Gamo Zone Geresse Zuria woreda government communication affairs office

  • Home
  • Ethiopia
  • Gerese
  • Gamo Zone Geresse Zuria woreda government communication affairs office

Gamo Zone Geresse Zuria woreda government communication affairs office Hayissi Gereththe yusho worada qodumaga yafarako !!

አስቾካይ የጉባኤ ጥሪ!!ገርሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ምክር ቤት በቀን 30/12/2018 ዓ/ም 4ኛ ዙሪ መርሐ ግብር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ዙር አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋል።   የወረዳው ም...
04/09/2026

አስቾካይ የጉባኤ ጥሪ!!
ገርሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ምክር ቤት በቀን 30/12/2018 ዓ/ም 4ኛ ዙሪ መርሐ ግብር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ዙር አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋል።

የወረዳው ምክር ቤት አባላት 2:30 ስዓት ላይ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስ/ር አዳራሽ እንድትገኙ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዜና ችሎትየሕዝብና የመንግስት  ጥብቅ ደን ዉስጥ በመግባት ወረራ በመፈጸም ለእርሻ በማስፋፋት ወንጀል በተከሰሱ 8 ሰዎች ላይ የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ተላለፈባቸው።የገረሴ ዙሪያ ወረዳ...
01/09/2026

ዜና ችሎት
የሕዝብና የመንግስት ጥብቅ ደን ዉስጥ በመግባት ወረራ በመፈጸም ለእርሻ በማስፋፋት ወንጀል በተከሰሱ 8 ሰዎች ላይ የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ተላለፈባቸው።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት በገረሴ ዙሪያ ወረዳ በኮሻሌ ቀበሌ በሚገኘው በቃቄ ደን እና በቶልኮወራ ደን ውስጥ በመግባት ከ25 ሄ/ር በላይ የደን መሬት ላይ ወረራ በመፈጸም ደኑን መንጥረው በመያዝ ባረሱ 8 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ የፌደራል የደን ልማት፡ጥበቃ እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር፦1065/2010 አንቀጽ፦25(1) እና 26(4) በመጥቀስ ክስ መሥርቷል።

3ቱ ተከሳሾች ችሎት ቀርበው የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸውንና ጥፋተኛነታቸውን አምነው በመከራከራቸው በሰጡት የእምነት ቃል መሰረት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር፦134(1) መሠረት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቱዋል፡፡

ቀሪ 5ት ተከሳሾች ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ህግ ማስረጃ አቅርቦ አስረድቶ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን የሰጠ ብሆንም ተከሳሾቹ ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃዎች የዐቃቤ ህግን የማሰረጃ ቃል በሚያጠናክር ሁኔታ ተከሳሾች ወደ ደን ክልል ውስጥ በመግባት ደኑን መንጥረው ማረሳቸውን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የማስረጃ ቃል በመመርመር ተከሳሾች ያልተከላከሉ በመሆናቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ በተከሳሾች ላይ በማስተላለፍ በግራ ቀኙ በኩል የቀረበዉን የቅጣት አስተያየት በማመዛዘን ተከሳሾችን ያርማል ለሎችን ያሰተምራል በማለት በ5ቱ ተከሳሾች ላይ የሁለት ዓመት ፅኑ እሥራትና የ7500ብር የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ወስኗል።

የቀሩት ሶስት ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ አምነው የተከራከሩ በመሆናቸው፣ ከዚህ አስቀድሞ በሌላ ወንጀል ተቀጥተው የማያውቁ በመሆናቸው ምክንያት እና የያዙትን የደን ይዞታ ለቀው ለመውጣት ፊቃደኛ መሆናቸውንም በችሎት ያመለከቱ በመሆናቸው በሶስቱም ላይ የተወሰነው የእስራት ቅጣት በሁለት ዓመት ተገድቦ እና በ10 ሽህ ብር የመቀጮ ቅጣት እንዲቀጡ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኑዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አራቱም ተከሳሾች በቀን 5/13/2018 ዓ.ም ዕለቴ ሐሙስ በሚውለው የኮሻሌ ገበያ ላይ ዞሬው ስለ ደን ጥቅምና ደንን የወረረ ሰው የሚቀጣውን ቅጣት፣ ለ2 ሰዓት በገበያው ውስጥ በማወጅ ህዝቡን በማስተማር ሪፖሪት እንዲያቀርቡ ጭምር ውሳኔ ማስተላለፉን የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት አሳውቋል።

በ2018 ዓ.ም መልካም አፈጻጸም ላስመዘገቡ የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አባላት የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበረከተገረሴ፦ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገል...
31/08/2026

በ2018 ዓ.ም መልካም አፈጻጸም ላስመዘገቡ የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አባላት የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበረከተ

ገረሴ፦ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)

በ2018 ዓ.ም በነበራቸው የታዛዥነት፣ ተልዕኮን በድልና በጀግንነት በመወጣት መልካ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አባላት የዕውቅና ሰርቲፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ።በዚሁ መሠረት ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከ1 - 3ኛ የወጡ 1ኛ፡ ዋና ሳጅን ማርቆስ አብርሃም፣2ኛ፡ ሳጅን ተሾሜ ኡሙቃ፣ 3ኛ፡ ዋና ሳጅን ጌታቸው ቱናቃ የዕውቅና ሰርቲፊኬት እና የማበረታቻ ተሸላሚ የሆኑ ሲሆን፣ በየሥራ ሂደቱ መልካም አፈጻጸም ያሳዩ ሌሎች የፖሊስ አባላትም የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተረክበዋል።

የመድረኩን ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የገረሴ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ መንዛ፣ ካለንበት ወቅት አንጻር ጉድለቶችን የማረምና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን የማበረታታት ሥራ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። በፖሊስ ተቋሙ የታየው በጎ ጅምር ከፍ ብሎ መታየት እንዳለበት ጠቁመው፣ የወረዳውን ሰላምና ጸጥታ በላቀ ደረጃ ማስጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም ከአባላቱ የተነሱት ጠቃሚና ገንቢ አስተያየቶች ህዝብን በሙሉ ፍላጎት ለማገልገል ከፍተኛ መንፈስ እንደሚፈጥሩ ገልጸው፣ ባለፈው ዓመት በጋርባንሳ ክላስተር የተካሄደው "ከወንጀል ነፃ ቀጠና" የማድረግ በጎ ልምድ በሌሎች ቀበሌዎችም ተስፋፍቶ እንዲቀጥል በትኩረት መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መድረኩን በጋራ የመሩት የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ካሳዬ፣ የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ታዬ እና የፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ማቴዎስ መርጊያ በበኩላቸው፣ የፖሊስ አባላት ግዴታቸውን በአግባቡ እየተወጡ በመሆኑ መብታቸው ሊከበርላቸው እንደሚገባ ገልጸዋል። በተጨማሪም የተሽከርካሪና የትጥቅ እጥረት የመሳሰሉ የሎጂስቲክስ ችግሮች በቀጣይ ሊፈቱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም በአፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ የተገለጹ ጉድለቶችን በማረም መሠራት እንዳለበትና ወረዳው ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር የሚነሱ የጸጥታ ችግሮችን ግንባር ቀደም ሆኖ ላደረጉት አስተዋጽኦ ከዞኑ ዕውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም የፖሊስ ተቋሙን ለማዘመንና የተሽከርካሪ እጥረቶችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሠራ የተገለጸ ሲሆን፣ ከአስቸኳይ የትራፊክ ቁጥጥር ባለፈ የገቢ አሰባሰብ ላይ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸው ተጠቅሶ አባላት አንድነታቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው ተመልከቷል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እያካሄ ይገኛል።ገረሴ፦ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት...
31/08/2026

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እያካሄ ይገኛል።

ገረሴ፦ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ካሳዬ እንደገለጹት፤ ፖሊስ የሀገርን ሰላምና የሕዝብን ደኅንነት የማስጠበቅ ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮና ኃላፊነት ያለበት ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባለፈው ዓመት ያጋጠሙ በርካታ ፈተናዎችን በፖሊስ አባላት ትጋትና ጥንካሬ በሰላም ማለፍ መቻሉን የገለጹት ምክትል ዋና አስተዳዳሪው፤ በተለይም በአጎራባች ወረዳዎች ተከሰቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ወቅት የፖሊስ ሰራዊቱ ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግረው በግንባር ቀደምትነት ተሰልፎ ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ሰላምን ማስከበር መቻሉን ገልጸዋል።

አክለውም ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሚሰሩ የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍ፣ በሁሉም የወረዳው ቀበሌያት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለተሠራው ሥራ አክብሮት የሚያሰጥ ሥራ የፖሊስ ተቋሙ ከፍተኛ ምስጋናና ዕውቅና እንደሚገባው ተናግረዋል።

ይህ የጽናትና የውጤታማነት ጉዞ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ ከድር፤ በተለያዩ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎች ብቃታቸውን አጎልብተው የመጡ መኮኒኖች በትምህርት ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ በተግባር በማዋል፣ ለሌሎች አባላት በማካፈልና እርስ በእርስ በመተባበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ማቴዎስ መርጊያ በበኩላቸው፤ ተቋሙ በ2018 ዓ.ም በርካታ ውጣ ውረዶችንና ፈተናዎችን አልፎ ስኬታማ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።

እንስፔክተሩ አክለውም፤ በአጎራባች ወረዳዎች በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች የተሰጡ ግዳጆችን በብቃት በመወጣት፣ የ2018 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ፣ የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ክልላዊና ሀገራዊ ፈተናዎች በሰላም ተጠናቀቀው እንዲሸኙ ጥበቃ በማድረግ፣ እንዲሁም የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ሥራዎችን በመሥራት የወረዳው ጸጥታ ያለ ምንም ሥጋት በሰላም እንዲያልፍ መደረጉን ገልጸዋል።

በእነዚህ ሁሉ ተግዳሮቶች ውስጥ አንድም የሰው ሕይወት ሳያልፍ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን ጠቅሰው ፈጣሪን በማመስገን፤ ለዚህ አበራታች አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፖሊስ አባላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም የፖሊስ አዛዡ ለተቋሙ ውጤታማነትና ለተልዕኮው መሳካት ላደረጉት አስተዋጽኦ ለገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር እና ለወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የገቢ አፈጻጸም እና የ2019 ዓ.ም የገቢ ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።ገረሴ፦ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮ...
28/08/2026

በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የገቢ አፈጻጸም እና የ2019 ዓ.ም የገቢ ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

ገረሴ፦ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)

ውይይቱን የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ካሳዬ፣ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ መንዛ እና የገቢዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ በጋራ መርተውታል።

የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ካሳዬ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

አክለውም የገቢ አማራጮችን አሟጦ መሰብሰብ እንደሚገባ፣ ባለፈው ዓመት ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሳዩ የማዘጋጃ ቤት ገቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባና የኦዲት ግኝቶችን ላይ ትኩረት መሠራት እንዳለበት አስዝበዋል።

የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ መንዛ በበኩላቸው፤ የገቢ ስብሰባ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው የዓመቱን ዕቅድ በቀን፣ በሳምንትና በወር ከፍሎ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ማዘጋጃ ቤቶች የሕዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የገቢ አቅማቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው የጠቆሙት አቶ መለሰ፤ የንግድ ጽሕፈት ቤት ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ሕጋዊ መስመር የማምጣትና የማዕድን ገቢዎችን በየዓመቱ የማሳደግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ የገቢዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ በ2019 በጀት ዓመት 240 ሚሊዮን 751 ሺህ 175 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል።

ይህንንም ዕቅድ ለማሳካት የገበያ በረቶችን ማጠናከር እና የመኪና ማረፊያ መናኸሪያዎችን ማስፋፋት፤ ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን፣ የሞተር ሳይክሎችንና የደንብ መጣስ ድርጊቶችን መቆጣጠር፤ የማዕድን ገቢዎችን አሟጦ መሰብሰብ እንዳለበት አስታውቋል።

በትምህርት ቤቶች በጥረ ገንዘብና የሕብረተሰብ ተሳትፎዎችን ወደ ገቢ ሥርዓት ማስገባት፤ ከጤና ተቋማት፣ ከደን ውጤቶች፣ ከቁም እንስሳት፣ ከአርሶ አደሮች የመሬት መጠቀሚያ ግብር እና ከኦዲት ግኝቶች የሚገኙ ገቢዎችን በሙሉ አቅም መሰብሰብ ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

የጋርባንሳ ጋርቼ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ አንድ በሬ በመስጠት  ተሰጥቷል።የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለጋ/ካርቼ ቀበሌ ምሥጋና...
27/08/2026

የጋርባንሳ ጋርቼ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ አንድ በሬ በመስጠት ተሰጥቷል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለጋ/ካርቼ ቀበሌ ምሥጋና እያቀረበ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል።

#ሀብታችንን ለታላቁ ስታዲዬማችን! ​"በጋራ እንነሳ፣ በትብብር እንገንባ፣ በአንድነት እንጨርስ!" በሚል መሪህ ቃል የተጀመረውን የሦስተኛ ዙር የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ይሳተፉ ስታዲየሙን ያጠናቂቁ !!

​የገቢ_ማሰባሰቢያ_የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000640532851

የአልጉዴ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ ሁለት በጎችን በመስጠት  ተሰጥቷል።የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለአልጉዴ ቀበሌ ምሥጋና እያቀ...
27/08/2026

የአልጉዴ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ ሁለት በጎችን በመስጠት ተሰጥቷል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለአልጉዴ ቀበሌ ምሥጋና እያቀረበ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል።

#ሀብታችንን ለታላቁ ስታዲዬማችን! ​"በጋራ እንነሳ፣ በትብብር እንገንባ፣ በአንድነት እንጨርስ!" በሚል መሪህ ቃል የተጀመረውን የሦስተኛ ዙር የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ይሳተፉ ስታዲየሙን ያጠናቂቁ !!

​የገቢ_ማሰባሰቢያ_የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000640532851

የጋርባንሳ ሦሮጌ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ ሁለት በሬ በመስጠት  ተሰጥቷል።የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለጋርባንሳ ሦሮጌ ቀበሌ ...
27/08/2026

የጋርባንሳ ሦሮጌ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ ሁለት በሬ በመስጠት ተሰጥቷል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለጋርባንሳ ሦሮጌ ቀበሌ ምሥጋና እያቀረበ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል።

#ሀብታችንን ለታላቁ ስታዲዬማችን! ​"በጋራ እንነሳ፣ በትብብር እንገንባ፣ በአንድነት እንጨርስ!" በሚል መሪህ ቃል የተጀመረውን የሦስተኛ ዙር የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ይሳተፉ ስታዲየሙን ያጠናቂቁ !!

​የገቢ_ማሰባሰቢያ_የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000640532851

የዳንብ ኦቶራ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ አንድ በሬ በመስጠት  ተሰጥቷል።የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለዳንብሌ ኦቶራ ቀበሌ ምሥጋ...
27/08/2026

የዳንብ ኦቶራ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ አንድ በሬ በመስጠት ተሰጥቷል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለዳንብሌ ኦቶራ ቀበሌ ምሥጋና እያቀረበ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል።

#ሀብታችንን ለታላቁ ስታዲዬማችን! ​"በጋራ እንነሳ፣ በትብብር እንገንባ፣ በአንድነት እንጨርስ!" በሚል መሪህ ቃል የተጀመረውን የሦስተኛ ዙር የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ይሳተፉ ስታዲየሙን ያጠናቂቁ !!

​የገቢ_ማሰባሰቢያ_የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000640532851

የጎራቴ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ የተለያዩ ስጦታዎችን በዓይነት በማሰባሰብ  ምላሽ እየሰጠ ይገኛል።የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ...
26/08/2026

የጎራቴ ቀበሌ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሀብት ማሰባሰቢያ ሦስተኛ ዙር የድጋፍ ጥሪ የተለያዩ ስጦታዎችን በዓይነት በማሰባሰብ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ለጎራቴ ቀበሌ ምሥጋና እያቀረበ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል።

#ሀብታችንን ለታላቁ ስታዲዬማችን! ​"በጋራ እንነሳ፣ በትብብር እንገንባ፣ በአንድነት እንጨርስ!" በሚል መሪህ ቃል የተጀመረውን የሦስተኛ ዙር የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ይሳተፉ ስታዲየሙን ያጠናቂቁ !!

​የገቢ_ማሰባሰቢያ_የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000640532851

Address

Gerese

Telephone

+251964867066

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Geresse Zuria woreda government communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gamo Zone Geresse Zuria woreda government communication affairs office:

Shortcuts

Share