25/10/2025
ወገን የህፃናት የእናቶች መረጃ ድርጅት ለ130 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች የገቢ ማስገኛ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ድርጅቱ ለ130 ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች የገቢ ማስገኛ ለእያንዳንዳቸው 10ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ።
የወገን ህፃናትና እናቶች መረጃ ድርጅት ስራ-አስኪያጅ ወይዘሮ ህብስት መኮነን እንደገለጹት ድርጀቱ በጤና፣ በንፁህ ውሃ አቅርቦት ፣ በትምህርት ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፈ ብዙ የማህበረሰቡን ችግር ፈች ድጋፍ እና በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ያለ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል ።
በዚህ ሳምንት ብቻ የበርካታ እናቶች እና እህቶች አስከፊ ችግር ለመቅረፍ እና መከላከል ይቻል ዘንድ ከተለያዩ የማዕከላዊ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ለተወጣጡ 32 የህክምና ባለሙያዎች ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በፊስቱላና ማህፀን መውጣት ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረጉን እና
ዛሬ ደግሞ በገቢ ማስገኛ ለተሰማሩ ለ130 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች ለእያንዳንዳቸው 10ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ።
በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ታሳቢ በማድረግ የህይወት ክህሎት ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል ።
በዚህ ዓመት 900 በላይ ለሚሆኑ እናቶች የገቢ ማስገኛ ለእያንዳንዳቸው ከ10ሺህ እሰከ 20 ሺህ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል ።
ወገን የህፃናት የእናቶች መረጃ ድርጅት የቦርድ አመራር ዶክተር አዳነ ከበደ በበኩላቸው ወገን በተለያዩ ስራዎችን በመስራት በርካታ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል ።
ለዛሬ ያደረገው ድጋፍ ለስራ መስሪያ በመሆኑ የንግድ ክህሎታቸውን በማዳበር ሁለትና ከዚያም በላይ በመቀናጀት ወይም በተናጠል ከተረጂነት ለመውጣት መስራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል ።
በመስራት መቆጠብ ለተሻለ ስራ ራስን ማዘጋጀት እንደሚገባም ገልፀው በጋራ ሆኖ በመስራት ክፍተቶች በመሙላት ሀብት ለመፍጠር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው አስርድተዋል ።
ካላችሁበት የኑሮ ዘቤ ለመወጣት በጋራ መስራት፣መደጋገፍ ፣መቆጠብ እና ሀብት በማፍራት በኢኮኖሚው ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ማስፋፊያ ቡድን መሪ አቶ ተከታይ ጫቅሉ ደግሞ ወገን በጎንደር ከተማ ለበርካታ ሴቶች ድጋፍ እያደረገ ያለ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል ።
ድርጅቱ ለበርካታ ሴቶች ፣ህፃናት ድጋፍ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በገቢ ማስገኛ ዝቀተኛ ገቢ ያላቸውን ድጋፍ በማድረግ በኑሮ ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል ።
ድጋፍ ለሚሹ የህብርተሰብ ከፍሎች ድርጀቱ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።
ድጋፍ የተደረገላቸው ለድርጅቱ ምስጋና አቅርበዋል ።