Harari Region Planning and Development Commission

Harari Region Planning and Development Commission Harari Regional Planning and Development Commission

24/08/2026
21/08/2026
18/08/2026
ወጣቶች አቅማቸውን ለሀገር ብልፅግናና ለጋራ እድገት ሊያውሉ ይገባል :-  ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ወጣቶች አቅማቸውን ለሀገር ብልፅግናና ለጋራ እድገት ሊያውሉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕ...
12/08/2026

ወጣቶች አቅማቸውን ለሀገር ብልፅግናና ለጋራ እድገት ሊያውሉ ይገባል :- ወይዘሮ ሮዛ ኡመር

ወጣቶች አቅማቸውን ለሀገር ብልፅግናና ለጋራ እድገት ሊያውሉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገለፁ

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከሐረሪ ክልል መንግሥት ጋር በመተባበር የወጣቶች ንቅናቄን፣ የሥራ ባህልን፣ ሀገር ወዳድነትንና በጎ ፈቃደኝነትን ማዕከል ያደረገ አህጉራዊ/ክልላዊ የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር እንደገለጹት፤ ወጣቶች የሀገር ትልቅ ሀብት መሆናቸውን በመገንዘብ አቅማቸውን ለሀገር ብልፅግና እና ለጋራ እድገት ማዋል ይኖርባቸዋል።

ወጣቶች በክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ከክልል ተሻግረው ሀገራቸውን እንዲያውቁና አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያስችሉ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ አያይዘውም፤ በከተማና በገጠር በተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ የግብርናና ሌሎች ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች መፈጠራቸውን ጠቁመው፣ ወጣቶች ከሱስ የጸዱ እንዲሆኑና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያዘወትሩ የማዘውተሪያ ቦታዎች ከኢንቨስትመንት ጋር ተያይዘው እንዲገነቡ መደረጉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ አሁንም የሥራ ባህል ክፍተቶች፣ ሥራ የመናቅ ሁኔታዎችና ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ዋና ዋና ማነቆዎች መሆናቸውን ያነሱት ወይዘሮ ሮዛ፤ ወጣቶች ከትንሽ ተነስተው ማደግ እንዳለባቸውና በአንድ ጊዜ ትልቅ ደረጃ ለመድረስ ከሚደረግ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የወጣት አደረጃጀቶችና አመራሮችም ያሉበትን ማነቆዎች በውይይት እየፈቱ፣ ወጣቱን ማዕከል ያደረጉ የልማት ሥራዎችን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አግንዘዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ስዩም መኮንን በበኩላቸው፤ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት የታሪካዊቷን ከተማ ውበትና ቅርሶች በጠበቀ መንገድ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል።

የኮሪደር ልማቱ የመሠረተ-ልማት፣ የመብራትና የአካባቢ ፅዳትን ከማሻሻሉም በላይ፤ ታሪካዊቷን የጀጎል ግንብና የጅብ መግበያ ስፍራዎችን ለቱሪዝም ምቹና ማራኪ በማድረግ የከተማዋን ገጽታ መቀየሩን አብራርተዋል።

አቶ ስዩም አያይዘውም፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ትስስርን ከመገንባትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ለወጣቶች የሥራ ልምድና የክህሎት ማደጊያ እድል እንደሚፈጥር ገልጸው፣ የሐረሪ ክልል ህዝብ ያለው አብሮ የመኖርና የመቻቻል እሴት ለዚህ በጎ ፈቃድ አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።

የውይይት መድረኩ በሐረር ከተማ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ በዕለቱ መጠናቀቂያ ላይም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲዩም መኮንን በሀረሪ ክልል አረንጓዴ አሻራ አኖሩ።በዛሬው እለት 06/12/2018 የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ...
12/08/2026

የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲዩም መኮንን በሀረሪ ክልል አረንጓዴ አሻራ አኖሩ።

በዛሬው እለት 06/12/2018 የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲዩም መኮንን እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በሐረሪ ክልል በመገኘት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ።

ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲዩም በክልሉ ባካሄዱት በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፤ የአካባቢ ጥበቃን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም እና የሀገሪቱን የደን ሽፋን ማሳደግ ለዘላቂ ልማት ያለው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የተራቆቱ መሬቶችን ለማገገም እየተከናወነ ያለ ዘላቂ የልማት ስራ አካል ነው ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአካባቢ ጥበቃ እና በችግኝ ተከላው የተጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ ከሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር ሰፊ የልማት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዛሬው እለት በሐረሪ ክልል የሚኖሩ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችል የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በይፋ የሚያስጀምር ይሆናል።

ይህ አራያነት ያለው የበጎ አድራጎት ስራ ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ማህበራዊ ደህንነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አመራሮች ከክልሉ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ የልማት፣ የኢኮኖሚ ተሳትፎ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሰፊ የምክክር መርሃ ግብር ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ የምክክር መርሃ ግብር ወጣቶች በሀገር ግንባታ እና በልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ የበለጠ ለማሳደግ ያለመ ነው።

የኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሐረሪ ክልል ለ10 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመረ*********የኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሐረሪ ክልል ለ10 አቅመ ደካሞች የመኖሪ...
12/08/2026

የኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሐረሪ ክልል ለ10 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመረ
*********

የኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሐረሪ ክልል ለ10 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በዛሬው እለት አስጀምሯል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስዩም መኮንን በወቅቱ እንደገለፁት ድጋፉ ለ10 አቅመ-ደካሞች ደረጃውን የጠበቀ፣ ሙሉ የቤት ቁሳቁስና የኢኮኖሚ ድጋፍ ያካተተ የመኖሪያ ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል።

ለ600 ያህል ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በተለይም ወላጅ አልባና አቅም ለሌላቸው ህፃና ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል።

ወጣቶች በክረምት ወቅት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ እንዲሳተፉ፣ የሥራ ልምድ እንዲያካብቱና ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያስችሉ መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸውን አክለዋል።

ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ከተጀመረበት ባለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውንና ይህም የአካባቢ መራቆትን ከመከላከል ባለፈ ለኢኮኖሚና ለሥራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አክለውም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነትና የአንድነት ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ በባለቤትነትና "ያገባኛል" በሚል መንፈስ እንዲያስቀጥለው ጥሪ አቅርበዋል።

የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ዑመር የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ እንደገለፁት በሀረሪ ክልል በ2018 የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር 47 ሺህ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ216 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ግብ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱ ገልፀዋል።

በበጎ ፈቃድ ስራው 200 ሚሊየን ብር የሚገመት የበጎ አገአካሂዷል። ቁሳቁስ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን፣ በዋናነትም ለአቅመ ደካሞች ቤት የመገንባትና የማደስ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ የደግነትና የወገንተኝነት እሴት መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም “አንድ ቤት ስንገነባ ጣሪያና ግድግዳ ብቻ ሳይሆን ክብርን ማሳያ፣ ደህንነትን መዋጋትና የነገ ተስፋን እንገነባለን” በሚል የደግነት እሳቤ መሆኑን አስረድተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢኒሸቲቭ በየደረጃው ከሚገኙ ተቋማትና ወጣቶች ጋር በመቀናጀት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ በ2017 ዓ.ም የተከናወኑት የበጎ ፈቃድ ስራዎችም ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸውና በርካታ አቅመ ደካሞችን መደገፍ የተቻለበት እንደነበር ገልፀዋል ።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ወቅት ስራ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን ዘላቂ የልማት ባህል ሊሆን እንደሚገባና ዜጎችም "ለሀገሬና ለማህበረሰቤ ምን አደረግኩ? በሚል ስሜት በበጎነት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከሐረሪ ክልል ጋር የወጣቶች ንቅናቄ በሥራ ባህል፣አገር ወዳድነት እና በጎፍቃደኝነት የተዘጋጀ የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂዷል።

የመረጃ ምንጭ :- ሀረሪ ብሮድከስትንግ ኔትዎርክ

በገዛኸኝ አራጌ
06/12/18

የሚዲያ ባለሞያዎች በተቋማትና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ይገባል - አቶ ሄኖክ ሙሉነህየሀረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር ለሚ...
08/08/2026

የሚዲያ ባለሞያዎች በተቋማትና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ይገባል - አቶ ሄኖክ ሙሉነህ

የሀረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር ለሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ ላይም የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ በተጠናቀቀው በጀት አመት በትክክለኛ መረጃ ላይ የተገነባ ማህበረሰብ በመፍጠር የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥኖች በላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ ውጤታማ እንዲሆን የማድረግ ስራ መከናወኑን አንስተዋል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መንግስታዊ መረጃዎች ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የመገናኛ ብዙሃን እና የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች የላቀ ሙያዊ ኃላፊነታቸው መወጣታቸውን ገልጸዋል።

መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ ሃሰተኛ መረጃዎችን በመመከትና የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ለህዝብ የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በክልሉ በሚዲያና በኮሙኒኬሽን ዘርፉ እየተሰሩ የሚገኙ ውጤታማ ስራዎች የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

እንደ አቶ ሄኖክ ገለፃ የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በእያንዳንዱ ሴክተር የሚከናወኑትን ተግባራት አውቀውና ተረድተው ለዜጎች የማሳወቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ፅህፈት ቤቱ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ስልጠና መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ለአብነትም ከክልሉ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር እየተሰጠ የሚገኘው ሙያዊ ስልጠና የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም የሚዲያ ባለሙያዎች ፅህፈት ቤቱ የጀመራቸውን ውጤታማ ተግባራት በማላቅ ረገድ የድርሻውን ተልዕኮ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ለዚህም ለሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ለሁለት ቀን የሚሰጠው ስልጠና የሚኖረው አበርክቶ የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የመረጃ ምንጭ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት
ነህሴ 2/12/2018

Address

Harar

Telephone

+251968665171

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Region Planning and Development Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Harari Region Planning and Development Commission:

Shortcuts

Share