13/06/2026
!! 🇪🇹
#በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በ2018 ዓ.ም ከ200 ሄክታር በላይ የፍራፍሬ ልማት ኮሪደር ለመፍጠር የተያዘው ታላቅ ዕቅድ ወደ ተግባር የሚገባበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ለልማቱ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በተሳካ ሁኔታ እየተጠናቀቁ ሲሆን፣ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሙሉ የትግበራ ምዕራፍ ይገባል።
ይህ የፍራፍሬ ልማት ኮሪደር የአካባቢውን የምርት አቅም በማሳደግ፣ የአርሶአደሮችን ገቢ በማሻሻል፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲኖረው በቅንጅት እየተሰራበት ይገኛል።
!
!