Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/

  • Home
  • Ethiopia
  • Harbu
  • Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/

Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/ Information communication

በከሚሴ ከተማ በተካሄደው ጨዋታ     1-ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ዋንጫውን ወሰደ🏆🏆🏆
19/07/2026

በከሚሴ ከተማ በተካሄደው ጨዋታ
1-ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ዋንጫውን ወሰደ🏆🏆🏆

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!!በደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ከተማ አስተዳደር በየሳምንቱ የሚካሄደው የፅዳት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በሀርቡ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር አካል በሆ...
19/07/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!!

በደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ከተማ አስተዳደር በየሳምንቱ የሚካሄደው የፅዳት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሀርቡ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር አካል በሆነው የፅዳት ዘመቻ ዛሬም የከተማው አመራሮች ፣ወጣቶች እና በጎ ፍቃደኞች ተሳትፎ ተከናውኗል።

ዘመቻው የከተማዋን ንፅህና ለማሻሻል፣ የአካባቢ ውበትን ለማጎልበት እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ የንፅህና ባህልን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት...
17/07/2026

በኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ እና ደስታ ተገኝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም 105 ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ በመውሰድና ከ188 ሚሊየን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብሰብ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የቆዩ በመሆናቸው ከዱባይ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ሥር ውለው ለሀገራችን ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርጓል ብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ዱባይ ተቀምጠው ሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት ወጣቶችን በመመልመል ወደ ዱባይ በመላክ፣ በተዘጋጀ የማገቻ ቦታ በማቆየት፣ በተለይ በሴቶች ላይ ጥቃት በማድረስና በማሰቃየት ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽሙ የቆዩ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ፌደራል ፖሊስም ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በተቀናጀ መንገድ ወንጀሉን ሲፈፅሙ በቆዩት ተጠርጣሪዎችና በግብረአበሮቻቸው ላይ የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ከዱባይ ፖሊስ ጋር በትብብር በመስራት በቁጥጥር ሥር ውለው ለሀገራችን ተላልፈው እንዲሰጡ አድርጓል ነው ያለው።

ተጠርጣሪዎቹ ሰውን ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው፣ በሀገር ውስጥ ያለው ቡድን ከውጪ ካለው ቡድን ጋር ትስስር በመፍጠር “በተለያዩ ኩባንያዎች እናስቀጥራችኋለን’’ በማለት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ዜጎችን በመመልመል፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና ያልተገባ ተስፋ በመስጠት ለኪሳራና ጉዳት ዳርገዋል።

በዚህም ከአንድ ሰው ከ320 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር በመቀበል ማታለያ የቱሪስት ቪዛ አዘጋጅተው በመላክ፣ በሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው በተከፈተ የባንክ አካውንት ገንዘቡን በኢትዮጵያ ብር፣ በድርሃም እና በሪያል ገቢ የሚያስደርጉ መሆናቸውን ፖሊስ ደርሶበታል።

ገንዘቡን የከፈሉ ተጎጂዎች ዱባይ እንደገቡ በጉልበት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ፣ ከተጎጂዎች "ኮሚሽን" በሚል ተጨማሪ ገንዘብ በማስከፈል እንዲሁም የሁለት ወር የቱሪስት ቪዛ ሲያልቅ "የሁለት ዓመት የመኖሪያ ፍቃድ እናሰጣችኋለን፤ ካልከፈላችሁ ግን ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳላችሁ" በማለት በአንድ ሰው 1 ሺህ 200 ድርሃም እንዲከፍሉ በማድረግ ግፍና ስቃይ ሲያደርሱ ቆይተዋል ብሏል ፖሊስ።

ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎችን ከዱባይ ኤርፖርት ከተቀበሉ በኋላ ሰዎችን የሚያከማቹበት ቦታ በመውሰድ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ በርካታ ወንዶችንና ሴቶችን በማገት ለከፍተኛ ርሃብ እና እንግልት እንዲሁም ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲያደርሱባቸው መቆየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ሆነው ዱባይ ካሉት ግብረ-አበሮቻቸው በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ሰዎችን መልምሎ በመላክና የባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያሰባሰቡ የነበሩ 1ኛ ብዙአየሁ አውግቸው እና 2ኛ ራህመት አበበ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራውን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጿል።

ፖሊስ ምርመራውን ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች ተጠቅሞ ይህንን ውስብስብና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀል ለማጣራት እንዲሁም በእነዚህ ተጠርጣሪዎች አማካኝነት ከሀገር ወጥተው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸው ከነበሩ ግለሰቦችና ተጎጂዎች ካሉበት ዱባይ የቀጥታ ቨርቹዋል የምስክርነት ቃላቸውን በመቀበል ላይ ይገኛል።

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ15 ቀናት ውስጥ የዝግጅት ምዕራፍን ጨምሮ የ52 በመቶ አፈጻጸም አስመዘገበ።በደቡብ ወሎ ዞን ዘንድሮ እየተገበረ የሚገኘው የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገል...
17/07/2026

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ15 ቀናት ውስጥ የዝግጅት ምዕራፍን ጨምሮ የ52 በመቶ አፈጻጸም አስመዘገበ።

በደቡብ ወሎ ዞን ዘንድሮ እየተገበረ የሚገኘው የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በተጀመረ በ15 ቀናት ውስጥ ከተቀመጡት አጠቃላይ ግቦች መካከል ከ52 በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉን ተገልጿል።

የዞኑ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ግብረ ኃይል ባካሄደው የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ እንደተመለከተው፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሰማሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ከ626 ሺህ በላይ የሚሆኑቱ ወጣቶች ናቸው። በመርሃ ግብሩ ከተለዩት 17 ዋና ዋና ተግባራት ውስጥም በ16ቱ ላይ ሥራ መጀመር ተችሏል።

በትምህርት ዘርፍ፦ በ126 ትምህርት ቤቶች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት ታቅዶ፣ እስካሁን በ74 ትምህርት ቤቶች 3 ሺህ 456 ተማሪዎችን ማስተማር ተጀምሯል። በተጨማሪም 1 ሺህ 100 ደርዘን ደብተር እና 125 ፓኮ እስክርቢቶ ተሰባስቧል።

በጤና ዘርፍ፦ ለ6 ሺህ 332 ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለ5 ሺህ 566 ሰዎች ተደራሽ የተደረገ ሲሆን፣ ከታቀደው 4 ሺህ 200 ዩኒት የደም ክምችት ውስጥ 830 ዩኒት ደም ተሰባስቧል።

በአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ እና ጥገና፦ ለመጠገን ከታቀዱት 2 ሺህ 532 ነባር የአቅመ ደካሞች ቤቶች ውስጥ 148ቱ የተጠገኑ ሲሆን፣ ከ1 ሺህ 277 አዳዲስ ቤቶች ግንባታ ዕቅድ ውስጥ ደግሞ የ214ቱ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል።

በልማትና ማኅበራዊ ድጋፍ፦ በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት 28 ሺህ 400 የፍራፍሬ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ ለ8 ሺህ 750 ዝቅተኛ ነዋሪዎችም የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በባለፉት ቀናት በተደረገው አጠቃላይ አፈጻጸም 16 ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በአንጻሩ መሐል ሳይንት፣ ደላንታ፣ አምባሰል፣ አምሓራ ሳይንት እና ወረኢሉ ወረዳዎች ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ መሆናቸው በግምገማው ተገልጿል።

የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢ አቶ ተስፋ ዳኛው በጥቅል አፈጻጸሙ የታየውን መሻሻል አድንቀው፣ ይሁንና በየወረዳዎቹና በተቋማት መካከል ሰፊ የአፈጻጸም ልዩነት መኖሩን ጠቁመዋል።

ኃላፊው አክለውም የታችኛው መዋቅር ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ሊደገፍ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ የተጀመሩ የቤት ግንባታዎችና ሌሎች ተግባራት ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ ብርቱ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በታቀደው አጭር ጊዜ ውስጥ "ሞዴል ቀበሌዎችን" የመፍጠር ግብ እንዲሳካ እና የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ፈጥኖ ወደ ሥራ እንዲገባም አቶ ተስፋ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

*****
ደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን

 #ትውልድ ግንባታ  #ትምህርት #
16/07/2026

#ትውልድ ግንባታ #ትምህርት #

“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተዛባ ታሪክን የመቀየር ጉዳይ ነው” — አቶ አሊ መኮንን የደቡብ ወሎ ዞን የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ከተረጂነ...
16/07/2026

“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተዛባ ታሪክን የመቀየር ጉዳይ ነው” — አቶ አሊ መኮንን

የደቡብ ወሎ ዞን የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገውን የሽግግር ሂደት አፈጻጸም በዝርዝር ገመገመ።

ይህ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው ሽግግር አገር በውጭ እርዳታና ተመጽዋችነት ላይ ያላትን ጥገኝነት ለማስወገድ፣ የኢኮኖሚ ነፃነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ክብር በዘላቂነት ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

ለዚህም ስኬታማነት በደቡብ ወሎ ዞን አምስት ፍኖተ ካርታዎችና ልዩ ልዩ ፓኬጆች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር መገባቱ ተጠቅሷል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑ በርካታ ክፍተቶች በግልጽ ተለይተው ቀርበዋል፡

ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተፈናቃዮች፣ የሴፍተኔት ተጠቃሚዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በትክክል የመለየት ሥራ በሚፈለገው ልክ አለመከናወኑ ተጠቁሟል።

ከማኅበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት በማድረግ ረገድ የታዩ እንቅስቃሴዎች አጥጋቢ ባለመሆናቸው፣ በጉዳዩ ላይ ሙሉ መግባባትና መተማመን መፍጠር አልተቻለም።

ተረጂዎችን በራስ አቅም ለመደገፍና ለማብቃት የሚያስፈልጉ የእርሻ ዝግጅት፣ የጥሬ ገንዘብ፣ የእህል መጋዘንና ሌሎች መሠረታዊ ግብዓቶችን በማሰባሰብ ረገድ ውስንነቶች ታይተዋል።

ተግባሩ ከዞን እስከ ወረዳ ባሉ የተለያዩ ተቋማት የሚፈጸም ቢሆንም፣ በቂ ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት የመምራትና የመከታተል ክፍተት በመኖሩ አጠቃላይ ውጤቱ ከሚጠበቀው በታች ሆኖ ተገኝቷል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን እንደገለጹት፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው ሽግግር ለደቡብ ወሎ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተዛባ ታሪክን የመቀየር ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ነው።

በመሆኑም በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ባለድርሻ አካላት ይህንን እውነት በውል ተገንዝበው በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዚህ ዓመት ከዓየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የክረምቱ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ኃላፊነታችንን ድርብ ያደርገዋል ሲሉም አመላክተዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም፣ ከዞን እስከ ወረዳ የሚገኙ
የግብረ ኃይሉ አባላትና ተቋማት የተዘጋጁትን ፍኖተ ካርታዎችና ፓኬጆች መሠረት በማድረግ ግልጽ ዕቅድ አውጥተው በሙሉ አቅማቸው መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመሆኑም በቀጣይ ሳምንት እያንዳንዱ ተቋም አሁን ካለው አፈጻጸም ተሻሽሎ በመውጣት፣ ፈጣን፣ ተጨባጭና ትርጉም ያለው ለውጥ ማስመዝገብ እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
South Wollo Zone Gov. Communication Dept.

 በሀርቡ ከተማ አስተዳደር በክረምት የማህበረሰብ አቀፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ አካል የሆነውን የማጠናከሪያ ትምህርት በዛሬው ዕለት በጃሮታ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጀምሯል።...
16/07/2026



በሀርቡ ከተማ አስተዳደር በክረምት የማህበረሰብ አቀፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ አካል የሆነውን የማጠናከሪያ ትምህርት በዛሬው ዕለት በጃሮታ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የደቡብ ወሎ ዞን ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ሶፊያ እብሬ
የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ተ/ም/ዋና ከንቲባ አቶ መሀመድ ሹመት፣የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይማም ሰይድ፣የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሪት አምሳል መሀመድ እንዲሁም ሌሎች የከተማው አመራሮችና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

​የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለህብረተሰብ ዕድገት!
​ #ትምህርት

"ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሰዎችንና አገልግሎቶችን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ ለውጤታማነቱ መሥራት ግድ ይላል" — አቶ አሊ ይማም ደሴ ፣ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬ...
15/07/2026

"ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሰዎችንና አገልግሎቶችን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ ለውጤታማነቱ መሥራት ግድ ይላል" — አቶ አሊ ይማም

ደሴ ፣ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን)

በደቡብ ወሎ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጋ የኅብረተሰብ ክፍል የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ።

የዞኑ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ግብረ ኃይል የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም በገመገመበት መድረክ ላይ እንደተመለከተው፣ በዞኑ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ለማድረግ በንቅናቄ ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ግብርና፣ ትምህርት፣ መሬት፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ዕቅድና አፈጻጸማቸውን በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በቀረበው ሪፖርት መሠረት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተሠራው የተቀናጀ ሥራ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ችሏል።

11 ወረዳዎች ከዕቅዳቸው አንጻር ሙሉ በሙሉ እና ከዚያም በላይ ያሳኩ መሆናቸው በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ተቋማዊ ክትትሉ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ አንዳንድ ተቋማት ተናበው ለመሥራት ያሳዩት ተነሳሽነትና ጥረት እጅግ አበረታች ነው።

ከዚህም በተጨማሪ የከተማ ነዋሪዎች ስለ ቴክኖሎጂው የተሻለ ግንዛቤ በመኖሩ በከተሞች ያለው አፈጻጸም ከፍተኛ ነው።

በአንጻሩ በአርሶ አደሩና በሕፃናት ዙሪያ የሚፈለገውን ያህል ውጤት አልተመዘገበም። ለዚህም በየወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ አመራሮች የጋራ አመራር፣ ተገቢ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ረገድ ውስንነቶች መኖራቸው እንዲሁም የቅንጅት እጥረት በምክንያትነት አቶ አሊ ጠቅሰዋል።

ምክትል ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የነዋሪዎችን ማንነት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ለማረጋገጥ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍና የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ" ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የተዘጋጀ ብሔራዊ ሥርዓት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሰዎችን እና አገልግሎቶችን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። በቀጣይ ማንኛውም የመንግሥትም ሆነ የሌሎች ተቋማት አገልግሎቶች ያለ ፋይዳ መታወቂያ ተደራሽ ማድረግ አይቻልም። በሌለ ድልድይ ደግሞ አገልግሎት መስጠትም ሆነ መቀበል አይታሰብም ሲሉ አብራርተዋል አቶ አሊ፡፡

አቶ አሊ በመጨረሻም የሕዝቡን የአገልግሎት ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስና መላውን የኅብረተሰብ ክፍል የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ለማድረግ፣ አመራሩ ከዕቅድ ባለፈ በጋራና በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባው አጥብቀው አሳስበዋል።

ፋይዳ (Fayda) የነዋሪዎችን ባዮሜትሪክ (የጣት አሻራ እና የፊት ገጽታ) እንዲሁም ዲሞግራፊክ መረጃዎችን በመጠቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ ልዩ መለያ የሚሰጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል።

"ምክክሩ ጠንካራ እና አስተማማኝ ሀገር ለመገንባት አዲስ ምእራፍ የሚከፍት ነው" ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በም...
15/07/2026

"ምክክሩ ጠንካራ እና አስተማማኝ ሀገር ለመገንባት አዲስ ምእራፍ የሚከፍት ነው" ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በምክክር ጉባኤው መክፈቻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በምክክር ጉባኤው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ እንዳሉት ምክክሩ ጠንካራ እና አስተማማኝ ሀገር ለመገንባት አዲስ ምእራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ታላቅነት ለማስቀጠል እንቅፋት የሚኾኑ ጉዳዮችን ለመፍታትም ያገለግላል ነው ያሉት።

ጉባኤው የሀገራችንን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ የጉዞ አቅጣጫ የሚያቀና፣ ለቀጣዩ ትውልድም ጠንካራ እና አስተማማኝ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል አዲስ ምእራፍ ከፋች ነው ብለውታል።

የኢትዮጵያን ታላቅነት ለማስቀጠል እንቅፋት የሆኑ በርካታ አለመግባባቶች የዜጎችን እና የሀገርን ሰላም እየፈተኑ ይገኛሉ። እነዚህን ስር የሰደዱ ችግሮች በኀይል ጊዜያዊ ማስታገሻዎች ሳይኾን በምክክር መፍታት ይገባል ነው ያሉት። ግልጽ፣ ታማኝ እና ሳይንሳዊ ሀገራዊ ምክክር ማድረግም ወሳኝ መኾኑን አመላክተዋል።
***********
ደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን

 የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት በሰርግ ግዜ የሚተኮስ ርችትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ። ስለ ህገ-ወጥ የርችት ተኩስ አፈጻጸም ላነሳችሁት ጥያቄ እና አስተያየት ለማህበረሰቡ ምስጋና በ...
15/07/2026


የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት በሰርግ ግዜ የሚተኮስ ርችትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ።

ስለ ህገ-ወጥ የርችት ተኩስ አፈጻጸም ላነሳችሁት ጥያቄ እና አስተያየት ለማህበረሰቡ ምስጋና በማቅረብ ህጉ በተግባር ላይ ማዋል መጀመሩን ፅ/ቤቱ ገልጿል።

ሀምሌ 8/2018ዓ.ም

የከተማ አስተዳደሩና የፖሊስ ጽ/ቤት ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር ለመቆጣጠር እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን በይፋ ማረጋገጥ እንወዳለን ሲል ፖሊስ ፅ/ቤቱ አሳውቋል።

ለአብነት ያክል በሀርቡ ከተማ 02 ቀበሌ በተካሄደ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ህገ-ወጥ የርችት ተኩስ በመፈጸም የህብረተሰቡን ሰላም የረበሹ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ርምጃ ተወስዷል።

እነዚህ ግለሰቦች በቀበሌው ማኅበራዊ ፍርድ ቤት ቀርበው፣ እንደየድርጊታቸው ክብደት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

በሌላ መልኩ በቀጣይም ህጉን በመተላለፍ በሰርግ፣ በልደት ወይም በሌሎች ዝግጅቶች ያለፈቃድ ርችት በመተኮስ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚያውክ ማንኛውም አካል ከዚህ ቀደም በኮማንድ ፖስቱ እንደተወሰነው እስከ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የሚደርስ ቅጣትና ተጨማሪ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት በጥብቅ እናሳስባለን።

ህብረተሰቡም ሰላሙን በጋራ እንዲጠብቅ እና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የሀርቡ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት
🇪🇹 ሰላማችንን በጋራ እንጠብቃለን!

Address

Harbu

Telephone

+251909257361

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share