Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Harari Regional State Innovation and Technology Agency This is official page of Harari Regional State Innovation and Technology Agency

ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት የሚያሸጋግረው የኮደርስ ኢኒሼቲቭ***************************ዓለም በፍጥነት ወደ ዲጂታል ዘመን እየተሸጋገረች ባለችበት...
21/08/2026

ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት የሚያሸጋግረው የኮደርስ ኢኒሼቲቭ
***************************

ዓለም በፍጥነት ወደ ዲጂታል ዘመን እየተሸጋገረች ባለችበት ወቅት፣ የአንድ ሀገር የወደፊት ተወዳዳሪነት የሚወሰነው ባላት የተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን፣ ዜጎቿ ባላቸው ዕውቀትና ክህሎት ነው።

በዚህ የለውጥ ሂደት ኢትዮጵያ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ባሻገር የራሷን የዲጂታል አቅም በመገንባት ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመሸጋገር እየሠራች ትገኛለች።

የዚህ ሽግግር ዋና መሠረት የሰው ኃይል ነው። ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ቴክኖሎጂን መፍጠር፣ ችግርን በዲጂታል መንገድ መፍታት እና እውቀትን ወደ ኢኮኖሚያዊ እሴት መቀየር የሚችል ትውልድ መገንባት ወሳኝ ነው።

በዚህ አቅጣጫ የተጀመረው በሚሊየን የሚቆጠሩ ወጣቶችን የዲጂታል ክህሎት ባለቤት የማድረግ ጥረት ከአንድ የሥልጠና ፕሮግራም በላይ የሆነ ሀገራዊ የለውጥ አቅጣጫ ነው።

7 ሚሊዮን ኮደሮች የሚለውም ቁጥር ብቻ ሳይሆን የሐሳብ፣ የፈጠራና የኢኮኖሚ አቅምን የሚወክል ግብ ነው። አንድ ወጣት ኮዲንግ ሲማር በኮምፒዩተር ላይ ኮድ መጻፍን ብቻ ሳይሆን፤ ችግርን መተንተን፣ መፍትሔ መንደፍ፣ ሐሳብን ወደ ምርት መቀየር እና የራሱን የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችል አቅም ያገኛል።

ይህም ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ቴክኖሎጂ ፈጣሪነት ለማሸጋገር የሚያግዝ እድል ነው። የዲጂታል ክህሎት ያለው ወጣት ለራሱ ሥራ ከመፍጠር ባሻገር ለሌሎችም የሥራ እድል ይፈጥራል።

በተለይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) መስፋፋት ይህንን ሽግግር የበለጠ አፋጥኖታል። ከመረጃ ትንተና እስከ ጤና፣ ከግብርና እስከ ትምህርት የዘለቀ አዳዲስ የችግር መፍቻ መንገዶችን እያስገኘ ነው።

በዚህ ዘርፍ የሚፈጠረው እውቀት ኢትዮጵያ የራሷን ቴክኖሎጂ እንድታበለጽግ እና በአፍሪካና በዓለም ዲጂታል ገበያ ውስጥ የበለጠ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያግዛል።

ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስንሸጋገርም ትኩረቱ ዲጂታል አገልግሎት ከማስፋፋት ባሻገር የሚፈጥር የሰው ኃይልን ማብዛት ላይ ነው። የተማረ ወጣት የሚፈጥረው ሶፍትዌር፣ የሚያበለጽገው መተግበሪያ፣ የሚያቀርበው ዲጂታል አገልግሎት እና የሚፈጥረው የዲጂታል ኢኮኖሚው ተጨባጭ ውጤቶች ናቸው።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ከኮምፒዩተር እና ከኢንተርኔት የሚጀምር ቢመስልም፣ ትልቁ መሠረት ሰው ነው። ዛሬ የሚማረው ክህሎት ነገ የሚፈጠረው ምርት ነው፤ ዛሬ የሚወጣው ሐሳብ ነገ የሚመሠረተው ኩባንያ ነው፤ ዛሬ የሚገነባው የዲጂታል አቅም ነገ የሀገር ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት ነው።

ስለዚህ ከዲጂታል ክህሎት ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚደረገው ጉዞ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጠራ፣ ከእውቀት ወደ እሴት፣ ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት እና ከአካባቢያዊ ገበያ ወደ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚወስድ የኢትዮጵያ የነገ ጉዞ ነው።

7 ሚሊዮን ኮደሮችም የዚህ ጉዞ ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ፣ የነገዋን ዲጂታል ኢትዮጵያ የሚገነቡ ሚሊዮን አዕምሮዎች ናቸው።

Source Ethiopian Broadcasting Corporation

ሰባት ሚሊዮን ኮደሮች፡ ኢትዮጵያ ዓለምን ለመፎካከር ዝግጁ ናትዓለማችን በቴክኖሎጂ ፍጥነት እጅግ እየተሽከረከረች ባለችበት በዚህ ዘመን፣ ኢትዮጵያ ዳር ቆማ ተመልካች መሆንን አልመረጠችም።የመደ...
21/08/2026

ሰባት ሚሊዮን ኮደሮች፡ ኢትዮጵያ ዓለምን ለመፎካከር ዝግጁ ናት

ዓለማችን በቴክኖሎጂ ፍጥነት እጅግ እየተሽከረከረች ባለችበት በዚህ ዘመን፣ ኢትዮጵያ ዳር ቆማ ተመልካች መሆንን አልመረጠችም።

የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት የዲጂታል አገልግሎቶችን መስጠት ብቻ ሳይሆን የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን እና ክህሎቶችን በማዳበር እንዲሁም ተቋማትን በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና አሁን እየተተገበረ ባለው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዕቅድ መሠረት በመገንባት ላይ ይገኛል።

በዚህም ከስድስት ዓመታት በፊት እንደ ሀገር ብዙም ያልተለመደውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ጽንሰ-ሀሳብ ወደ ተቋም በመቀየር በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ፖሊሲ ቀርጻ ወደ ሥራ ገብታለች።

አሁን ደግሞ በአህጉሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ እውን እያደረገች ሲሆን፣ ይህም ሀገራችን በዘርፉ ያላትን ራዕይና የነገዋን ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ከፍታ በግልጽ የሚያሳይ ነው።

ይሁንና እነዚህ ግዙፍ መሠረተ ልማቶች ትርጉም የሚኖራቸው ዕውቀቱና ክህሎቱ ባለው አምራች ዜጋ ሲመሩ ብቻ ነው።

ለዚህም ነው "ትውልድ ይማር፣ ትውልድ ይሰልጥን፣ ከዓለም ጋር ይፎካከር" በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ውጥን፣ አስደናቂ ሀገራዊ ንቅናቄ የፈጠረው።

በሦስት ዓመት ለማሳካት የታቀደውን ተሳትፎ በሁለት ዓመት በማሳካት፣ አሁን ግቡን ወደ 7 ሚሊዮን ከፍ ማድረግ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ዲጂታል ክህሎት ማጣት፣ ልክ እንደ ቀድሞው ዘመን ማንበብና መጻፍ አለመቻል ተደርጎ የሚቆጠርበት የለውጥ ጊዜ ላይ ደርሰናል።

በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት ዲጂታል ዕውቀት ወሳኝ ሚና አለው።

በመሆኑም ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዕቅድ ስንሸጋገር፣ አካታች የሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እና ኢትዮጵያን የዲጂታል ኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ የወጣቱ ዝግጁነት ቁልፍ መስፈርት ነው።

ዓለም አቀፍ ተቋማት መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ የሚመርጡት፣ በቴክኖሎጂ የታነጸ እና ብቁ የሰው ኃይል ያላትን ሀገር በመሆኑ፣ የጀመርነውን የክህሎት ግንባታ አጠናክረን መቀጠል ግድ ይለናል።

ስለዚህም መላው የሀገራችን ወጣቶች ይህን በነፃ የሚሰጥ እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ሥልጠና ትልቅ ዕድል አድርጋችሁ ልትጠቀሙበት ይገባል።

በተለይም በዕረፍት እና በክረምት ወቅት ጊዜያችሁን በአግባቡ በመጠቀም፣ ተመዝግባችሁ ሥልጠናውን በማጠናቀቅ ለራሳችሁም ሆነ ለሀገራችሁ የችግር ፈቺነት ሚናችሁን እንድትወጡ አጥብቀን እናሳስባለን።

ዛሬ ላይ የምንገነባው ዲጂታል አቅም፣ ነገ ኢትዮጵያን ይበልጥ ተስፈኛ ሳትሆን ተስፋዋን ጨብጣ የምትኖር፣ በዓለም አቀፍ መድረክም ተወዳዳሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር እንድትሆን የሚያደርጋት ጽኑ መሠረታችን ነው።

ኢቢሲ

ዲጂታል 2030፦የኢትዮጵያ አዲሱ የቴክኖሎጂ ዘመን!የዲጂታል 2025 መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ታኅሣሥ 11 ቀን 2018...
20/08/2026

ዲጂታል 2030፦የኢትዮጵያ አዲሱ የቴክኖሎጂ ዘመን!

የዲጂታል 2025 መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ይህ አዲስ ምዕራፍ ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በዲጂታል ዘርፉ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች አጠናክሮ ለመቀጠል የተዘጋጀ ታላቅ አገራዊ እቅድ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች ሲሉ ገልጸዋል።ተደራሽነትን ማስፋት፣እኩል እድል መፍጠር እና በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት የስትራቴጂው ቁልፍ ትልሞች ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛውና ለአፍሪካ የመጀመሪያው የሚሆነውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ግንባታ በይፋ አስጀምራለች። ይህ ዩኒቨርሲቲ ሀገሪቱን በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግና የላቀ የኤአይ ባለሙያዎችንና ተመራማሪዎችን የሚያፈራ ታሪካዊ ተቋም ይሆናል።

ይህ ታላቅ የትምህርት ተቋም ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) በማመቻቸት፣ ኢትዮጵያን የአህጉሪቱ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) የማድረግ ራዕይን በግንባር ቀደምትነት የሚያስፈጽም ይሆናል።

በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አጋርነት የተመረቀው 'AI UniPod' ማዕከል፣ ወጣቶች በሮቦቲክስ፣ በዳታ ሳይንስና በኤአይ ምርምሮች ላይ እንዲሰማሩ ትልቅ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ፈጥሯል።

አዲሱ ስትራቴጂ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠርን ያለመ ነው። ይህም ቢሮክራሲን በመቀነስ ለዜጎች ፈጣንና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።

በተጨማሪም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር የስትራቴጂው ዋና ግብ ነው።

የዲጂታል ኢኮኖሚው ሲያድግ የመረጃ ደህንነት ወሳኝ በመሆኑ፣ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማቶችን ማጠናከር የዚሁ ዕቅድ ዋነኛ አካል ተደርጎ ተይዟል። ይህም የዜጎችንና የተቋማትን የመረጃ ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ይፈጥራል።

ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል። ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ በጥራት እንዲያሻሽልና አገልግሎቶችን እንዲያቀልጥ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

በተጨማሪም ይፋ በተደረጉ አገራዊ መረጃዎች መሰረት፣ የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ደንበኞችን ቁጥር 128 ሚሊዮን ማድረስ እና የ5G አውታረ መረብ ተደራሽነትን 100% ማድረስን አልሟል።ይህም የመገናኛ አቅምን በማሳደግ የዲጂታል ክፍተቱን በከፍተኛ ደረጃ ያጠበዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ ማካሄድ ሌላው ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራበት ሀገራዊ ግብ ነው። ይህም አሰራርን ግልጽ፣ ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው። ለዚህም ስኬት የሁሉም አካላት ትብብርና ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቅሷል።

በመጨረሻም፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬት ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ የበለጸገች፣ የወጣቶችን ፈጠራ የምታበረታታ እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ የሚያገለግል ታላቅ የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ነው።

Source Ethiopian News Agency

🛡️ ከዲጂታል ዕድገት ጋር የሚራመደው የሳይበር ደኅንነት እና የግል መረጃን ማስጠበቅየዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ኑሮ በእጅጉ በመቀየር፤ መግባባትን፣ ግብይትን፣ የባ...
20/08/2026

🛡️ ከዲጂታል ዕድገት ጋር የሚራመደው የሳይበር ደኅንነት እና የግል መረጃን ማስጠበቅ

የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ኑሮ በእጅጉ በመቀየር፤ መግባባትን፣ ግብይትን፣ የባንክ አገልግሎትን፣ ትምህርትን እና የመንግሥት አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀላል እና ፈጣን አድርጎታል።
ሆኖም ከዚህ ዕድገት ጋር ተያይዞ የግል መረጃን ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነትም አብሮ መጥቷል!

ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የኢ-ሜይል አድራሻ፣ የይለፍ ቃል፣ የባንክ መረጃ እና ሌሎች ምሥጢራዊ መረጃዎች የዲጂታል ማንነታችን አካል ናቸው። እነዚህ መረጃዎች አጭበርባሪዎች እጅ ከገቡ የገንዘብ ማጭበርበር፣ የመለያ ጠለፋ (Hacking) እና የማንነት ስርቆት ሰለባ ሊያደርጉን ይችላሉ። አጥቂዎች በተለይም ከታመነ ተቋም የመጣ በሚመስል ሐሰተኛ መልዕክት (Phishing) ወይም ሊንክ በማላክ እንድናታልል ይሞክራሉ።

ስለሆነም የግል መረጃን መጠበቅ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ የግል ኃላፊነት በመሆኑ ቀጣዮቹን የጥንቃቄ እርምጃዎች ዘወትር ይተግብሩ፦
🔑 ጠንካራ የይለፍ ቃል፦ ለእያንዳንዱ መለያ የተለየ እና ጠንካራ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ፤

🔐 ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ (Multi Factor Authentication-MFA) ፦ በማኅበራዊ ሚዲያዎ እና በሌሎች አካውንቶችዎ ላይ ባለ 2-ደረጃ ማረጋገጫን ያብሩ፤

📱 ሁሌም ማዘመን (Update)፦ ስልክዎን፣ ኮምፒውተርዎን እና መተግበሪያዎችን በየጊዜው ያዘምኑ፤

🔗 ጥንቃቄ በሊንኮች፦ ከማያውቁት ምንጭ የሚመጡ አጠራጣሪ ሊንኮችን በፍጹም አይክፈቱ፤

🤫 የግል መረጃን አለማጋራት፦ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የግል እና ምሥጢራዊ መረጃዎችን በይፋ ከማጋራት ይቆጠቡ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እያደረገች ባለው ሽግግር፤ የሳይበር ደኅንነት እና የመረጃ ጥበቃ የዲጂታል ልማታችን ዋነኛ አካል ሊሆን ይገባል! መንግሥታዊ ተቋማት፣ የፋይናንስ ዘርፉ እና የቴክኖሎጂ ተቋማትም መረጃን በአግባቡ ለመጠበቅ ጠንካራ ሥርዓት መዘርጋታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
ደኅንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል አካባቢ በመፍጠር የዜጎችን እምነት፣ የኢኮኖሚ ደኅንነት እና የዲጂታል ማኅበረሰባችንን ዘላቂነት በጋራ እናረጋግጥ!
📌 ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)

እንግልትን ያስቀረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትመንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አ...
18/08/2026

እንግልትን ያስቀረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት

መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው።

የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ።

በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው።ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል።

የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል።

በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል።

በሐረሪ ክልልም ዘጠኝ ቁልፍ የክልሉና የፌደራል የመንግሥት ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል።

እነዚህ ተቋማት ፦የገቢዎች ፣ የንግድ ፣ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ መሬት ልማት ፣ ኢንተርፕራይዝ ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፣ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ 96 አገልግሎቶች ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል።

በማዕከሉ ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ተችላል።

ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው።

ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ዜጎች ምቹ አገልግሎት እየቀረበበት የሚገኘው የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በውጤታማነቱ ይበል የሚያሰኝ መሆኑንም ተገልጋዮች ይገልጻሉ።

18/08/2026

ዲጂታል ፋና ወጊዋ ኢትዮጵያ

የቻይና ክፍት ምንጭ ሞዴሎች ዕድል እና የምዕራባዊያን ስጋትቻይና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እያደረገች ያለችው ፈጣን ፉክክር የዓለምን ቴክኖሎጂና ኢኮኖሚ ሥርዓት ሊቀይር እንደሚችል ባለሙ...
17/08/2026

የቻይና ክፍት ምንጭ ሞዴሎች ዕድል እና የምዕራባዊያን ስጋት

ቻይና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እያደረገች ያለችው ፈጣን ፉክክር የዓለምን ቴክኖሎጂና ኢኮኖሚ ሥርዓት ሊቀይር እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው “ቀጣዩ የቻይና ንዝረት” ተብሎ የሚጠራው ይህ እንቅስቃሴ ቻይና በዝቅተኛ ወጪ የምታመርታቸው ምርቶች ዓለምን እንደተቆጣጠሩት ሁሉ አሁን ደግሞ በክፍት ምንጭ የኤአይ ሞዴሎች አማካኝነት ተመሳሳይ ተጽዕኖ እያሳደረች መሆኑን ያሳያል።
እንደ ዲፕሲክ ያሉ ኩባንያዎች ከምዕራባውያን ተፎካካሪዎቻቸው በአነስተኛ ወጪ እና በሰፊ ተደራሽነት የኤአይ ቴክኖሎጂዎችን ለገበያ በማቅረብ የገበያ ሚዛኑን እየቀየሩት ይገኛሉ። ይህ የክፍት ምንጭ (open source) ኤአይ እድገት ለታዳጊ አገራትና ለአነስተኛ ኩባንያዎች ትልቅ ዕድል ነው፡፡

የዲጂታል ክህሎትዎን የሚያሳድጉበት ወርቃማ እድል!ለ5 ሚሊዮን ወጣቶች ተጀምሮ የነበረው ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአሁኑ ጊዜ ወደ 7 ሚሊዮን ተሳታፊዎች እንዲያድግ ተደርጓል።በዌብ ፕሮግራሚንግ፣...
16/08/2026

የዲጂታል ክህሎትዎን የሚያሳድጉበት ወርቃማ እድል!

ለ5 ሚሊዮን ወጣቶች ተጀምሮ የነበረው ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአሁኑ ጊዜ ወደ 7 ሚሊዮን ተሳታፊዎች እንዲያድግ ተደርጓል።

በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የሚሰጠውን ነጻ የኦንላይን ስልጠና በመውሰድ የዲጂታል ክህሎትዎን ያዳብሩ፣ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬትም ያግኙ።

በዚህ ሊንክ https://ethiocoders.et/ ዛሬውኑ ይመዝገቡ፤ የዲጂታል ትውልዱ አካል ይሁኑ!

የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ተመራቂ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም በፓናል ውይይት ላይ በሰጠችው አስተያየት፦ ፕሮግራሚንግን ለማወቅ  የግድ የኮምፒውተር ሳይንስ ወ...
10/08/2026

የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ተመራቂ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም በፓናል ውይይት ላይ በሰጠችው አስተያየት፦ ፕሮግራሚንግን ለማወቅ የግድ የኮምፒውተር ሳይንስ ወይም ልዩ የትምህርት ዘርፍ እንደማያስፈልግ ይልቁንም ሰዎች በእጃቸው ያሉትን የኢንተርኔት እና የቴክኖሎጂ መረጃዎች በመጠቀም እንዲሁም የአካባቢያቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመተንተን ተግባራዊ መፍትሔ ማምጣት እንደሚችሉ አብራርታለች።

‎በአሁኑ ወቅት ዲጂታል የትምህርት ቁሳቁሶች እና የመማሪያ አማራጮች በቀላሉ በእጃችን የሚገኙ በመሆናቸው ያነሳችው ማኅሌት፤ ወጣቶች ለዲጂታል ክህሎት ተነሳሽነትንና ጥረትን በማድረግ አበይት ችግሮች መፍታት እንደሚችሉ ጠቁማለች። ለዚህም ወጣቶች ዘወትር እውቀታቸውን ማደስ፣ አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ እንዲሁም ራሳቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ማብቃት እንደሚኖርባቸው ገልጻለች።

Mahlet Seyoum, alumnus of the 5 million Ethiopian Coders Initiative, and tech entrepreneur, reflects on the panel that programming does not require a specialized background. Instead, individuals can solve meaningful problems by leveraging existing resources and analyzing their immediate surroundings. She noted that because educational tools are highly accessible today, anyone can address massive challenges.

To achieve this, young people must continuously update their skills, enroll in targeted courses, and actively equip themselves with modern technology.

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉ እና የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚ...
10/08/2026

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉ እና የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት በኢኒሼቲቩ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎ይህ ዝግጅት የዘርፉን መሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎች፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውን የኢኒሼቲቩን ተመራቂዎች እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድነት ያገናኘ ነው። ተሳታፊዎች ተሞክሯቸውንና እይታቸውን በመድረኩ እንዲያካፍሉ መደላድልን በመፍጠርም፣ መርሃ ግብሩ በተግባራዊ ዲጂታል ክህሎት ልማት አማካኝነት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አጀንዳ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል።

‎መርሃ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ኃላፊዋ በንግግራቸው የወጣቶች የቴክኒክና የዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው በዚህ ክረምት የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል።

‎በመቀጠል በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ልምዳቸውንና እይታቸውን ያካፈሉ አራት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ፓናሊስቶቹም፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ (gheero) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሔም ደሴ፣ እንዲሁም የኢኒሼቲቩ ምሩቃን የሆኑት አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም ነበሩ።

ተሳታፊዎችና ወጣቶች ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ፣ በተግባር ላይ ያተኮሩ መፍትሔዎችን እንዲያበለጽጉ እና በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገትና ፈጠራ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች አበረታተዋል። ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት ነው። ይህ የልምድ ልውውጥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ እና ሀገራዊ ለውጥን ለማፋጠን ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።

Following Prime Minister Abiy Ahmed’s public call for Ethiopia’s youth to join the 5 Million Ethiopian Coders Initiative and expand its reach to 7 million participants by the end of the rainy season, the Office of the Prime Minister hosted an experience-sharing program on the Initiative. The event brought together certified graduates, industry leaders, policymakers, and young professionals to share their experiences and insights, while contributing to the advancement of the Digital Ethiopia 2030 agenda through practical digital skills development.

The program opened with a tour of an exhibition on Artificial Intelligence, followed by a followed by a keynote from Billene Seyoum, Head of the Press Secretariat at the Office of the Prime Minister, who framed youth technical capability as a vital national asset and reaffirmed the Prime Minister's call to reach 7 million coders this summer.

A panel discussion that ensured featured four speakers who shared their experiences and perspectives on the 5 Million Ethiopian Coders Initiative. The panel featured Dr. Abiyot Bayou, Senior Advisor to the Minister of Innovation and Technology; Bethlehem Dessie, CEO of gheero (ጊሮ); and Initiative alumni Azimeraw Taddese and Mahlet Seyoum, a tech entrepreneur. The panellists encouraged participants to continuously hone their skills, develop practical solutions, and contribute to growth and innovation within Ethiopia’s digital ecosystem.

The program concluded with an open networking session, during which young participants engaged the panellists with thoughtful and insightful questions. The exchange reaffirmed the 5 Million Ethiopian Coders Initiative’s role as a catalyst for developing digital talent and driving national transformation.

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Regional State Innovation and Technology Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share