West denbiya woreda court

West denbiya woreda court ለፍትህ መስፈን ሁሉም ድርሻ አለው::
ፍርድ ቤት ደግሞ የፍትህ ሚዛኗ ነው :

ፍትሕን በታማኝነት!!!

ቤተሰብ ይሁኑ!የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤትን የፌስቡክ ገፅ በመከተል አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ፈጥነው እንዲደርሶት ያድርጉ! ሊንኩን ይጫኑ 👇[https://www.facebook.com/p...
06/09/2026

ቤተሰብ ይሁኑ!
የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤትን የፌስቡክ ገፅ በመከተል አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ፈጥነው እንዲደርሶት ያድርጉ! ሊንኩን ይጫኑ 👇
[https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552](https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552)

West Dembiya Communication Gondar Ketema woreda court page East Dembiya Wereda Court ላይ አርማጭሆ ወረዳ ፍርድ ቤት/Lay Armachiho Woreda Court Page የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት /High Court Of Central Gondar Page Oromo Special Zone High Court East Gojjam Zone high court/የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት ምዕራብደምብያ ወረዳ ፍርድቤት Wondale Ayalew የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region Alie Endalkachew West denbiya woreda court Chilga woreda Court Page/ጭልጋ ወረዳ ፍርድ ቤት

 #አርብ |  ፍርድ ቤታችን በዚህ ሳምንት   👏 ሰላም ውድ የገፃችን ተከታዮች🙏   የምዕ/ ደም/ወ/ፍ/ ቤት የሚዲያ በባለፈው አርብ ዘገባችን ፍርድ ቤታችን በዚህ አመት በሚል አምድ የ2018...
04/09/2026

#አርብ | ፍርድ ቤታችን በዚህ ሳምንት

👏 ሰላም ውድ የገፃችን ተከታዮች🙏

የምዕ/ ደም/ወ/ፍ/ ቤት የሚዲያ በባለፈው አርብ ዘገባችን ፍርድ ቤታችን በዚህ አመት በሚል አምድ የ2018 ዓ.ም አበይት የስራ ክንውኖችን ይዘንላችሁ ቀርበን ነበር ። በዛሬው ፕሮግሮማችን ደግሞ ፍርድ ቤታችን በዚህ ሳምንት በሚለውን አምዳችን የሳምንቱን አበይት ስራዎች በአጭሩ ይዘን ቀርበናል::

ምንም እንኳን የዳኞች የእረፍት ጊዜ ቢሆንም ዳኞች በወረፋ እየገቡ ከአስተዳደር ሰራተኛው ጋር በመሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በክረምት እንዲሰሩ የፈቀደውን የጉዳይ አይነቶች እንደ ልጅ ቀለብ፣ ዋስትና እና የመሳሰሉትን መሰረት አድርገው በርካታ መዝገቦች እየሰሩ ይገኛሉ።
የክረምት የስራ ጫና መቀነሱን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ በዳታ ቤዝ አድምንስትሬሽን ባለሙያዎች በተደረገ ያላሰለሰ ጥረት ወደ CCMS ሲስተሙ እየተመዘገቡ ያሉት የቆዩ መዛግብቶች ብዛት በዚህ ሳምት ተጠናክሮ ቀጥሎ ከ2000 በላይ ሆኗል።
የፍርድ ቤቱ የሚዲያ ክንፍ ኮሜቴ የዘገባ ስራውን እና የየቀን የኦላይን ውይይቱን አጠናክሮ እየሰራ በየቀኑ በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ዘገባዎች እየተሰሩ ለገፃችን ተከታዮች እያደረሰ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት ማለትም ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ኮሜቴው በፍ/ቤቱ ፕሬዘዳት ሰብሳቢነት በአካል በመገናኘት 1ኛ/ የሚዲያ ስራውን ኮሜቴው ከጀመርን ጀምሮ ምን ትምህርት አገኘን ? ምንስ ችግር ገጠመን? እንዴትስ እናስተካክል ? 2ኛ/ ኮሜቴው የተሰጠውን ስራ በአግባቡ እየተወጣ ነው ወይ? በሚሉ በ2 አጀንዳዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጎ በውይይቱም ኮሜቴዎች በሚዲያ ስራው ጥሩ እውቀት እንዳገኙበት ገልፀው ሊስተካከሉ የሚገባቸውም ዘገባው ለአንባቢያን እንዳያሰለች አጠር ባለ ፅሁፍ ሰፊ ሀሳብ የማስተላለፍ ልምድ ማዳበር እንዳለብን እንዲሁም በ2ኛው አጀንዳ ላይ በኦላይን ውይይቱ ወቅት ሰአት የሚሸራርፉ ኮሜቴዎች ሰአት መከበር እንዳለበት ተወስኗል።
በመጨረሻም የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ጅማሮው መልካም እንደሆነ ገልፀው ወደፊት ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት አሳስበው ለኮሚቴዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው ስብሰባው ተጠናቋል።

ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት
ጯሂት
ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
#ተዘጋጀ:- በምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት ሚዲያ ክንፍ ኮሜቴ

❤️ #ይወዳጁን 👇

https://www.facebook.com/weste.denbiya

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት /High Court Of Central Gondar Page የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ West Dembiya Communication

04/09/2026

ምዕራብ ደምብያ ወረዳ ፍርድ ቤት ፍትሐ ብሔር መዝገብ ቤት አሁናዊ ገፅታ!!👇

 #ሀሙስ ዕርቅ ጠቀሜታ (ክፍል ሁለት) ውድ የገፃችን ቤተሰቦች፤ሰላም ለእናንተ ይሁን!የምዕራብ ደ/ወ/ፍ/ቤት የሚዳያ ክንፍ ኮሚቴ በዛሬው  አምዱ ባለፈው ዝግጅታችን 'ስለ ዕርቅ ጠቀሜታ' ሰፋ...
03/09/2026

#ሀሙስ ዕርቅ ጠቀሜታ (ክፍል ሁለት)

ውድ የገፃችን ቤተሰቦች፤ሰላም ለእናንተ ይሁን!የምዕራብ ደ/ወ/ፍ/ቤት የሚዳያ ክንፍ ኮሚቴ በዛሬው አምዱ ባለፈው ዝግጅታችን 'ስለ ዕርቅ ጠቀሜታ' ሰፋ ያለ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የዚሁ ዘገባችን ቀጣይ ክፍል የሆነውን ዘመናዊው የፍርድ ቤት ሒደትና አገር በቀሉ የዕርቅ ስርዓት፣ በሰው ልጆች ማህበራዊ ግንኙነት ላይ ያላቸውን ትልቅ ልዩነት ይዘንላችሁ ቀርበናል።

በህይወት ጎዳናችን ላይ አለመግባባቶች መፈጠራቸው አይቀርም። እነዚህን አለመግባባቶች ለመፍታት ወደ ፍርድ ቤት ደጃፍ ስናመራ፣ ብዙ ጊዜ ሂደቱ ቀለል ያለ አይሆንም። ተከራካሪዎች ለዓመታት የገነቡትን አብሮነት ዘንግተው፣ ፊት ለፊት ተካርረው ይቆማሉ። የፍርድ ቤት ሂደት ጊዜ ይወስዳል፣ ወጪ ይጠይቃል፤ ከምንም በላይ ደግሞ የሰዎችን ልብ ያደክማል።
ዳኞች ውሳኔ የሚሰጡት በማንነት፣ በስሜት ወይም በማህበራዊ ትስስር ላይ ሳይሆን፤ በቀረበላቸው ደረቅ ማስረጃ እና በህግ አንቀፅ ላይ ብቻ ተመስርተው ነው። በዚህም በወረቀት ላይ ፍትህ ይሰፍን ይሆናል። ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን አንዱ አሸናፊ፣ ሌላኛው ደግሞ ተሸናፊ መሆኑ አይቀርም።ህጋዊ መብትም ተከብሮ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የዘመናት አብሮነት ይቋረጣል። በልብ ውስጥ የተቋጠረው ማህበራዊ ቂም እና ቁርሾ በቀላሉ አይጠፋም፤ ሰዎቹ መንገድ ላይ ሲገናኙ ዞሮ ማየት፣ በሰርግና በሀዘን መረዳዳት፣ አብሮ መብላትም ያቆማሉ።
ወደ ማህበረሰባችን ጥልቅ የዕርቅ ሥነ-ሥርዓት ስንመጣ ግን፣ ታሪኩ ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል። የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በመሃል ሲቆሙ የጥፋተኝነት ጣት ከመቀሰር እና ህግ ከመምዘዝ ይልቅ፣ የይቅርታ እና የፍቅር መንፈስ ይነግሳል። የሚደረግ ክርክር የለም፣ ልብን የሚጠግን መደማመጥ አለ። አባቶች የሁለቱንም ወገን የልብ ስብራት፣ ብሶት እና እሮሮ በእርጋታ ያዳምጣሉ።
ከዚያም፣ የሁለቱም ወገን ልብ ሲረጋጋ፣ 'ይቅር ለፈጣሪ' በሚለው ኃያል እና መንፈሳዊ ቃል፣ የጠነከረው ልብ ይለዝባል። በእኛ አገር በቀል የዕርቅ ስርዓት ውስጥ አንዱን ጥሎ ሌላውን ማዳን፣ ወይም አንዱን አሸናፊ ሌላውን ተሸናፊ ማድረግ የሚባል ነገር የለም። ማህበራዊ ሰላም ስለሚወርድ፣ ሁለቱም ወገኖች አሸናፊዎች ናቸው።
ከዕርቁ በኋላ ቂም አይቀርም፣ ቁርሾ አይታሰብም። በእንባ ታጥቦ፣ ተቃቅፎ ማልቀስ፣ ከልብ ይቅር መባባል እና የተቋረጠውን አብሮነት ዳግም ማደስ ይቀጥላል።
ፍርድ ቤት መብትን ሲያስከብር፣ ዕርቅ ደግሞ አብሮነትን ያድሳል። ችሎት ግለሰብን በህግ ሲቀጣ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ደግሞ ልብን በፍቅር ያሸንፋሉ። የተበጠሰው የማህበራዊ ትስስር ክር፣ በእንባ ታጥቦ እንደገና አምሮ የሚገመደው... ከችሎቱ መዶሻ ይልቅ በሽማግሌዎቹ ምርቃት ነው! ሰለዚህ
ዘመናዊው የህግ ስርዓታችንም ቢሆን፣ ይህንን አገር በቀል የዕርቅ ስርዓት አጥብቆ የሚደግፈውና የሚያበረታታው ለዚሁ ነው።

ነሀሴ 28 ቀን 2018ዓ/ም
ጯሂት
"ፍትህን በታማኝነት!"

እርሶም ሀሳብ አስተያየትዎን በኮሜንት መስጫው ላይ ያካፍሉን
የፌስቡክ ገፃችን ላይክና ሸር በማድረግ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ፦

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት /High Court Of Central Gondar Page የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region East Dembiya Wereda Court @

ከሕጎቹ ባሻገር  ባህልና ወግን ያማከሉ በርካታ ገንቢ ግንዛቤዎችን ያስጨበጠ ስልጠና እና ግምገማ ነበርእናመሰግናለን ክቡራን 🙏🙏🙏
03/09/2026

ከሕጎቹ ባሻገር ባህልና ወግን ያማከሉ በርካታ ገንቢ ግንዛቤዎችን ያስጨበጠ ስልጠና እና ግምገማ ነበር
እናመሰግናለን ክቡራን 🙏🙏🙏

🙏🙏🙏👇
02/09/2026

🙏🙏🙏👇

የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት ህዝብ ግንኙነት (የሚዲያ ክንፍ) #ማክሰኞ:- ምን እናስተካክልልዎ?     (የምልከታ ዘገባ - ክፍል 2)  ​ውድ የገጻችን ቤተሰቦች፣ እንደምን ሰነበታችሁ!...
01/09/2026

የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት ህዝብ ግንኙነት (የሚዲያ ክንፍ)

#ማክሰኞ:- ምን እናስተካክልልዎ?

(የምልከታ ዘገባ - ክፍል 2)

​ውድ የገጻችን ቤተሰቦች፣ እንደምን ሰነበታችሁ!

የምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት ሚዲያ ክንፍ እውነተኛ ለውጥ የሚጀምረው የራስን ክፍተት በድፍረት አምኖ ከመቀበል እና ለማስተካከል ከመትጋት ነው !!! የሚል መርህን አንግቦ ፦

በፍርድ ቤቱ ICT የስራ ሂደት (ዳታ አድሚኒስትሬሽን) ላይ ያደረገውን የውስጥ ምልከታ እና ዳሰሳ ይዞላችሁ ቀርቧል።

​በጉብኝታችን ወቅት ከዳታ አድሚኒስትሬሽን ባለሙያዎች (ወ/ሪት የመንግስት ዳኘው እና ወ/ሮ ታሪክ ባዘዘው) ጋር ባደረግነው ቆይታ፣ መረጃን በአግባቡ ለመያዝ እና የቆዩ መዛግብትን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዳታቤዝ (CCMS) በማስገባት ህዝብን በቅንነት ለማገልገል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተመልከተናል።
ሆኖም ለስራው እንቅፋት የሆኑ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግዳሮቶች ተለይተዋል፦

​⚠️ ያጋጠሙ ዋና ዋና ተግዳሮቶች፦
1ኛ:- ​የመብራት መቆራረጥ፦ በክረምት እረፍት ወቅት ከ2000 እስከ 2004 ዓ.ም የነበሩ መዛግብትን ለይቶ ወደ ዳታቤዝ ለማስገባት በሁለት ባለሙያዎች ስራ ቢጀመርም፣ ተደጋጋሚ የመብራት መጥፋት ስራውን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ለማጠናቀቅ ፈታኝ ሆኗል።

2ኛ:- ​የመዛግብት ሁኔታ፦ መዛግብቱ ለ13-18 ዓመታት በቢሮ ጥበት ምክንያት ባልተገባ ቦታ ታሽገው የቆዩ በመሆናቸው፣ በምዝገባ ወቅት አየር የመታመቅ እና ደስ የማይል ሽታ ችግር ፈጥረዋል።

3ኛ:- ​የቢሮ እና የዕቃዎች ማረጃት፦ የICT ክፍሉ ያረጀ በመሆኑ ኮምፒውተሮችን ከአቧራ መከላከል አለመቻሉ እና በቫይረስ መጠቃት የአገልግሎት ጥራቱ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

4ኛ:- በባለሙያዎች የተጠቆሙ የመፍትሔ ሃሳቦች፦
​ተቋሙ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመነጋገር የነዳጅ አቅርቦት በማመቻቸት፣ መብራት በሚጠፋበት ጊዜ ጀነሬተር መጠቀም ከተቻለ መዛግብቱን በታቀደው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት መመዝገብ ይቻላል።

​የሚመለከተው አካል መረጃ የፍርድ ቤቱ ዋና ሀብት መሆኑን በመረዳት ለተቋሙ ገጽታ ግንባታ እና ለማቴሪያል እጥረት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
​ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
ጯሂት

⚖️ "ፍትሕን በታማኝነት!"

​👇 እርሶም ሀሳብ አስተያየትዎን በኮሜንት መስጫው ላይ ያካፍሉን!

​🔗 የፌስቡክ ገጻችንን Like እና Follow በማድረግ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ፦

ይህ የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት የፌስቡክ ገፅ ሊንክ ነው ገፁን በመከተል ቤተሰብ በመሆን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶዎ ያድርጉ!
👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552

​(ማስታወሻ፡ በፍትሐብሔር የስራ ሂደት ላይ የተጀመረው ዘገባ በሌላ ጊዜ ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል!)

በጣም ጥሩ ግምገማና ብዙ አሰሪ አቅጣጫዎች የተሰጡበት ጉባኤ ነው 🙏🙏🙏💯✔️
01/09/2026

በጣም ጥሩ ግምገማና ብዙ አሰሪ አቅጣጫዎች የተሰጡበት ጉባኤ ነው 🙏🙏🙏💯✔️

 #ሰኞ:- እኛን እናስተዋውቅዎ (ክፍል ሁለት)የፍርድ ቤታችን መዋቅር እና ወደ እኛ ሲመጡ ማወቅ ያለብዎ ነጥቦች!ሰላም ውድ የገፃችን ቤተሰቦች! ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ምን ማለት እንደሆነ...
31/08/2026

#ሰኞ:- እኛን እናስተዋውቅዎ (ክፍል ሁለት)

የፍርድ ቤታችን መዋቅር እና ወደ እኛ ሲመጡ ማወቅ ያለብዎ ነጥቦች!

ሰላም ውድ የገፃችን ቤተሰቦች! ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ምን ማለት እንደሆነ እና መርሆቻችንን ተመልክተናል። ዛሬ ደግሞ የፍርድ ቤቶቻችንን አደረጃጀት እና ወደኛ ሲመጡ ማወቅ ስለሚገቧችሁ ጉዳዮች በአጭሩ እናወራለን።

# የፍርድ ቤቶቻችን መዋቅር፦
ፍትህ ለህዝብ ቅርብ እንዲሆን ፍርድ ቤቶቻችን በሶስት ይከፈላሉ፦
የወረዳ ፍርድ ቤቶች፡-ለህብረተሰቡ ቅርብ የሆኑና መሰረታዊ ጉዳዮችን በመጀመሪያ ደረጃ የሚያዩ የፍትህ በሮቻችን ናቸው።
የከፍተኛ ፍርድ ቤቶች፡- ከባድ የህግ ጉዳዮችን እና ከወረዳ ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚመጡ አቤቱታዎችን መርምረው ውሳኔ ይሰጣሉ።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፡- በክልሉ ከፍተኛው የዳኝነት አካል ሲሆን፣ የመጨረሻ ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታዎችን ይመረምራል።

#ወደ ፍርድ ቤታችን ሲመጡ ይህንን ልብ ይበሉ፦
1.ከደላሎች ይራቁ!
ፍትህ አይሸጥም አይገዛምና ጉዳይዎን ለማስፈፀም ማንም ሰው ገንዘብ ቢጠይቅዎ ወዲያውኑ ይጠቁሙ። ትክክለኛውን መረጃ ከመረጃ ጠያቂዎቻችን ብቻ ያግኙ።
2.ማስረጃዎን ያደራጁ፡-
ፍርድ ቤት የሚሰራው በማስረጃ እና በህግ ብቻ ስለሆነ፤ አቤቱታዎን ሲያቀርቡ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃዎችዎን አሟልተው ይቅረቡ።
3.ክስም ሆነ መልስ ከማቅረብዎ በፊት ከተቻለ የሕግ ባለሙያ አቅም ከሌለና ካልተቻለ የፍርድ ቤት ልምድ ያለው ሰው ቢያማክሩ እጅግ ውጤታማ ይሆናል::
@ እስከ ሳምንት ቸር እንሰንብት🙏🙏🙏
ቀጣይ ስንገናኝ ክፍል ሶስትን ይዘን የምንመለስ ይሆናል ::

"ፍትሕን በታማኝነት!"

ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
ጯሂት

**ቤተሰብ ይሁኑ!
የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤትን የፌስቡክ ገፅ በመከተል አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ፈጥነው እንዲደርሶት ያድርጉ! ሊንኩን ይጫኑ 👇
[https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552](https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552)

29/08/2026

Address

ምዕራብ ደምብያ :-ጯሂት
Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West denbiya woreda court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share