ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ኦፊስ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ኦፊስ

ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ኦፊስ ምዕ/ጎንደር ዞን ምዕ/አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

የአፋብን የሃብት ልማት ምክትል ኀላፊ በለጠ አዱኛ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ህዝቡ ተቀላቀለ። # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # ...
07/09/2026

የአፋብን የሃብት ልማት ምክትል ኀላፊ በለጠ አዱኛ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ህዝቡ ተቀላቀለ።
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
የአማራን ሕዝብ ወሰን እና ማንነት ጥያቄ አሳልፈው ላለመስጠት የሰላም አማራጭን መከተላቸውን የቀድሞ ታጣቂ መሪዎች ገለጹ።

በአማራ ሕዝብ የማንነት እና ወሰን ጥያቄ ስም የሚደረጉ የተሳሳቱ እንቅስቃሴዎችን በመቃወም የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሕዝቡ መቀላቀላቸውን በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአፋብን ከፍተኛ መሪዎች ተናግረዋል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በጫካ በተሳሳተ መንገድ መቆየታቸውን የጠቀሱት የአፋብን የሃብት ልማት ምክትል ኀላፊ በለጠ አዱኛ ወደ ጫካ የገቡት የሕዝብን ጥያቄዎች ለማስመለስ አልመው እንደነበር ጠቅሷል። ከዚህ አላማ በተቃራኒ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን እና የሕዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ አካሄድ በመኖሩ የመንግሥትን የሰላም አማራጭ መምረጣቸውን ገልጿል።

የእርስ በእርስ መገዳደል መፍትሔ እንደማያመጣ በመጠቆም ከመንግሥት ጋር በመኾን የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ቁርጠኛ መኾናቸውን አጋግጧል። ሌሎች ታጣቂዎችም ወደ ሰላም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

ለታጣቂዎቹ አቀባበል ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጌታቸው ሙሉጌታ እና የጠገዴ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ጋሻው ፍታለው የታጣቂዎቹን ውሳኔ አድንቀዋል።

መሪዎቹ በጫካ ያሉ አደረጃጀቶች የሕዝብን ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈም ሀገር ለማፍረስ እየሠሩ መኾኑን ተረድተው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለስ ሀገርን እና ሕዝብን የሚያስቀድም ትክክለኛ ውሳኔ መኾኑን ገልጸዋል።

#አሚኮ ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም

በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ጳጉሜን-2 "የማንሰራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ በአብርሃጅራ ከተማ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በመጎብኘት ተከበረ።"ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰ...
07/09/2026

በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ጳጉሜን-2 "የማንሰራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ በአብርሃጅራ ከተማ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በመጎብኘት ተከበረ።

"ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የማንሰራራት ቀንን በማስመልከት በአብርሃጅራ ከተማ በክረምት በጎፈቃድ የተገነቡ የእቅመ ደካማ ቤቶች፣ ማደያዎች ፣ ሆቴሎች፣በምግብ እራስን ለመቻል የተሰበሰበን እህል እና የውሃ ግንባታዎችን በመጎብኘት ተከብሮ ውሏል።

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጋሻው ስዩም ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ዕውን ለማድረግ የሁላችን ትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ጳጉሜ 2 «የማንሰራራት ቀን» ተብሎ የሚከበረው የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አቀባበል መነሻ በማድረግ እና የተስፋ፣ የእድገት እንዲሁም የለውጥን አስፈላጊነት ለማሳሰብ መሆኑንም ገልፀዋል።

ሌላው በፕሮግራሙ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አስችላ አማረ ባሳለፍነው 2018 በጀት አመት በሁሉም መስኮች የተገኙ ስኬቶችን በማስታወስ እና በማስተዋወቅ አዲሱ አመትን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ሆነን የማንሰራራት ቀንን በማክበራችን ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የጳጉሜ ቀናቶች የዓመቱን ጉድለቶቻችን በመገምገም ለመጪው አዲስ ዓመት የምንሰራቸውን ስራዎች የምናቅድባቸው መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

በጉብኝት ፕሮግራሙ ተገኝተው ከገበኙት መካከል አባ ተካ አለሙ እና ፈረደ ጫኔ ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት የተሰራው ቤት ለበርካታ አመታት በቀን ስራ የሚተዳደሩ እና አቅም የሌላቸው በመሆናቸው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የተሰራው ስራ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይም እንደዚህ አይነት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበቸው አስተያየታቸውን የሰጡት ጎብኝዎቹ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶችም የህዝብን ችግር የሚፈቱ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በጉብኝት ፕሮግራሙ የወረዳው አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የአብርሃጅራ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

አብርሃጅራ፦ጳጉሜ-2/2018 ዓ/ም የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
youtube:
https://youtube.com/?si=9zUtvoNNNSOblOik

06/09/2026

ጳጉሜን-1 «የእመርታ ቀን» በተመለከተ በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የተካሄደ የሰብል እና የተፋሰስ ልማት ጉብኝት

አብርሃጅራ፦ ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ።

‎ጳጉሜን-1 «የእመርታ ቀን» በድምቀት‎‎በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ  አብርሃጅራ 01ቀበሌ ጳጉሜ-1 "የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ በftc የገበሬዎች ማሰልጠኛ  እና ...
06/09/2026

‎ጳጉሜን-1 «የእመርታ ቀን» በድምቀት

‎በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብርሃጅራ 01ቀበሌ ጳጉሜ-1 "የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ በftc የገበሬዎች ማሰልጠኛ እና የሰላም ተፋሰስ ልማት ያለበትን ሁኔታ የመስክ ጉብኝትና የአርሶአደር የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሂዷል።

‎በመስክ ጉብኝቱ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ftc የአኩሪ አተር፣ የሰሊጥ፣ የማሽላ እና የftc ማሰልጠኛ ቢሮ ግንባታው ተጎብኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የአብርሃጅራ 01ቀበሌ ሰላም ተፉስስ ያለበት ሁኔታ ተጎብኝቷል።

‎የጷጉሜ ቀናቶች የተመዘገቡ ሀገራዊ ስኬቶችን በማጉላት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በተለያዩ ሁኔታዎች እየተከበሩ መሆናቸውን የገለፁት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ ጌጡ ዋለ "ጳጉሜን-1 «የእመርታ ቀን» ግብርና በበላይነት የሚያስተባብረውና ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎችን የሚቃኙበት መሆኑን ተናግረዋል

‎በምልከታው የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየለማ የሚገኘው ሰብል የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በተግባር የሚያሳይ እንደሆነም ተመላክቷል።

‎ በፕሮግራሙ የወረዳ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች ፣የአብርሃጅራ 01/02 ቀበሌ ነዋሪዎች ተገኝተው ጎብኝተዋል።

‎አብርሃጅራ ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
Telegrams :https://t.me/+xuUwI1oZM-I2M2U8
youtube:https://youtube.com/?

በምዕራብ አርመጭሆ ወረዳ  “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል መሪ መልዕክት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ የአቅመ ደካማ መኖርያ ቤቶች ተጠናቆ ርክክብ ተካሄደ ።አብርሃጅራ:-ነሐሴ ...
05/09/2026

በምዕራብ አርመጭሆ ወረዳ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል መሪ መልዕክት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ የአቅመ ደካማ መኖርያ ቤቶች ተጠናቆ ርክክብ ተካሄደ ።

አብርሃጅራ:-ነሐሴ 30/2018 ዓ/ም (የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት) በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በክረምት በጎ ፍቃድ አግልግሎትና በመንግሥት ድጋፍ ተገንብተው የተጠናቀቁ ቤቶችን ለተገነባለቸው አቅመ ደካማ እናቶች አስረክቧል ።

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል ቃል የተጀመረው የክረምት የበጎ ፍቃድ አግልግሎት ብዙ የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከችግር እያወጣ መሆኑ የተናገሩት የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጋሻው ስዩም በክረምት ከተሰሩ የበጎ ስራዎች ተግባር አንዱ ቤት ለሌላቸው ለአቅመ ደካሞች ቤት መገንባት መሆኑን ተናግረዋል ።

በዛሬው ዕለትም በወረዳው መንገድ ትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ፅ/ቤት አስተበባሪነት ከበጎ ፈቃደኛ አሽከርካሪዎች ገንዘብ በመሰብሰብ ገንብቶ ያጠናቀቀውን የአቅመ ዳካማ ቤት በማስረከባችን ደስተኛ ነኝ ብለዋል።ይህን ድጋፍ ላስተባበሩ እና ገንዘባቸውን ለዚህ ጥሩ አላማ ለደገፉ አሽከርካሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

እንደ ወረዳ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩት የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ የሽወርቅ ሙቀት በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 16ቤት በአዲስ መገንባት እና 29 ቤት በማድስ ለአቅመ ደካሞች ማስረከብ መቻሉን ገልፀዋል ።

የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር የአቅመ ደካማዎችን ጫና በማቃለል የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ይህ ድጋፍ
ለአደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ቁልፉን ያስረከቡት የወረዳው መንገድ ትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ፅ/ቤት የትራንስፓርት ዘርፍ አስተበባሪ አቶ ጋሻው ጨርቆስ በክረምት የበጎ አድራጎት ከሚሰሩት ተግባራት ውስጥ አንዱ የአቅመ ደካማ ቤት መስራት መሆኑን ገልፀው ከተሽከርካሪ ዘርፉ ከ145ሺህ ብር በላይ በመሰብስብ ቤቶችን በአዲስ በመገንባት ለአቅመ ደካሞች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል ።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእያንዳንዳችን ትንንሽ ድጋፎች ሲሰባሰቡ ትላልቅ ስራዎችን መስራት የሚቻል መሆኑን ያየንበት ተግባር ነው ያሉት አቶ ጋሻው ጨርቆስ በቀጣይም እንደዚህ ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል ይገባ ብለዋል።
በዚህ በጎፈቃድተግባር ለተሳተፉ አሽከርካሪዎችም ምስጋና አቅርበዋል።

ቁልፉን የተረከቡት የአብርሃጅራ 01ቀበሌ ነዋሪዋ ወ/ሮ አጫዋች ሞላ በቀበሌው ከ20አመት በላይ በክራይ ቤት እንደኖረች እና የቀን ስራ በመስራት የቤት ክራይ ትከፍል እንደነበር ተናገራለች።

አሁን ግን በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ቤት ተሰርቶ በመሰጠቷ በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች።

ከዚህ በተጨማሪም በአብርሃጅራ 02 ቀበሌ ነዋሪ ለሆነችው ወ/ሮ የብር ውሃ ፈንቴ በህብረተሰብ ተሳትፎ በተሰበሰብ 100ሺህ ብር በላይ ቤት ገንብቶ ማስረከብ ተችሏል።

በርክክብ ፕሮግራሙ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጋሻው ስዩም፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አስችላ አማረ ፣የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ የሽወርቅ ሙቀት ፣ ሌሎች የተቋማት እና የቀበሌ አመራሮች ፣የመንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፅ/ቤት የትራንስፓርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ጋሻው ጨርቆስ፣ የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አስተባባሪ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
Telegrams :https://t.me/+xuUwI1oZM-I2M2U8
youtube:https://youtube.com/?

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አንገረብ ሁለገብ  የባህል ቡድን12ኛ አመት የምስረታ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አከበረ።የባህል ቡድኑ የአርማጭሆን ባህልና እሴት ከሚያስተዋውቁ በወረዳው ከሚገኙ የባህል ...
04/09/2026

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አንገረብ ሁለገብ የባህል ቡድን
12ኛ አመት የምስረታ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አከበረ።

የባህል ቡድኑ የአርማጭሆን ባህልና እሴት ከሚያስተዋውቁ በወረዳው ከሚገኙ የባህል ቡድኖች አንዱ ነው።
በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አስተዳደር ዋነኛ የበጀት ድጋፍ እንዲሁም በወረዳው ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ፅ/ቤት አስተዳደራዊና ልዩ ልዩ ድጋፎች የሚታገዘው ይህ ቡድን ስራ አስኪያጁን ጨምሮ ከ30 በላይ አባላት አሉት።

ከተቋቋመበት 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደትም በርካታ ህዝባዊና መንግስታዊ መድረኮችን በመስራት የአካባቢያችንን ብሎም የሀገራችንን ባህል፣ ታሪክ፣አብሮነት፣እድገት እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በኪነ ጥበብ እያዋዛ መድረክ ላይ በማቅረብ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የባህል ቡድን ነው።

በዚህም በመድረክ ስራዎቹ በወረዳ እና በዞን መምሪያዎች ልዩ ልዩ ምስጋናዎችንና አንቱታን ያተረፈ ምርጥ የባህል ቡድን ነው።

በ12ኛ አመት የምስረታ በዓሉም በወረዳው አስተዳደር 400ሺህ ብር ድጋ የተገዛውን የሙዚቃ መሳሪያዎች እና አልባሳት ተረክቧል።

በበዓሉ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ፅ/ቤት ተወካይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አስፈሬ የባህል ቡድኑ አሁን ላይ በዞናችን ከሚገኙ የባህል ቡድኖች በአደረጃጀቱ፣ በተሻለ የድምጽ ፣ የሙዚቃ መሳሪያና የአልባሳት አጠቃቀሙ መተሻለ መንገድ የሚቀመጥ የባህል ቡድን ነው ብለዋል።

የወረዳው አስተዳደር 400ሺህ ብር በጀት በመመደብ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና አልባሳት እንዲሟሉ ለማደረግ ያደረገው ድጋፍ ለለአንገረብ ሁለገብ የባህል ቡድን ያለውን ትልቅ ከበሬታ ያሳየ መሆኑን የገለፁት ተወካይ ኃላፊው ለወረዳው አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።

የባህል ቡድኑ በቀጣይ ጥራት ያላቸውን የመድረክ ስራዎች ለህዝብ በማቅረብ በወረዳው ብሎም በዞንና በክልል ደረጃ ተጽእኖ ፈጣሪ የባህል ቡድን ለመሆን ጠንክሮ መስራት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

በምስረታ በዓሉ የተገኙት እና በተለያዩ ጊዜያት የባህል ቡድኑን የሚደግፉት አቶ ነጠረ መኮነን የተገዛውን አልባሳት ለባህል በድኑ አስረክበው መጤ ባህሎችን ወደ ጎን በመተው የአርማጭሆ እና የሀገራችሁን ትክክለኛ ባህል ማስተዋወቅ አለበችሁ ብለዋል።
በፕሮግራሙ ዝግጅት ደስተኛ የሆኑት አቶ ነጠረ መኮነን ለባህል ቡድኑ 1000 ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በመስረታ ፕሮግራሙ ባህል ቡድኑን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለደገፉ የተቋማት ባለሙያዎች፣ለባህል ቡድኑ አስተባባሪዎች ፣ በደምፅ ፣ በውዝዋዜና በሌሎች ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው የባህል ቡድኑ አባላት የምስጋና የምስክር ወረቀት እና የሞባይልካርድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የባህል በድኑ የአርማጭሆን እና የክልሉን ባህል ለማስተዋወቅ ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።400ሺህ ብር ድጋፍ ያደረገላቸውን የወረዳውን አስተዳደርም አመስግነዋል።

አብርሃጅራ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
Telegrams :https://t.me/+xuUwI1oZM-I2M2U8
youtube:https://youtube.com/?

03/09/2026

«የሕይወት ለውጥ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፡የእናቶች ተጋድሎ እና ተስፋ »
በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የፌስ ቡክ ቤጅ በቅርብ ቀን ይጠብቁን።

አብርሃጅራ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

በጎነት ለኢትዮጵያ  ከፍታ በሚል መሪ ቃል ድጋፍ ለሚሹ  ተማሪዎች የተሰበሰበ 372 ደርዘን ደብተር  እርክክብ ተደረገ።አብርሃጅራ:-ነሐሴ 27/2018 ዓ/ም (የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስ...
02/09/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የተሰበሰበ 372 ደርዘን ደብተር እርክክብ ተደረገ።

አብርሃጅራ:-ነሐሴ 27/2018 ዓ/ም (የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት) በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ለማገዝ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ፣ከተቋማት እና ከወረዳው ነዋሪዎች የተሰበሰበ የመማሪያ ቁሳቁስ እርክክብ ተደርጓል።

በርክክብ ፕሮግራሙ የተገኙት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሰማርቶ አላምረው በ2018 በጀት አመት አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ የሚል መልዕክት ይዘን ከበጎ አድራጊ ተቋማት እና ግለሰቦች በመሰብሰብ በርካታ የአቅም ውስንነት ያለባቸው እና ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች በወቅቱ ወደ ትምህርት ገበታቸው ገበተው እንዲማሩ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

ይህን በጎ ተግባር በ2019 በጀት አመት የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር አጠናክሮ ለማስቀጠል እቅድ በመያዝ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ፣በተቋማት እና ከወረዳው ነዋሪዎች የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ሲሰበሰብ መቆየቱን ገለፀዋል።

በዛሬው ዕለትም በተደረገው የመማሪያ ቁሳቁስ የበጎ አድራጎት የማሰባሰብ ስራ 372 ደርዘን ደብተር 27 ፓኮ እስክብሪቶ እና 5 የተማሪዎች ቦርሳ ተሰብስቦ እርክክብ መድረጉን አብራርተዋል።

የተሰበሰበውን የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ የተረከቡት የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋሲል ማለደ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ በማሰብ የተለያዩ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረው ይህ ተግባር የማህበረሰቡን የመረዳዳት፣የመተጋገዝ፣የአብሮነትን እሴትና ባህል የሚያጎለብትና የነገ ትውልድ ተረካቢዎችን የቀጣይ ተስፋና ራዕይ የሚያሳካ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ የሚዲያ ዘመቻ አስተባባሪዎች ፣ለተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ለወረዳው ነዋሪዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ፋሲል ማለደ ሁሉም የወረዳችን ህዝብ በዚህ በጎ አድራጎት ተግባር በመሳተፍ አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆን ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መሰራት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

በርክክብ ፕሮግራሙ የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ምክትል አስተደዳሪ አቶ አሰማርቶ አላምረው ፣የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ አላፊ አቶ ጋሻው ስዬም፣ የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፅ/ቤት ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አስችላ አማረ፣ የወረዳው ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ነው ለወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት እርክክብ የተደረገው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
Telegrams :https://t.me/+xuUwI1oZM-I2M2U8
youtube:https://youtube.com/?

ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የሚደረገው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ   ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ሲሰበሰብ መቆየቱ ይታወቃ...
02/09/2026

ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የሚደረገው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ሲሰበሰብ መቆየቱ ይታወቃል። በዚህም በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተሰበሰበውን 43ደርዘን ደብተር፣ 5 የተማሪ ቦርሳ እና 5 ፓኮ እስክብሪቶ ለበጎ አድራጎት አስተባባሪ ተቋማት አስረክቧል።

​በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሠረት ብርሃኑ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማበረታታትና የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስተባበር ከበጎ አድራጊ ወገኖች በመሰብሰብ 43ደርዘን ደብተር፣ 5 የተማሪ ቦርሳ እና 5 ፓኮ እስክብሪቶ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አስተባባሪው አቶ መሰረት ብርሃኑ እንደገለጹት ይህ ተግባር በወረዳው ያሉ የኢኮኖሚ አቅም የሌላቸውን እና አቅመ ደካማ የሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን ያለምንም የቁሳቁስ ስጋት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲልኩ ለማገዝ ያለመ ነው ብለዋል።

ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተግባር የህዝባችንን የቆየና የተለመደ የማኅበረሰብ አጋርነት ያሳየ ተግባር መሆኑን አስተባባሪው ጠቅሰዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አስተባባሪ አቶ መሰረት ብርሃኑ የኢኮኖሚ አቅም የሌላቸው እና አቅመ ደካማ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ገብተው መማር እንዲችሉ ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሸወርቅ ሙቀት በበኩላቸው የማህበራዊ የሚዲያ ዘመቻ አስተባባሪዎች ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ማቴሪያል ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳያቋርጡ ለማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላሳዩት አርአያነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሸወርቅ ሙቀት ለወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት አስረክበዋል።

አብርሃጅራ ነሐሴ 27/2018 ዓ/ም የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
Telegrams :https://t.me/+xuUwI1oZM-I2M2U8
youtube:https://youtube.com/?

01/09/2026

በ10ሺህ ብር የተጀመረ አስደናቂ ስኬት! ወጣት ቀኑ አደራጀው ከቲክቶክ እስከ ሰቆጣ ፕሮጀክት የሄደችበት አነቃቂ ጉዞ።

አብርሃጅራ ነሐሴ 26/12/2018 ዓ/ም የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/share/1CsG1K8GAR/
Telegrams :https://t.me/+xuUwI1oZM-I2M2U8
youtube:https://youtube.com/?

Address

Gondar

Telephone

+251970887823

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ኦፊስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share