLRP-II) የ2018 ዓ.ም የዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት ለሁሉም የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትና ሠራተኞች የማስተዋወቅ መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሄደ።

የክልሉ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶክተር ቤል ቢቾክ ቸፕሮጀክቱ በ2018 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችንና በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ተግዳሮቶችን በመገምገም የቀጣይ ዓመት ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ መፈጸም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዶክተር ቤል ቢቾክ እንደገለጹት፣ የLLRP-II ፕሮጀክት ዋና ትኩረት በቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦችን የኑሮ መረጋጋትና የመቋቋም አቅም ማጠናከር ሲሆን፣ ይህንን ለማሳካት የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት በዕቅድ፣ በአፈጻጸምና በክትትል ሂደት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በተለይም የፕሮጀክቱ የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በተገቢው ሁኔታ እንዲፈጸም፣ የተመደበው በጀት ለታቀዱ ተግባራት ብቻ በብቃትና በጥንቃቄ መጠቀም፣ የሥራ አፈጻጸም በየደረጃው በመከታተል የታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ ማስተካከል እንደሚገባ አስተባባሪው አሳስበዋል።

በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት አፈጻጸም በመገምገም፣ በ2019 ዓ.ም ለፕሮጀክቱ የተያዘው ዕቅድና በጀት ለተሳታፊዎች ቀርቧል። በተጨማሪም በፕሮጀክቱ የተካተቱ የግጭት ተያያዥ የሀብት አያያዝ፣ የአየር ንብረት መቋቋምና ዘላቂ የኑሮ ማጠናከሪያ ሥራዎች ላይም ትኩረት ተደርጓል።

በሌላ በኩል፣ የፕሮጀክቱ የጥራት አስተዳደር፣ የሥራ ክትትልና ግምገማ፣ የግዥና የፋይናንስ አስተዳደር እንዲሁም የቅሬታ አፈታት ሥርዓት በተገቢው እንዲተገበር ተሳታፊዎቹ በጋራ መወያየታቸው ተገልጿል።

የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በውጤታማነት መፈጸም በመስክ የሚገኙ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች፣ የዞንና ወረዳ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች በጋራ በመስራት ለማህበረሰቡ የሚደርሱ የልማት ጥቅሞችን ማሳደግ እንደሚጠይቅ በውይይቱ ተገልጿል።

LLRP-II በክልሉ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ መረጋጋትንና የማህበረሰብ መቋቋም አቅምን ለማጠናከር የሚሰራ ፕሮጀክት ሲሆን፣ በዓለም ባንክና በIFAD ድጋፍ ከፌዴራልና ከክልል ተቋማት ጋር በመተባበር የሚተገበር መሆኑ ከመድረኩ መረጃ ይታያል።

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከኢሉአባቦር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በአኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን ወሰን ተሻጋሪ የዜግነት አገልግሎት አበረከቱ።​በኢ...
04/09/2026

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከኢሉአባቦር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በአኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን ወሰን ተሻጋሪ የዜግነት አገልግሎት አበረከቱ።​

በኢሉአባቦር ወጣቶች ክንፍ የተደረገው የዜግነት አገልግሎት፥የዞኑ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ከማስታገስ ባለፈም በዜጎች መካከል የትብብር፣ የአብሮነት እና የጋራ ኃላፊነት መንፈስን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

የአኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውኃና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አቡዎላ ኡኳዮ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፥ የኢሉአባቦር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክልል እና የዞን ወሰኖችን በማሻገር ያበረከተው የዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ አብሮነትን እና አጋርነትን ማጠናከር የሚቻልበትን የፖለቲካ እና የማህበራዊ ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።

የኢሉአባቦር ዞን ወጣቶች ክንፍ ያበረከተው ድጋፍ የእርስ በእርስ ትስስርና የጋራ አላማ ከማጠናከር ባለፈም ​ፓርቲያችን ብልጽግና የያዛቸውን ታላላቅ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ለማሳካት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አመላክተዋል።

​የኢሉአባቦር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ምትኬ ለገሰ በበኩላቸው፥የኢሉአባቦር ዞን ወጣቶች ክንፍ ክልላዊ ወሰንን አልፈው ወደ አኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን የመጡት አካላዊ ርቀትን ሰብረው ከወንድም ህዝቦች ጋር ያላቸውን ፍቅርና አብሮነት በተግባር በማሳየት የዜግነት አገልግሎት ለማበርከት መሆኑን ጠቁመዋል።

ወጣቱ ትውልድ የሀገሪቱን የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ጉዞ በባለቤትነት እየመራ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ምትኬ፥የዛሬው የዜግነት አገልግሎት መርሃ ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ከፍታ በወጣቶች ጉልበት እና ትብብር እውን ለማድረግ የያዘውን ፅኑ አቋም የሚያሳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተለይም ብልጽግና ፓርቲ ልዩነቶችን እንደ ጸጋ ወስዶ በጋራ በመቆም ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት የሚያስችለውን አቅጣጫ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለአኙዋኣ ብሔረሰብ ከተደረገላቸው ድጋፎች ፍራሽ ፣ብርድ ልብስ፣ ፣ደብተር ፣እስክሪብቶ፣ቦርሳ ፣የምግብ ዘይትና ሳሙና እንደሚገኝባቸውን ወይዘሮ ምትኬ ጨምሮ ገልጸዋል።

የጋምቤላ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የባህልና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዘርፈ ኃላፊ አቶ ፔን ኡጁሉ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ፥የኢሉአባቦር ዞን ወጣቶች ወሰን ተሻግረው ያሳዩት የዜግነት አገልግሎት ተግባር የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይም የወጣቶች ትስስር ምን ያህል የፀና እና የማይበጠስ መሆኑን ህያው ማሳያ ነው ብለዋል።

አያይዘውም የጋምቤላ ክልል ህዝብ ከሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ከመጡ ወንድም ህዝቦች ጋር ባለው ታሪካዊ ትስስር እንደሚያኮራ ገልጸው፣ የብልጽግና ፓርቲ እውነተኛ ሀገራዊነትን እና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በተግባር እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም የኦሮሚያ እና የጋምቤላ ክልል ህዝቦች ከጥንት ጀምሮ የነበራቸውን የጋራ እሴቶችን ይበልጥ የሚያጸና እና ወሰን አቋርጦ የሚቀጥል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በጋምቤላ ክልል የግብርና ልማትን ለማጠናከር የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።በክልሉ የሚከናወነውን የ...
04/09/2026

በጋምቤላ ክልል የግብርና ልማትን ለማጠናከር የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

በክልሉ የሚከናወነውን የግብርና ልማት ስራ ለመገምገምና ለቀጣይ የግብርና ልማት ንቅናቄ ለማጠናከር የባለሙያዎችና የቴክኒክ ኮሚቴ ቡድን ስምሪት ተደርጓል።

የብልፅግና ፓርቲ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን ለቴክኒክ ኮሚቴውና ለባለሙያዎች ቡድኑ በሰጡት አቅጣጫ፣ የግብርና ልማቱን ለማጠናከር በዘርፉ የሚገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በክልሉ እየተከሰተ ያለውን የድርቅ ሁኔታ ለመቋቋምም በቀጣይ ወራት አርሶ አደሩ ብቻ ሳይሆን መላው ማህበረሰብ በመስኖና በውሃ ሽሽ ልማት ላይ በመሰማራት ምርታማነቱን ማሳደግ እንደሚገባ አቶ አሽኔ አስገንዝበዋል።

በስምሪቱ መሰረት የባለሙያዎች ቡድኑ ወደ ዞኖችና ወረዳዎች በመውረድ በታቀደው ዕቅድ መሰረት የማህበረሰብ ንቅናቄ እንዲፈጥርና ውጤታማ የግብርና ልማት ስራ እንዲከናወን ተጠባቂ መሆኑንም ገልጸዋል።

አቶ አሽኔ አክለውም፣ የመስኖና የውሃ ሽሽ ልማት አቅም ባለበት አካባቢ ማን ማምረት እንዳለበትና ምን ዓይነት የሰብል ዓይነቶች መመረት እንዳለባቸው በመለየት ወደ ምርት መግባት እንደሚገባ አስረድተዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድሪዉ ቱት በበኩላቸው፣ በዘንድሮ የምርት ዘመን የዝናብ እጥረት በመከሰቱ በአርሶ አደሩ ሰብል ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

የድርቁ ያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስና ለማካካስ ማህበረሰቡ ወደ መስኖና የውሃ ሽሽ ልማት በመሰማራት ምርታማነትን ለማሳደግ ባለው አቅም ሁሉ መረባረብ እንደሚገባ አቶ አንድሪዉ ገልጸዋል።

ወደ ዞንና ወረዳዎች የተሰማራው የባለሙያዎች ቡድንና ባለድርሻ አካላትም በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር በባለቤትነት ስሜት ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቡድኑ በዞኖችና በወረዳዎች በሚያደርገው የሁለት ሳምንት ቆይታም የ2018/2019 ዓ.ም የመኸር ግብርና ልማት ያለበትን ሁኔታ የሚገመግም ሲሆን፣ በግምገማው የሚለዩ ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ የግብርና ልማት ስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ይሰራል።

የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶችን  ለማጠናከር  በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ  የሚሳተፉ የጋምቤላ ክልል እንግዶች ደምቢዶሎ ከተማ ገቡየቡድኑ አባላት  ውይይቱ በሚካሄድበት ወደ ደምቢዶ...
04/09/2026

የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶችን ለማጠናከር በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የሚሳተፉ የጋምቤላ ክልል እንግዶች ደምቢዶሎ ከተማ ገቡ

የቡድኑ አባላት ውይይቱ በሚካሄድበት ወደ ደምቢዶሎ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል

ከክልሉ በመድረኩ ላይ የሚሳተፉ እንግዶች ደንቢዶሎ አየር ማረፍያ ሲደርሱ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የሁለቱ ክልሎች የጋራ የውይይት መድረክ በነገው ዕለት እንደሚካሄድ ተገልጿል

የጋምቤላ ወረዳ ምክር ቤት ከ476 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ 36ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ።​የጋምቤላ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ የምርጫ ጊዜ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉ...
04/09/2026

የጋምቤላ ወረዳ ምክር ቤት ከ476 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ 36ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ።

​የጋምቤላ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ የምርጫ ጊዜ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2019 በጀት አመት የስራ እቅድ እና ማስፈፀሚያ የሚሆን በጀት መርምሮ በማፅደቅ ተጠናቋል።

ለ2019 በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከወረዳው የራስ ገቢ፡ 246 ሚሊዮን 589 ሺህ 741 ብር ሲሆን ፤ ​ከክልሉ መንግሥት የተመደበ ድጎማ፡ 230 ሚሊዮን 47 ሺህ 493 ብር ነው።

​በዚህም መሠረት የጋምቤላ ወረዳ የ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ የገቢ እና የድጎማ በጀት 476 ሚሊዮን 637 ሺህ 234 ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

​የፀደቀው በጀት በወረዳው የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አጁሉ ኡጁሉ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት በ2019 በጀት አመት የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ቅንጅታዊ ትብብር ሊኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በወረዳው ሰላምን በማፅናት ለሁለንተናዊ ብልፅግና እና ልማት በጋራ እንትጋ ሲሉም አሳስበዋል።

የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነትና የፅናት መልዕክትን ይዘው የሚንቀሳቀሱትና የሰላም ጉዞ  አምባሳደር የሆኑት  ፓስተር ኢዮብ ጋምቤላ ገቡ።ጋምቤላ አየር ማረፍያ ሲደርሱም የሰላም፣የአንድነትና የፅ...
04/09/2026

የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነትና የፅናት መልዕክትን ይዘው የሚንቀሳቀሱትና የሰላም ጉዞ አምባሳደር የሆኑት ፓስተር ኢዮብ ጋምቤላ ገቡ።

ጋምቤላ አየር ማረፍያ ሲደርሱም የሰላም፣የአንድነትና የፅናት መልዕክትን ይዘው የሚጓዙት ፓስተር ፖች ኡኩዌር፣ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችና የሰላም ባለራዕዮች አብያተ ክርስትያናት ህብረት አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የአምባሳደሩ ወደ ጋምቤላ መምጣት በክልሉ የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነትና የጽናት መልዕክትን ለማጠናከር ከሚደረገው ጥረት ጋር የተያያዘ መሆኑን ተገልጿል።

Address

Gambella

Telephone

+251905688270

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office:

Shortcuts

Share