Ebinat Industry & Investment office

Ebinat Industry & Investment office Addres :- Ebinat woreda kebele :- 02 with in ORDA office

02/08/2023
በእብናት ወረዳ የማዕድን ሀብት ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ የእብናት ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ ወንድሙ እንደገለፁት የአብክመ ማዕድን ሀብት ልማት ...
23/06/2023

በእብናት ወረዳ የማዕድን ሀብት ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ
የእብናት ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ ወንድሙ እንደገለፁት
የአብክመ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ጂኦሎጅ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር በእብናት ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች በመዘዋወር የማዕድን ጥናትና የምርመራ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል ::

በወረዳችን የተለያዩ የማዕድን ፀጋዎች እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ያሉትን ማዕድናት ወደስራ ለማስገባት በተደረገ ጥረት አንድ የግራናይት ማዕድን የማምረት ስራ ፈቃድና አንድ የግራናይት ማዕድን የምርመራ ስራ ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ይገኛሉ ሲሉ ኃላፊው ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

አቶ አሰፋ አክለውም ከዚህ በፊት በተቋሙ ባለሙያዎች በተደረገ የማዕድን አሰሳና ቅኝት የተገኙትን ማዕድናት ለክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት በሮ ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት ሀብቱን እያስጠናን ስለሆነ ማንኛውም አካል በወረዳችን ሁሉም ቀበሌዎችና ጎጦች አሉ የሚባሉ ወይም የማዕድን ይዘት ይኖራቸዋል ብላችሁ የምትጠረጥሩትን አፈር ፣ ድንጋይም ሆነ ፈሳሽ ነገሮች ጥቆማ እንድትሰጡን እየጠየቅን የወረዳችን እምቅ ሀብት በጥናት በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል ለምናደርገው ጥረት ከጎናችን ስለሆናችሁ በቅድሚያ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል ።

ጥቆማ መስጠት ለምትፈልጉ
በአካል ጽ/ቤታችን ድረስ ሳምፕልሎችን ማምጣት ወይም በአካል ማዕድኑ ካለበት ቦታ ድረስ መውሰድ ለምትፈልጉ ጽ/ቤታችን አመልድ ኢትዮጵያ ግቢ ነው
እንዲሁም
በተቋማችን የፌስቡክ ገፅ - Ebinat industry & investment office
በኢሜል አድራሻ - [email protected]
በስልክ ቁጥር :-
0584400789/0584400833
+251918093496/+251918214343
ማሳወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን
''ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለወረዳችን !!''
16/10/2015 ዓ.ም
እብናት

የደቡብ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በ2015 በጀት አመት የ7 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በክልሉ ካሉት ዞኖች ሲነፃፀር ዞኑ ላሳየው ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢና የተሻለ...
25/02/2023

የደቡብ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በ2015 በጀት አመት የ7 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በክልሉ ካሉት ዞኖች ሲነፃፀር ዞኑ ላሳየው ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢና የተሻለ አፈፃፀም ምስጋና እና ዕውቅና ተሰጠው፤

ዛሬ በባህርዳር ከተማ "ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ የንቅናቄ መድረክም የደቡብ ጎንደር ዞን የኢንዱስትሪና አመንቨስትመንት መምሪያ በ2015 በጀት ዓመት መሬት በማዘጋጀት፣ ፕሮጀክቶችን ወደ አፈፃፀም በማስገባትና የዘርፉን ማነቆዎች ተከታትሎ በመፍታት ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ በመፍጠር ለአሳየው ከፍተኛ መነሳሳት የምስክር ወረቀት ከታላቅ አክብሮት ጋር ተበርክቶለታል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለ4ኛ ዙር ሠልጣኞች የምዝገባ ቀናትን ማራዘሙን አስታውቋል‼️የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ለ4ኛ ዙር ላዘጋጀው ሥልጠና የሚያ...
25/01/2023

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለ4ኛ ዙር ሠልጣኞች የምዝገባ ቀናትን ማራዘሙን አስታውቋል‼️

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ለ4ኛ ዙር ላዘጋጀው ሥልጠና የሚያካሄደውን የምዝገባ ጊዜ ማራዘሙን አስተውቋል፡፡

ለሥልጠናው ፍላጎት ያሳዩ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ፣ በየቅርንጫፎቹ የታየው የተመዝጋቢዎች መጉላላትን ለማስቀረት፣ ተጨማሪ ተመዝጋቢዎችንም ለማካተት እና በሚፈለገው መልኩ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ፣ ምዝገባውን በእርጋታ ለማካሄድ ይቻል ዘንድ እስከ መጪው እሑድ ጥር 21 ቀን 2015 ድረስ ምዝገባው ለ4 ተከታታይ ቀናት ማራዘሙን የባንኩ ማኔጅመንት አስተውቋል፡፡

በመሆኑም ተመዝጋቢዎች በቀሪዎቹ ቀናት ተረጋግተው ምዝገባቸውን እንዲያካሂዱ ባንኩ አሳስቧል፡፡ ይህንኑ በማስፈጸም ላይ ላሉ የባንኩ ቅርንጫፎችም መመሪያ መተላላፉ ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

ልዩ የስልጠና ዕድል ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ 1. በአራተኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው ስልጠና ለመሳተፍ ምዝገባ   እስከ ጥር 16/2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያ...
23/01/2023

ልዩ የስልጠና ዕድል ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ

1. በአራተኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው ስልጠና ለመሳተፍ ምዝገባ እስከ ጥር 16/2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

2. ምዝገባ የሚካሄደው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ነው

3. ምዝገባውን በሚቀርባችሁ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ መመዝገብ ይቻላል

4. ለምዝገባ የወጡ መስፈርቶች፣

4.1. ለስልጠና ለመመዝገብ ሲሄዱ ተመዝጋቢው ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ መያዝ አለበት

4.2 ስልጠና ፈላጊው ወይንም ህጋዊ ወኪሉ እራሱ በአካል ቀርቦ መመዝገብ አለበት

4.3 ሰልጣኞች የትምህርት ዝግጅታቸው ቢያንስ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም በቀድሞው የ10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወይም በአሁኑ የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብሎ በንግድ ስራ ላይ ቢያንስ ሶስት ዓመት ሲሰሩ የቆዩ ሆነው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ከቻሉ ስልጠናውን መውሰድ ይችላሉ

4.4. ለሰርተፍኬት ብቁ ለመሆን ሰልጣኙ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳያቋርጥ መሰልጠን ይጠበቅበታል፣

4.5 ከአሁን ቀደም በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ተመርቃችሁ በህብረት ስራ ኮሚሽን በኩል ምዝገባ ያካሄዳችሁ በሙሉ በአራተኛው ዙር ስልጠና መሳትፍ ይኖርባችኃል። በመሆኑም በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፎች በመገኘት እንድትመዘገቡ

4.6 ባንኩ በቀጣይ የሚሰጣቸውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመጠቀም የተዘጋጃችሁ እና የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሆናችሁ ስልጠና መውሰድ የምትፈልጉ በተመሳሳይ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፎች ሄዳችሁ በመመዝገብ በስልጠናው መሳተፍ ትችላላችሁ

Development Bank of Ethiopia

መሺ ፔትሮሊየም የነዳጅ ማደያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ !!በደቡብ ጎንደር አስ/ዞን በእብናት ወረዳ በ2013 ዓ.ም ክልሉ በሰጠው እድል መሰረት  መስፈርቱን አሟልተው ለነዳጅ ማደያ የሚሆኑ ቦ...
22/01/2023

መሺ ፔትሮሊየም የነዳጅ ማደያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ !!
በደቡብ ጎንደር አስ/ዞን በእብናት ወረዳ በ2013 ዓ.ም ክልሉ በሰጠው እድል መሰረት መስፈርቱን አሟልተው ለነዳጅ ማደያ የሚሆኑ ቦታዎችን ከተረከቡ 4 ባለሀብቶች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ማራቸው ሙጨ በጥር ወር 2015 ዓ.ም ግንባታቸውን ሙሉ በሙሉ አጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት አቶ ማራቸው ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ 5,000,000 ብር ወጭ ያደረጉ ሲሆን በተፈለገው ፍጥነት ለማጠናቀቅ የህልውና ዘመቻውና የግንባታ እቃዎች ዋጋ መናርና መጥፋት ማነቆ እንደነበረ አውስተዋል
አቶ ማራቸው ይህ ፕሮጀክት ተጠናቆ አልግሎት እንዲሰጥ በህብረተሰቡ እና በየደረጃው ባሉ አመራሮች ለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ።
በመጨረሻም አቶ ማረ ድርጅታቸው በእብናት ከተማ ቀበሌ 02 ወደበለሳ መውጫ ከእንሳሳት ገበያው ፊትለፊት የሚገኝ ሲሆን 24 ስዓት ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አብስረውናል ።
''ኑ እብናትን በጋራ እናልማ!!''
መረጃው :-
የእብናት ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ነው
14/05/2015 ዓ.ም

የግራናይት ማዕድን ማምረቻ የመንገድ ቆረጣ ስራ ተጀመረ የእብናት ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በእብናት ወረዳ ደብር አባጃሌ ቀበሌ ለሚያከናውነው የግራናይት ማዕድን ማማምረት ስራ ...
16/01/2023

የግራናይት ማዕድን ማምረቻ የመንገድ ቆረጣ ስራ ተጀመረ
የእብናት ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በእብናት ወረዳ ደብር አባጃሌ ቀበሌ ለሚያከናውነው የግራናይት ማዕድን ማማምረት ስራ ከቦታው የሚያደርሰውን የመንገድ ቆረጣ ስራ ጀምሯል

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ለይኩን ተፈራ እንደገለፁት መንገዱ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና 3,500,000 ብር የሚገመት ወጭ የሚያስፈልገው ሲሆን ወጭው ሙሉ በሙሉ በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል ብለዋል።

ድርጅቱ ወደዚህ አካባቢ ዘልቆ ማልማት ሲጀመር ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን ይዞ እንደሚመጣ የገለፁት ስራ አስኪያጁ አካባቢው የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ ልማት እጥረት ያለበት በመሆኑ የመንገድ ጠረጋው የመጀመሪያውን ችግር ያቃልላል ያሉ ሲሆን በቀጣይ መብራት ለማስገባት እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት ለመገንባት ማቀዳቸውን ጭምር ገልፀውልናል

እዚህ አካባቢ መተን ስናለማ የተለየ ተጠቃሚ እንሆናለን ማለት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ባለሀብቶች በየአካባቢው የሚገኘውን ፀጋ/ሃብት በመለየት፣ በማጥናትና በማልማት እራሳቸውን ፣ አካባቢያቸውን ብሎም ሀገራቸውን መጥቀም እንዲችሉ ማነሳሳትና ልምድ እንዲቀስሙ ለማድረግ ጭምር ነው ብለዋል

በመጨረሻም አቶ ለይኩን ወደ ስራ እንድንገባ በደብር ቀበሌ መዋቅር ፣ በእብናት ወረዳ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ፣ በእብናት ወረዳ አስተዳደር ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደርና በክልሉ በኩል ለተደረገልን ቀልጣፋ መስተንግዶና ትብብር በድርጅቱና በአካባቢው ማህበረሰብ ስም ከልብ እናመሰግናለን ብለው
አካባቢያችን ባለብዙ ፀጋ ባለቤት ስለሆነች ኑ በጋራ እናልማ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የእብናት ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት
08/05/2015 ዓ.ም

Address

Wogagen
Gondar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251584400833

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ebinat Industry & Investment office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ebinat Industry & Investment office:

Share