ADAL PRESS 405

ADAL PRESS 405 Beware of speaking too much, for it increases mistakes and engenders boredom.

ከ5 አመት በፊት ስለ ሶፍ ኡመር
22/10/2025

ከ5 አመት በፊት ስለ ሶፍ ኡመር

አላህ ጥራትና ልዕልና ይገባው ፣ ደጋግ ባሮቹን ትውልድ እንዲማርበት ስማቸውን ከፍ ያደርገዋል ።
ሶፍ ዑመር ዋሻ

22/10/2025

❶❾
በኢትዮጲያ ከሚገኙት ሁሉ ታላቁ ዋሻ ነው። ከአፍሪካም እንዲሁ 1ኛ ርዝመት እንዳለው ይጠቀሳል። ከአለም ደግሞ 306ኛ ። የዋሻው ርዝመት 15.1ኪሎሜትር ሲሆን በባሌ ዞን ይገኛል። የዚሁ ዋሻ ስም ሶፍ ዑመር የሙእሚኖች መሪ ዑመር አል ሪዳ (ሼኽ አባዲር) ለምስራቅ አፍሪካ አንድነት ያደረጉትን አስተዋፆ ለመዘከር ስያሜውን ያገኘ መሆኑን "ፈትሑል መዲነቱ ሐረር" ስያሜ ያለው የታሪክ መፅሐፍ ላይ ይገኛል ። ይህ መፅሐፍ አንድ ሚስኪን የአላህ ባሪያ የነበረ ሶፊ ያህያ ነስረላህ በተባለ ሰው የተፃፈ ነው ።አላህ መልካሙን ይመንዳው። መፅሐፉ በአሑን ወቅት ሐረር ሸሪፍ የግል ሙዚየም ውስጥ ይገኛል ። እዚህጋ ማወቅ ያለብን ሶፊ የዲን ማእረግ ስም ነበር ። ሱፊ (ሶፊ) ማለት የነፃነት ተቋም ነው ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሙስሊሞች በየትኛውም አካባቢ የእምነት ነፃነታቸውን ለማስጠበቅ የአው ሶፊ ተቋም ታላቅ መስዋእትነት ከፍሏል ።
ሰይዱና ወመውላና አሚር አልሙዕሚኒን ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም አልጋዚ የመሰሳሰሉትን ሙጃሒዶች ከዚሁ አው ሱፊ (ሶፊ) ሱፊዝም ተቋም የወጡ ጀግና ወጣቶችን መጥቀስ ይቻላል ። (ሶፊ –ሱፊዝም) ትክክለኛ ትርጉሙን ማወቅ እና መረዳት ያስፈልጋል ። ሱፊ (ሱፊዝም) እውነተኛ ትርጉሙ በአጭሩ ለመግለፅ "የዚህች ዱንያ ምቾትና ደስታን በመሸሽ ከራስ ፍላጎት የበለጠ ጊዜውን እና ህይወቱን ለአላህ ዲን የሰጠ ማለት ነው ። በሌላ ቋንቋ ስንመለከተው ሱፊዎች እስልምናን ከልብ የያዙ ናቸው ። ለፍትህ እና ለእኩልነት ይቆማሉ ይታገላሉ ። መልካም ስራ እየሰሩ የተቸገሩት ወገኖችን ይረዳሉ ። በአገሪቱ ወረርሽኝ እና ድርቅ ቢከሰት ግንባር ቀደም ሆነው እርዳታ ያሰባስባሉ ። ለመታየት እና ዝና ለማግኘት ፍላጎት የላቸውም ። የተቸገሩትን ሲረዱ ከአላህ እንጂ ከሰው ምንም አይጠብቁም ። ስለዚህም ሱፊዎች ከአሚሮች ይልቅ ለዲን መሪዎች ትእዛዝ ያስቀድሙ ነበር።
አላህ ይዘንላት አያቴ በየአመቱ ኑር ሁሴን ዚያራ ይሄዱ ነበር እግረ መንገዳቸውን የሶፍ ዑመር ዋሻ ገብተው ፀልየው ይመለሳሉ ። ነገር ግን እኔ ያኔ ልጅ ስለነበርኩ ብዙም አላውቅም ።
ሼኽ ዑመር አልሪዳ(አባዲር) የሐበሻ ሙስሊሞች የእስልምና ተቋማትን በሱፊ(የነፃነት ተቋም) ተቋም ስር አደራጅተዋል ። በዚህ ዘርፍ የተመረጡትስ ምን አይነት ስብእና ተላብሰዋል ? የስራ ሐላፊነታቸውስ ምንድነው? የሚለውን ከዚህ በመቀጠል የምናቀርበው ይሆናል ። የሐረር(አባዲር) ግዛት በውክልና የተመረጡ ሰዎች በሳል እና በመልካም ስነምግባር የተመሰከረላቸው ነበሩ ። አንድ ሰው ለመሪነት እጩ ሲቀርብ በስነምግባር (ጠንካራ ኢማን ያለው) ሲሆን ነው። ስራ ላይ አሚሮች ከማገልገል ባለፈ በሔዱበት አካባቢ የእስልምና ትክክለኛ የአላህ ዲን መሆኑን ያስተምራሉ። እነዚያ ኡለሞች የእስልምና ሃይማኖትን በማስተማር ግዳጃቸውን ከዳር በማድረስ የሚጠበቅባቸውን ሐላፊነት በሚገባ ፈፅመዋል ። ከሕዝብ ጋር ተዋህደዋል ። ተጋብተዋል። የእስልምናን ስልጣኔ አስፋፍተዋል ። ለዚህም ምስክርነት በተለያዩ የሐበሻ አካባቢዎች ይገኛል ። ለምሳሌ በአው አባዲር ዘመን ኑር ሁሴንን ወደ ባሌ ተልከው የእስልምና ኃይማኖት አስተምረዋል ።ወሊዩላህ ኑር ሑሴን የዲን ተልዕኮ በሚገባ ፈፅመው በሚያስተምሩበት አዋች ውስጥ ተቀብረዋል ። አሚር አብዱልሸኩር ዘመን በርካታ መስጂድ እና የቁርዓን ትምህርት ቤቶችን በዙሪያው ተገንብተዋል። ሶፍ ዐመር ዋሻ የእምነት ስፍራቸው ነበር ። ሶፍ ኡመር ዋሻ እጅግ ድንቅ የአላህ ተፈጥሮ ነው። ወሊዩላህ ኑር ሁሴን (ባሌ) ዘመን ሙስሊሞች በዋሻው ውስጥ ተሰብስበው የአላህን ፍጥረት ያደንቃሉ አላህን ያወድሱ ነበር ።

ዛሬ አንባቢ የሆነ ሰው ነገ መሪ ይሆናል
15/09/2025

ዛሬ አንባቢ የሆነ ሰው ነገ መሪ ይሆናል

15/09/2025

ከጥበብ የበለጠ ሀብት የለም፣ ከድንቁርና የበለጠ ድህነት የለም።
ኢማም ዐሊ ረ. ዐ

بسم الله الرحمن الرحيم
15/09/2025

بسم الله الرحمن الرحيم

11/09/2025

"Do not lose hope, nor be sad"
Quran 3:139

ጭንቀትህ ሰዎች እንዲወዱህ አይሁን!የሰው ልጅ ልቡ ተቀያያሪ ነው፣ ዛሬ የወደደህ ነገ ይጠላሀል ፣ ጭንቀትህ የሰዎቹ ጌታ(አላህ) እንዲወድህ ብቻ ይሁን!እሱ ከወደደህ የሰዎችን ልብ አንተን እን...
09/09/2025

ጭንቀትህ ሰዎች እንዲወዱህ አይሁን!
የሰው ልጅ ልቡ ተቀያያሪ ነው፣ ዛሬ የወደደህ ነገ ይጠላሀል ፣ ጭንቀትህ የሰዎቹ ጌታ(አላህ) እንዲወድህ ብቻ ይሁን!
እሱ ከወደደህ የሰዎችን ልብ አንተን እንድትወድ ያደርጋታል።

09/09/2025

አንድ የኢትዮጵያ አባት እንዳሉት
እኛ ስንኖር ሰዎች ስናርፍ አፈር ስናልፍ አገር እንሆናለን ። የትኛውም የኢትዮጲያዊ ክቡር ስጋና ደም በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል አፈር ሆኖ ታገኙታላችሁ። እኛ ኢትዮጵያውያን ስንኖር እንደ ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ እንሆናለን። ኢትዮጵያ የሁላችንም አገር የሁላችንም ቤት ናት። በአንድ አገር ውስጥ የሃሳብ ልዩነት ይኖራል የሃሳብ ልዩነት እርግማን አይደለም ። ልዩነት እንዳለ ሆኖ በመደማመጥ መርህ የተመሰረተ መግባባት ስንችል የሃሳብ ልዩነት በረክት ይዞልን ይመጣል ። በሃሳብ ግጭት ውስጥ መፍትሔ ይገኛል በመተባባር ውስጥ ሃይል አለ ስንደመር እንጠነክራለን አንድነት የማይፈታው ችግር አይኖርም አገር ይገነባልና። ያለችን አንድ ኢትዮጵያ ነች ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት በላይ አገራዊ አንድነት ይበልጣል ። አንድነት ማለት ግን አንድ አይነተኛነት ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል ። አንድነታችን ልዩነታችንን ያቀፈ ብዙሃንነታችን በሕብረ ብሄራዊነት የደመቀ መሆን አለበት ።

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከመጠናቀቁ በፊት የተለጠፈ ፖስት ነው። ዛሬ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በማየታችን አልላህ ይመስገን
09/09/2025

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከመጠናቀቁ በፊት የተለጠፈ ፖስት ነው።
ዛሬ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በማየታችን አልላህ ይመስገን

የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ ይህን ይመስላል ። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የአንድነት መገለጫ እንደጀመርነው ____ዋለን።

 ​ ​ ​ ​ ​
03/09/2025






03/09/2025

Address

Harar

Telephone

+251982563984

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ADAL PRESS 405 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ADAL PRESS 405:

Share