Harari Housing Development & Government Construction Agency

Harari Housing Development & Government Construction Agency We build the future. Restoring the past.

የክልሉ ህዝብ ነገ በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በንቃት እንዲሳተፍ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቀረቡ በነገው እለት በሚካሄደው የአንድ ...
02/08/2026

የክልሉ ህዝብ ነገ በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በንቃት እንዲሳተፍ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቀረቡ

በነገው እለት በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ ህዝቡ በንቃት እንዲሳተፍ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከአካባቢ ጥበቃና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለሀገራዊ መግባባት፣ ለአብሮነትና ለማህበራዊ መስተጋብር መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ የተከላ ጥሪ ተከትሎ ሐምሌ 27 በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃግብር አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

በመርሃግብሩ መሳተፍ ሀገርን መውደድ አንዱ የተግባር ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

የክልሉ ህዝብ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በሚካሄደው በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርlሃ ግብር በነቂስ በመውጣትና በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይገባል ሲሉ ነው የተናገሩት።

በክልሉ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል በትኩረት እየተሰራ ነው፦ አቶ መሀመድ ኑረዲን*****************በሐረሪ ክልል የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል የክልሉ መንግስት ከ...
09/07/2026

በክልሉ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል በትኩረት እየተሰራ ነው፦ አቶ መሀመድ ኑረዲን
*****************

በሐረሪ ክልል የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ዘርፈ-ብዙ አማራጮችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ የክልሉ የቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ሃላፊ አቶ መሀመድ ኑረዲን እንደገለጹት በክልሉ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ፍትሃዊ፣ ተደራሽና ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው።

በክልሉ በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ መሠረት በተለያዩ የቤት አቅርቦት አማራጮች ከ25 ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም ጨምረው ገልፀዋል።

የቤት ፍላጎትን በአንድ ወገን ጥረት ብቻ መፍታት እንደማይቻል ያስገነዘቡት አቶ መሀመድ በአሁኑ ወቅት ችግሩን ለማቃለል የተለያዩ አማራጮች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በዚሁም ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርግ የጋራ መኖሪያ አፓርታማዎች ግንባታ እንደሚከናወን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በማህበር የተደራጁ ዜጎች በራሳቸው አቅም መኖሪያ ቤት እንዲገነቡ የመሬት አቅርቦትና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠረ ይገኛል ያሉት አቶ መሀመድ በቤት ልማቱ ላይ የግሉ ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍ በማድረግ የአቅርቦት አማራጮችን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

በክልሉ ያለውን ውስን የመሬት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ሰፊ የልየታ ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት አቶ መሀመድ በ2018 ዓ.ም ብቻ የሊዝ ቅድመ ክፍያና ግዴታቸውን ለተወጡ 7 የተደራጁ ማህበራት የቤት መገንቢያ መሬት መተላለፉን ጠቁመዋል።

የቤት ልማት ፕሮግራሙ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ከማቃለልና የቤት ኪራይ ጫናን በዘላቂነት ከመቅረፍ ባለፈ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር፣ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚያነቃቃና የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያፋጥን ትልቅ አቅም እንዳለውም አመላክተዋል።

በመሆኑም በክልሉ በተለያዩ አማራጮች የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ መሀመድ አረጋግጠዋል።

በሐረሪ ክልል በ2018 ዓ.ም ከ20 ነጥብ 6 ሄክታር በላይ የመኖሪያ ቤት መገንቢያ መሬት ለልማት ተነሺዎች፣ ለግሉ ዘርፍ እና በማህበር ለተደራጁ ዜጎች መተላለፉን ከክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

02/11/18

27/06/2026
20/06/2026
29 ኛ አመት- ቁጥር 41 - ሰኔ 11/ 2018 በሐረሪ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ በወጣው ጋዜጣ ላይ ለ100/0 ቤት ተመዝጋቢዎች የወጣ ማስታወቂያ
18/06/2026

29 ኛ አመት- ቁጥር 41 - ሰኔ 11/ 2018 በሐረሪ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ በወጣው ጋዜጣ ላይ ለ100/0 ቤት ተመዝጋቢዎች የወጣ ማስታወቂያ

10/05/2026
የሀረሪ ክልል ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ “ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ/ኤድስ መላሸን ዘላቂነት እናረጋግጥ!!" በሚል ርዕስ  ለሰራተኞች ና ለ...
09/05/2026

የሀረሪ ክልል ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ “ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ/ኤድስ መላሸን ዘላቂነት እናረጋግጥ!!" በሚል ርዕስ ለሰራተኞች ና ለአመራሩ የግንዛቤ የመስጠት ፕሮግራም ተካሄደ።

የኤች አይቪ/ኤድስ በሽታ የልማት ፀር በመሆኑ ሰራተኞች ሰራቸውን ሲያከናውኑ ችግሩን በአግባቡ ተረድተው ለመከላከል ደግሞ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው እና ሁሉም ስራተኞችና አመራሩ በመከላከል ረገድ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ኮሙኒኬሽንና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ያህያ መሀመድ በመግለፅ የስልጠና መድረኩን የከፈቱት ስሆን።

በመቀጠል የሀረሪ ክልል ሀብኮ የተጋበዙት አሰልጣኝ ራሄል ገብረመድህን ሴቶችና ህፃናት ተጋላጭነታቸው ለኤች አይቪ ተጋላጭነታቸው የከፍ ስለሆነ ዘላቂነትና የማህበረሰብ ችግር ሆኖ እንዳይቀጥል ማህበራዊ ሀላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባ ገልፀዋል።

‎በተጨማሪም በሽታውን ለመከላከል በሚከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች የባሕርይ ለውጥ ሥርፀት ላይ መሻሻል መኖሩን የተመለከተ ሲሆን የባህሪ ለውጥ የማምጣት ተግባር ላይ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ መሰራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የሀረሪ ክልል ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
ግንቦት 01/2018

07/05/2026
27/04/2026

Address

Harar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30
Saturday 08:00 - 12:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Housing Development & Government Construction Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share