02/09/2026
ብቁና ተወዳዳሪ የፖሊስ ሰራዊት ለመገንባት በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተገለፀ
የሐረሪ ፖሊስ ወና ጠቅላይ መምሪያ ከሐረሪ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር በ27ኛው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምዝገባ ዙሪያ ውይይት አካሂዱ
በውይይቱ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሐመድ እንደገለፁት፣ ብቁና ተወዳዳሪ የፖሊስ ሰራዊት እንዲገነባ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ህዝብን የሚያገለግል ፖሊስ ብቁና ታማኝ የሐገር ፍቅር ስሜት ኖሮት የህግ የበላይነትን በቁርተኝነት የሚያስከብር መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።
ስለዚህ የሚመለመሉ የፌድራል ፖሊስ አባል ሆነው መስፈርቱ የሚጠይቀውን መመዘኛ የሚያሟሉ እና የሚሰጠውን ስልጠና በብቃት የሚወጣ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
የሐረሪ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አህመድ አብዲ በበኩላቸው፣ የፌደራል ፖሊስ ለሐረሪ ክልል የሰጠው ኮታ ተቀብሎ ወደ ምዝገባ ስራ መገባቱን ገልፀዋል።
የምዝገባው ሂደት ውጤታማ እንዲሆንም በጋራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ምልመላው ሲካሄድ በጥንቃቄና ሐላፊነት በተሞላበት ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት ገልፀዋል።
በውይይቱ የየወረዳዎቹ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎችና የሐረሪ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘገባ
አዳሱ በፍቃዱ