አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ

አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት  የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ this website was created to show every activities that are working in our livestock sector at adagn ager chako district

29/08/2026
🇪🇹🇪🇹✍️የአማራ ክልል አመራር አንድነት ከትናንት ስህተት የተማረና በሴራ የማይሸረሸር ጠንካራ አለት ነው✍️ታሪክ አላፊ ቢሆንም፣ ከእውነትና ከጽናት የሚመነጨው አሻራ ግን ዘላቂ ነው። በቀደሙ...
21/08/2026

🇪🇹🇪🇹✍️የአማራ ክልል አመራር አንድነት ከትናንት ስህተት የተማረና በሴራ የማይሸረሸር ጠንካራ አለት ነው

✍️ታሪክ አላፊ ቢሆንም፣ ከእውነትና ከጽናት የሚመነጨው አሻራ ግን ዘላቂ ነው። በቀደሙት ወቅቶች አመራሩን እርስ በርሱ እንዳይተማመን ለማድረግ፣ ከሕዝቡ ለማራቅና የተለያዩ እኩይ ፍላጎቶችን ለማስፈጸም የተከተሉ የመከፋፈልና የሴራ ፖለቲካ ስልቶች በግልጽ ይታወሳሉ። የዚህ ታሪክ ትልቁ ትምህርት ደግሞ ሕዝብንና አመራርን ለመለያየት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ በመጨረሻ የማይዘልቅ መሆኑ ነው።

ዛሬም የትናንቱን የተከፋፋይነት ስልት በመድገም፣ ከእውነት የራቀ መረጃና ፕሮፓጋንዳ በመንዛት የሕዝቡንና የክልሉን አመራር አንድነት ለማላላት የሚደረጉ ሙከራዎች የተለየ ውጤት አያመጡም። የቀድሞ የመከፋፈል ስልቶችን በመጠቀም የክልሉን አመራር አንድነት ማፍረስ ይቻላል ብሎ ማሰብም የፖለቲካ እውነታን ያላገናዘበ ስሌት ነው።

የአማራ ክልል አመራር ከትናንት ውድቀቶችና ስህተቶች የተማረ፣ የታሪክን ትምህርት በአግባቡ የተቀበለና ለሴራ የማይበረከክ አመራር ነው። አመራሩ በእውነት፣ በሕዝብ አመኔታና በጋራ ዓላማ ላይ የተመሠረተ አንድነት ያለው ሲሆን፣ ለሕዝቡ ሰላም፣ ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በትጋት የሚሠራ ነው። ስለሆነም ከእውነት የራቀ ወሬና ሐሰተኛ መረጃ በመንዛት አመራሩን ከሕዝቡ ወይም እርስ በርሱ ለማራራቅ የሚደረገው ሙከራ የሚያስገኘው ውጤት የለም።

በመሆኑም መላው ሕዝባችን የአመራሩ አንድነትና ትብብር ለክልላችን ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና መሠረት መሆኑን በመገንዘብ የመከፋፈልና የሴራ ፖለቲካን ከመቀበል መቆጠብ ይገባል። ትናንት ያልሠራው የመከፋፈል ስልት ዛሬም አይሠራም። የአማራ ክልል አመራርና ሕዝብ አንድነት በሴራ አይሸረሸርም፤ በሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳም አይናጋም።

✍️አንድነታችን የጥንካሬያችን፣ ሕብረታችን ደግሞ የድላችን መሠረት ሆኖ ይቀጥላል።

‎በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ የተሳካ የእንስሳት ክትባት ተሰጠ።‎🐄🐑🐃🐐🐂🐏🐄‎ቀን:10/12/2018  ዓ/ም‎በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች የእንስሳትን ጤንነት ለመጠበቅ እና የአርሶ ...
16/08/2026

‎በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ የተሳካ የእንስሳት ክትባት ተሰጠ።
‎🐄🐑🐃🐐🐂🐏🐄
‎ቀን:10/12/2018 ዓ/ም

‎በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች የእንስሳትን ጤንነት ለመጠበቅ እና የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ሰፊ የክትባት ዘመቻ መካሄድ ጀመረ።

‎በዚህም በእንስሳት ላይ ድንገተኛ ህልፈት እና ከፍተኛ የምርት መቀነስ ሊያስከትሉ ለሚችሉት **የአጉረብርብ እና የጎሮርሳ** በሽታዎች መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።

‎አርሶ አደሩ በቀጣይም እንስሳቱን በወቅቱ በማስከተብ ከሀብቱ ማግኘት የሚገባውን ሙሉ ጥቅም ያለምንም ስጋት እንዲያገኝ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

‎**መረጃው፡ የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት

‎🐄🐑🐃🐐🐂🐏🐄

16/08/2026
‎‎✍️በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ማህበረሰቡ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው የነበረው የእንስሳት ዝርያ ማዳቀል (Artificial Insemination - AI) አገልግሎት በይፋ ተጀመረ።‎‎✍️የምዕራብ ...
14/08/2026

‎‎✍️በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ማህበረሰቡ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው የነበረው የእንስሳት ዝርያ ማዳቀል (Artificial Insemination - AI) አገልግሎት በይፋ ተጀመረ።

‎✍️የምዕራብ ጎንደር ዞን እንሰሳት እና ዓሳ ሃብት መምሪያ ከክልሉ እንሰሳት እና ዓሳ ሀብት ቢሮ ጋር በመነጋገር ከባለሙያ ማሰልጠን ጀምሮ ለእንሰሳት ዝርያ የማዳቀል/Artificial Insemination - AI) ስራ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሟላት በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ የማህበረሰቡን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ ወደ ስራ ገብቷል።

የአርሶ አደሩን የወተት ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ፣ የተሻሻሉ የውጭ ደም (Exotic blood) ያላቸውን የእንስሳት ቁጥር ለመጨመር፣ እንዲሁም ይህንን የዝርያ ማዳቀል ስራ በቀጣይ ወደ ሌሎች የወረዳው ቀበሌዎች በስፋት ለማድረስ ታቅዷል።

✍️‎መረጃው የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት ነው።

ቀን:08/12/2018 ዓ/ም

08/08/2026
🌿 ዝሆኔ ሳር (Elephant Grass / Napier Grass)ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ ዘላቂ የመኖ ሳር👉 ዝሆኔ ሳር (Elephant Grass) ለብዙ ዓመታት የሚቆይ፣ ከፍተኛ የመኖ ምርት የሚ...
08/08/2026

🌿 ዝሆኔ ሳር (Elephant Grass / Napier Grass)

ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ ዘላቂ የመኖ ሳር

👉 ዝሆኔ ሳር (Elephant Grass) ለብዙ ዓመታት የሚቆይ፣ ከፍተኛ የመኖ ምርት የሚሰጥና ለከብት፣ ለበግና ለፍየል በጣም ተመራጭ የሆነ የመኖ ሳር ነው።
✅ ተስማሚ የአየር ሁኔታ
• በቆላማ አካባቢዎች በዝናብና በመስኖ በጥሩ ሁኔታ ያድጋል።
• አንዳንድ ዝርያዎች በደጋ አካባቢም ይበቅላሉ፤ ሆኖም ውርጭ ሊጎዳቸው ይችላል።
🌱 አባዛት
• በዘር አይባዛም።
• ከአገዳው (Stem cuttings) ወይም ከሥር ግንጣይ (Root splits) በቀላሉ ይተከላል።
📏 የመትከል ርቀት
• 1 ሜትር በመስመር መካከል።
• 30–50 ሴ.ሜ በተክል መካከል።
🌾 ማዳበሪያ
• በመትከል ወቅት 100 ኪ.ግ DAP በሄክታር ወይም በቂ የእንስሳት ፍግ መጨመር ይመከራል።
• ከሁለተኛው ዓመት ጀምሮ በየዓመቱ ፍግና ሌሎች ማዳበሪያዎችን እንደ አፈር ሁኔታ መጨመር የምርት መጠንን ያሳድጋል።
🌿 ከሌሎች የመኖ ተክሎች ጋር መቀላቀል
ዝሆኔ ሳርን ከዲስሞዲየም (Desmodium) ጋር በመቀላቀል መዝራት የመኖውን ጥራትና የፕሮቲን መጠን ያሻሽላል።
🌱 አረም ቁጥጥር
• በተለይ ከእያንዳንዱ አጨዳ በኋላ ማረምና ማኮተኮት የምርት መጠንን ይጨምራል።
✂️ የመኖ አጨዳ
• ቁመቱ 1–1.5 ሜትር ሲደርስ ማጨድ ይመከራል።
• በዚህ ወቅት የመኖው ጥራትና ምርት ከፍተኛ ይሆናል።
🐄 አጠቃቀም
• አረንጓዴውን በቀጥታ በማጨድ ለእንስሳት መመገብ ይቻላል።
• እንዲሁም ሳይሌጅ (Silage) በማዘጋጀት ለደረቅ ወቅት ማከማቸት ይቻላል።
📊 የመኖ ጥራትና ምርታማነት
✅ ከ9% በላይ የፕሮቲን ይዘት አለው።
✅ በዝናብ ሁኔታ 10–30 ቶን የደረቅ መኖ በሄክታር ሊሰጥ ይችላል።
✅ በመስኖ ከዚህ በላይ ከፍተኛ ምርት ይሰጣል።
🌿 ዝሆኔ ሳር በትክክል ከተመራ ለእንስሳት ቀጣይነት ያለውን ጥራት ያለው መኖ በማቅረብ የእንስሳት ምርታማነትን በእጅጉ ያሳድጋል።
📚 ምንጭ: Climate Smart Feed and Forage Innovations Training Workshop ከተዘጋጀ ሰነድ የተወሰደ።

27/07/2026
🐂🐃🐄🐐🐑🐓የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ቢሮ በምዕራብ ጎንደር ዞን ያካሄደው የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት የመስክ ድጋፍና ሱፐርቪዥን በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያበረታታ ተግባር ነው።...
27/07/2026

🐂🐃🐄🐐🐑🐓የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ቢሮ በምዕራብ ጎንደር ዞን ያካሄደው የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት የመስክ ድጋፍና ሱፐርቪዥን በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያበረታታ ተግባር ነው።
🐂🐐🐑🐄🐓🐃🐂በመስክ የተሰጠው ቴክኒካል ድጋፍ፣ የተደረገው ግምገማ እና የተቀመጡት አቅጣጫዎች በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ውጤታማነትን የሚያሳድጉ ናቸው።
🐄🐐🐑🐓🐂🐃በተቀናጀ አሰራር፣ በችግር ፈቺ ድጋፍ እና በቀጣይነት በሚደረግ ሱፐርቪዥን የእንስሳት ሀብታችንን ወደ ከፍተኛ ምርታማነት ማሸጋገር እንችላለን። በርቱልን🙏🙏

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ:

Shortcuts

Share