03/09/2026
በጎንደር ከተማ በማራኪ ክፍለ ከተማ ሲቪ አር ፕሮጀክት ለ53 ተማሪዎች ለአካል ጉዳተኞች የትምህርት ቁሣቁስ ደብተር ድጋፍ አደረገ።
በጎንደር ከተማ ማራኪ ክፍለ ከተማ ሲቪ አር ፕሮጀክት ለ53 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ፕሮጀክቱ በተማሪዎቹ የትምህርት ተሳትፎና የመማር ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ቁሳዊ ችግሮችን ለማቃለል ያደረገው ድጋፍ ደብተርን ጨምሮ የትምህርት ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።
የድጋፉ ዓላማ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የመማር ዕድል እንዲያገኙ፣ በትምህርታቸው እንዲበረታቱና የትምህርት ህልማቸውን እንዲያሳኩ ማገዝ መሆኑ ተገልጿል።
ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን የሚደረጉ እንዲህ ያሉ ድጋፎች ማኅበራዊ አካታችነትን ከማጠናከር ባለፈ፣ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በችግሮች ሳይሸነፉ በትምህርት ላይ እንዲቆዩ የሚያበረታቱ ናቸው።
“ማንም ተማሪ በቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት መራቅ የለበትም” የሚል መርህን በመከተል፣ የተማሪዎቹን ትምህርታዊ ተስፋ ለማጠናከር የሚደረጉ ድጋፎች እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።