በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Gunchire
  • በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለዜጎቻችን !!!

ነሐሴ 28/2018ዓ.ም==========በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ኢባራኝ ቀበሌ እየለማ ያለ የጤፍ ማሳ
03/09/2026

ነሐሴ 28/2018ዓ.ም
==========በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ኢባራኝ ቀበሌ እየለማ ያለ የጤፍ ማሳ

03/09/2026

በእኖር ወረዳ በቹጃ ኤፐዊ ሜና በወሄ ሃለት አነኸ ኧጥፈት ቢድሗ ቡር አቨቃት አብድልመጂድ ጀማል አትሔርሙ።

እእኖር ወረዳ ኧመንግስት ተኸልቅ አትራሁት ጥፈት ቢድ አስራጀን መስራጀ ኦቢኤን(OBN)📺 ዋኸ ሽካከተ አሁዋይ አሰንኣን።

ኦቢኤን(OBN)📺 እንግዝየ ቲና ኧኸርሑዋይ አኸዳንራ ኧስርኣሁዋ🙏።

ነሐሴ 28/2018ዓ.ም=======እንኳን ደስ ያላችሁ/ወሄም ሳረናሁምየእኖር ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም አጠቃላይ አፈጻጸም ከዞኑ 1ኛ በመሆን የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል...
03/09/2026

ነሐሴ 28/2018ዓ.ም
=======እንኳን ደስ ያላችሁ/ወሄም ሳረናሁም
የእኖር ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም አጠቃላይ አፈጻጸም ከዞኑ 1ኛ በመሆን የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም==============ዘመን ተሻጋሪው የጉራጌ ማህበረሰብ የጥበብ አሻራ እሴት የሆነው "ጀፎረ" ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍና በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የተ...
02/09/2026

ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም
==============ዘመን ተሻጋሪው የጉራጌ ማህበረሰብ የጥበብ አሻራ እሴት የሆነው "ጀፎረ" ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍና በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የተጀመረው ጥረት ማፋጠን እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ገለጸ።

በወረዳው አግኝተን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ጀፎረ በኮሪደር ልማት በማስዋብ፣በአግባቡ በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

የጽ/ቤቱ ሐላፊ ወ/ሮ ጨዋነሽ ኢማም የጉራጌ ህዝብ የውብና ማራኪ ባህልና ወግ ባለቤት ሲሆን በዋነኛነት ከሚታወቅባቸው ሀብቶቹ መካከል የመንደርና የጀፎረ አመሰራረቱ እንደሆነም ተናግረዋል።

ጀፎረ የቀድሞ የጉራጌ አባቶች ያለ ምንድስህና ጥበብ ያቆዩልን የወል ሀብት ሲሆን በገጠር ኮሪደር ልማት ይበልጥ ማስዋብ ይገባል ብለዋል።

ዘመን ተሻጋሪው የጉራጌ ማህበረሰብ የጥበብ አሻራ እሴት የሆነው "ጀፎረ" ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍና በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የተጀመረው ጥረት ማፋጠን እንደሚገባም ገልጸዋል።

ጀፎረ ዘርፈ ብዙ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው የጠቆሙት ሐላፊዋ በጀፎረ ቂጫ ደንብ መሰረት ህዝቡ የባለቤትነትና የተጠቃሚነት መብት ያለው በመሆኑ በአግባቡ ተንከባክቦና ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ አደራ እንደተጣለበትም ገልጸዋል።

ለጉራጌ መንደሮች ትልቅ ውበት መላበስ አንዱ ምክንያቱ ባህላዊ ጀፎረ መሆኑን ያወሱት ወ/ሮ ጨዋነሽ በጆፈረ መንገድ ዳር ላይ የተተከሉ አገር በቀል ዛፎች ለባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓት እና ለሌሎች ባህላዊ ክንዋኔዎች እንደ ጥላ ያገለግላሉ ብለዋል፡፡

በወረዳው አግኝተን ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት ጀፎረ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች አሉት።

ሰው ሲሞት የለቅሶ፣ ባህላዊ የእርቅ እና የሰርግ ስነ ስርአት ይከናወንበታልም ብለዋል።

ለሕጻናት መጫወቻ፣ ለሰው መሰብሰቢያና መመካከሪያ እንዲሁም በአረፋና በመስቀል በዓል የአካባቢው ማህበረሰብ መዝናኛ እንዲሁም የከብቶች የጋራ ማቆሚያ ስፍራ ከመሆኑም ባሻገር ለመንደሮች ውበት እንደሆነም ገልጸዋል።

በመሆኑም ጀፎረ በኮሪደር ልማት በማስዋብ፣በአግባቡ በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።ዘገባው የወረዳው መ/ኮ ነው።

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም===============በእኖር ወረዳ ጋሳውዴ ቀበሌ የሮዝመሪና ፍራፍሬ አምራች መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ለማዕከላዊ ኢትዮጲያ ግብርና ቢሮ ለዘር የሚሆን የአቮካዶ...
02/09/2026

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
===============
በእኖር ወረዳ ጋሳውዴ ቀበሌ የሮዝመሪና ፍራፍሬ አምራች መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ለማዕከላዊ ኢትዮጲያ ግብርና ቢሮ ለዘር የሚሆን የአቮካዶ ዘር እያቀረቡ መሆኑን የወረዳው ህብረት ስራ ልማት ፅ/ቤት ገለጸ።

የወረዳው ህብረት ስራ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ልጅወርቅ ንጋቱ እንደገለጹት ማህበሩ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት አንዱ መሆኑን ገልጸው ከተቋቋመ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም ከተደራጀበት ዓላማ፣የመንግስት እስትራቴጂና ግብ አኳያ እጅግ ፈጣንና ውጤታማ የሆነ ማህበር መሆኑንም አመላክተዋል።

ማህበሩ አሁን ባለው ሁኔታ ከ60 በላይ አባላት ያቀፈና በየጊዜው በሚያደርገው የስራ እንቅስቃሴ መደበኛ የኮሚቴና የአባላት ውይይት በማድረግ የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር ዘመኑን የዋጀ ስራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በየዓመቱ የአባላት መደበኛ የትርፍ ክፍፍል ከማድረጉም ባሻገር ወረዳዊ የገቢ አፈፃፀም ላይ አዎንታዊ አቅም ለማሳደግ 10% የግብር ገቢ በመክፈል አበረታች ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ማህበሩ ከተጣለበት ግብና የስራ ተልዕኮ አንፃር የሀገራችን የህብረት ስራ ማህበራት መተግበር ያለባቸውን ተልዕኮ መሰረት በማድረግ አረሶአደሩን የሚያመርታቸው የግብርና ምርቶች ከህገ ወጥ መንገድ በማላቀቅ በቀጥታ የማህበራት የአቅርቦት ሰንሰለት ተከትሎ የማስተዋወቅ ስራዎች እየሰራ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በወረዳው ጥራት ያለውና በግብርና ምርታማነታቸው የታወቁ አቮካዶ አምራች አርሶአደሮች ለይቶ ምርታቸውን በመሰብሰብ በመጀመሪያ ዙር 80 ኩ/ል እና በሁለተኛ ዙር 240 ኩ/ል በድምሩ 320 ኩ/ል የአቮካዶ ምርት ለማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ግብርና ቢሮ ለዘር የማቅረብ ስራ መሰራቱን ኃላፊው ገልጸዋል።

ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም*******************የትራኮማ በሽታ የህብረተሰቡ የጤና ችግር ሆኖ እንዳይቀጥል በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገለጸ።ይህንንም አስ...
02/09/2026

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
*******************
የትራኮማ በሽታ የህብረተሰቡ የጤና ችግር ሆኖ እንዳይቀጥል በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገለጸ።

ይህንንም አስመልክቶ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በጉንችሬ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ከጉራጌ ዞን ኦርቢስ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መስጠት ጀምሯል።

የጉራጌ ዞን ኦርቢስ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስተባባሪ አቶ ፍቅሩ ደሴ እንደገለጹት ለአይነ ስውርነት የሚዳርገውን የትራኮማ በሽታን ለማጥፋት ድርጅቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ችግሩ ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመለየት ስራ ሲካሄድ መቆየቱን የገለጹት አስተባባሪው የአይን ሞራ ግርዶሽ ላለባቸው ዜጎች የቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

​በሆስፒታሉ ነፃ የአይን ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ታካሚዎች በበኩላቸው፤ ለተደረገላቸው መልካም ህክምና፣ እንክብካቤ እና ዳግም ብርሃን ማግኘታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

01/09/2026

ነሐሴ 26/2018ዓ.ም
==========የእኖር ወረዳ ወቅታዊ የግብርና ልማት እንቅስቃሴ በሚመለከት ያሰናዳነው መሰናዶ እነሆ ተከታተሉት።

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም==============በእኖር ወረዳ የጉስባጃይ ኮፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፕሮጀክት የነገን ትውልድ በመቅረጽ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ተገለጸ።ፕሮጀክቱን ህጻና...
01/09/2026

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
==============
በእኖር ወረዳ የጉስባጃይ ኮፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፕሮጀክት የነገን ትውልድ በመቅረጽ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ተገለጸ።

ፕሮጀክቱን ህጻናት ከማስተማር ባሻገር የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ለ185 ተማሪዎች ለ2019 የትምህርት ዘመን የሚሆን ቦርሳ ፣ደብተር እስክሪብቶና ሌሎችም የመማሪያ ቁሳቁሶች አድሏል።

በጉስባጃይ ከተማ የሚገኘው የኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጲያ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ወልዴ እንደገለጹት ፕሮጀክቱን በቀጣይ ሀገርን ሊጠቅሙ የሚችሉ ተማሪዎቾ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሳሙኡል ለተማሪዎች ምቹና ማራኪ የመማሪያ ቦታ ለመፍጠር ከ4.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የመማሪያና የመጫወቻ ስፍራዎች መገንባቱንም አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱን መንግስት ያልደረሰላቸዉ የማህበረሰብ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠትና ለማገዝ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በ2018 ዓ.ም አጠቃላይ ለተማሪዎች ምቹና ማራኪ የመማሪያ ቦታ ለመፍጠር 10 ሚሊየን 627 ሺ 8 መቶ 40 ብር ወጪ ማድረጉን አመላክተዋል።

አቶ ሳሙኤል አክለውም ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትየጵያ በልጆች አካላዊ፣
አእምሮአዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል ሲል የዘገበው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ነሐሴ 26/2018ዓ.ም==========በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ከጃቱ አጋሬ እየተገነባ ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ በምስል
01/09/2026

ነሐሴ 26/2018ዓ.ም
==========በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ከጃቱ አጋሬ እየተገነባ ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ በምስል

01/09/2026

ቤፐዊ ምር በኮሪ

Address

Gurage Zone Enor Woreda
Gunchire

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share