02/09/2026
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
************************
ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.
በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ እና በፌደራል ፖሊሲ 27 ዙር መደበኛ ምልመላ እቅድ ዙሪያ ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን
በውይይቱ የክልሉን አንፃራዊ ሰላም ለማፅናት በፀጥታ አካላትና በማህበረሰቡ ቅንጅት እየተሰራ ያለው ሥራ ውጤታማ መሆኑ የተገኘውን ውጤት ለማጠናከርም በቀጣይ በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
እንዲሁም የ2019 የ1ኛ ዙር የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምልመላ ክልላችን በሀገር ደረጃ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻላችን የቅንጅታችን ውጤት መሆኑን ገልፀው በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተቋምን በሰው ኃይል ለማጠናከር ያላችሁን ተሞክሮ በመጠቀም መስፈርቱን ተከትላችሁ በተለይ የብሔር ተዋፅኦ በጠበቀ መልኩ ለስራው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን እንድትወጡ ሲሉ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ ገልፀዋል፡፡
የሐረሪ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አህመድ አብዲ በበኩላቸው የ27ኛው ዙር መደበኛ ምልመላ በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም በመቀናጀት በተገቢው የሙያ መስፈርት የተሰጠውን ኮታ በቁጥር ብቻ ሳይሆን በጥራት መፈፀም ተቋሙን በብቁ የሰው ኃይል ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑም ገልፀዋል ።
በመርሃ ግብሩ የዘጠኙም ወረዳ የሰላምና ፀጥታ አስተባባሪዎች፣ የጣቢያ አዛዦችና የሰው ኃይል ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል።
ሰላም ለሁሉም!!!!
ሁሉም ለሰላም!!!!