25/08/2026
በአማራ ክልል ፕላን ኢንስቲቱዩት ባለሙያዎች የዳንሻ ከተማ አስተዳደር የተሰራውን የስትራቴጅክ ፕላን በሰነድ ቀረበ።
ዳንሻ ፦ነሀሴ 19/2018 ዓ/ም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዳንሻ ከተማ አስተዳደር የክልሉ ፕላን ኢንስቲቱዩት ባለሙያዎች የዳንሻ ከተማ አስተዳደር የተሰራውን የእስትራቴጅክ ፕላን የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አደራጀው ዋኘው ፣የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ማሩ እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮሮች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የስትራቴጅክ ፕላኑን አጥንተው ለውይይት ያቀረቡት የክልሉ የፕላን ኢንስቲቱዩት ባለሙያ የሆኑት አቶ ምናላቸው ታየ እንዲሁም የኢኮኖሚ ጥናት ባለሙያ የሆኑት አቶ ምስጋናው ብርሀኑ በጋራ በመሆን ሲሆነ የከተማዋን ታሪካዊ አመሰራረት እና ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥንም መሰረት በማድረግ ጥናቱ ቀርቧል።
የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ታሪካዊ አመሰራረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ የምትገኝ ከተማ ስትሆን በርሀማውንና ደጋማውን አካባቢ የምታገናኝና በደረቅ ወደብነት የምታገለግል ከተማ ናት።
ከተማ አስተዳደሩ በጠገዴ ወረዳ ስር የምትገኝና ከአዲስ አበባ 900 ኪሎ ሜትር ርቀት እንዲሁም ከክልሉ ርዕሰ መዲና ባህርዳር በ335 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደምትገኝ ጥናቱ ይገልፃል።
ከተማዋ አስካሁን የሁለት ጊዜ የፕላን ዘመን እንዳሳለፈች በማንሳት የመጀመሪያው ፕላን በ1995 ዓ/ም የተሰራ የእድገት ፕላንና ለሁለተኛ ጊዜ የተሰራው ደግሞ በ2005 ዓ/ም በ677.18 ሄክታር የእስትራክቸር ፕላን እንደተሰራላት ጥናቱ አመላክቷል።
አሁን ላይ ለ3ኛ ጊዜ የሚሰራው የስትራቴጅክ ፕላን 4710 ሄክታር ስፋት ያለውና 26,649 በላይ ህዝብ የያዘና በፕላን አመቱ መጨረሻ ከ40,506 የሚደርስ ህብረተሰብን ታሳቢ በማድረግ ፕላኑ መሰራቱን ገልጾ በተጨማሪም ስትራቴጅክ ፕላኑ ሲሰራ ተፈፃሚ የሚሆነው በሰፈር ልማት ፕላን እንደሆነ ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል ሲሉ አጥኝዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲሱ የማስተር ፕላን ጥናት ተጠናቆ መሬት ላይ በሚወርድበት ወቅት ከተማዋን አዲስ ገፅታ ከማላበስ በተጨማሪ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በቁጥር እስከመጨመርና ጥራታቸውንም በዛው ለክ እንደሚያመጣ በባለሙያዎች ተብራርቷል።
ለጥናቱ አስቻይ ሁኔታ የሚነሳው የከተማዋም ሆነ የዙሪያው ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ የእንስሳትና የተፈጥሮ ሀብት፣ ሊታረስ የሚችል ሰፊ የእርሻ መሬት ፣ ሰፊ የሆነ የሰው ሀይል አቅምና መልካም የሆነ የስራ ባህሪ የተላበሰ ማህበረሰብ መኖሩ በተጨማሪም የዞኑ የግብርና ኢኮኖሚ እቅስቃሴ ማዕከል መሆኗ አስቻይ ሁኔታ እንደሚያደርገው ተገልፆል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው ማስተር ፕላኑ እንዳዲስ መሻሻሉ እንደመልካም ያኑሱ ሲሆን በመሻሻሉ ላይ የቦታዎች ስያሜ ወጥ የሆነና የፊደል ግድፈት ሳይኖራቸው እንዲሰሩና በተጨማሪም የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት እንደሆነም በማስተር ፕላኑ ላይ እንዴታወቅ ሲሉ ሀሳባቸውን አንስተዋል።