Harari

Harari Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Harari, Government Organization, Harer.

ክብርት  ወ/ሮ አዳነኝ  አቤቤ በሀረሪ ባህላዊ አልባሳት ተንቆጥቁጠው
24/05/2022

ክብርት ወ/ሮ አዳነኝ አቤቤ በሀረሪ ባህላዊ አልባሳት ተንቆጥቁጠው

ወቅቱን የሚገጽ መርጥ ምስል
24/05/2022

ወቅቱን የሚገጽ መርጥ ምስል

የሀረሪ ብሄረሰብ ልዩ መገለጫ የሆነው የሸዋል ኢድ በአል በመዲናችን አዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት የነበረው ድምቀት በከፊል የሚያሳይ የፎቶ ግራፍ መግለጫሀረሪዎች በመዲናች እንዲህ ፍክት ድም...
24/05/2022

የሀረሪ ብሄረሰብ ልዩ መገለጫ የሆነው የሸዋል ኢድ በአል በመዲናችን አዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት የነበረው ድምቀት በከፊል የሚያሳይ የፎቶ ግራፍ መግለጫ
ሀረሪዎች በመዲናች እንዲህ ፍክት ድምቅ ብለው ውለዋል፡፡
በተለይም ለአመራሮቻችን ከፍተኛ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመዲናችን አዲስ አበባ ለባህል ማእከል ማስገንቢያ ቦታ መዘጋጀቱን በእለቱ አብስረዋል፡፡ክብርት ከንቲባ ላቅ ያለ ክብር ይገባዎታል፡፡የአመራሮቻችን ዲፕሎማሲ...
24/05/2022

ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመዲናችን አዲስ አበባ ለባህል ማእከል ማስገንቢያ ቦታ መዘጋጀቱን በእለቱ አብስረዋል፡፡
ክብርት ከንቲባ ላቅ ያለ ክብር ይገባዎታል፡፡የአመራሮቻችን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስኬት መገለጫም አድርገን እናየዋለን፡፡

የደም ግፊት ቀን በሀረሪ ክልል እየተከበረ ይገኟል።እለቱን በማስመልከትም በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የደም ግፊት ምርመራ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹም ምርመራ በማድረግ የደም ግፊት ውጤታቸውን እንዲያው...
17/05/2022

የደም ግፊት ቀን በሀረሪ ክልል እየተከበረ ይገኟል።
እለቱን በማስመልከትም በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የደም ግፊት ምርመራ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹም ምርመራ በማድረግ የደም ግፊት ውጤታቸውን እንዲያውቁ ተደርጓል፡፡
በሐረሪ ክልል ለአራተኛ ጊዜ የደም ግፊት ቀን የደም ግፊቶን በአግባቡ ይቆጧጠሩ ረጅም እድሜዬ ይኑሩ በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡
በሀረሪ ክልል በተለያዩ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ነፃ የደም ልኬት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
እለቱ በአለም ኣቀፍ ደረጃ ለ5ኛ ጊዜ በሐረሪ ክልል ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

"ዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን።"- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫ...
17/05/2022

"ዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን።"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
ዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስገነዘቡ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ ያሉት አቶ ደመቀ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በተለያየ መንገድ ጫና እየደረሰበት ይገኛል።
እየደረሰ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በኢትዮጵያ ህዝብ ጽናት፣ በዳያስፖራው ተሳትፎ እና በኢትዮጵያ ወዳጆች ትብብር መቋቋም መቻሉን አመልክተዋል።
ለዚህም አስተዋጽኦ ለመላው ህዝብ፣ ለዳያስፖራውና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በጋራ ርብርቡ ጫናዎች የመለዘብ ምልክት ቢያሳዩም ጫናው በመቀጠሉ በትብብር መስራቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
“የዓለም ስርዓት ተገማች ያለመሆን፤ በተለያዩ ፍላጎቶችና የአሰላለፍ ለውጦች ምክንያት የዲፕሎማሲ ስራችን በእጅጉ ፈተና የበዛበት ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን ብለዋል።
ሰላምን ከማረጋገጥ ሂደት ጎን ለጎን በማስገንዘብና በማለዘብ ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነትን አጠናክሮ መቀጠል ይጠይቃል ሲሉ ገልጸዋል።
በጂኦ ፖለቲካ ፍላጎትና በልዩ ልዩ ውስጣዊ ሁኔታዎች ዲፕሎማሲው ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ቀድሞ መንቀሳቀስ የሚፈለግበት ዘመን ላይ መድረሱንም ጠቁመዋል ሲል ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

16/05/2022
16/05/2022
16/05/2022
በሀረሪ ክልል በግብርና ልማት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳ...
16/05/2022

በሀረሪ ክልል በግብርና ልማት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀረሪ ክልል በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ገምግሟል።
የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በውይይቱ ላይ እንዳሉት በክልሉ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በቀጣይ በክልሉ የግብርና ልማት ዘርፍን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት ምክትል ርእሰ መስተዳድሯ በቀጣይም እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን እንዲጠናከሩ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በተለይም የግብርና ስራውን ይበልጥ የማዘመንና ከመኖ፣ ከምርጥ ዘርና ከማዳበሪያ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሻሜ አብዲ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በሰብል፣ በእንስሳት ምርትና ምርታማነትን፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ አጠቃቀም እንዲሁም በመስኖ ግንባታ ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል።
ለበጋ መስኖ ፕሮጀክት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት፤ ለአርሶ አደሩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ መሬቱን አሟጦ እንዲያለማ ከማስቻል እና የገበያ ትስስርን ከመፍጠር አንፃር በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
ዘንድሮው አመት በክልሉ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ቋሚ ኮሚቴ አባላቱም በክልሉ ከሰብል ምርት፣ ከእንስሳት ሀብትና ከተፈጥሮ ሀብት ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ ያሉ አበረታች ተግባራት በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር ክልሉ ከሌሎች ክልሎች ተሞክሮ በመውሰድ በቅንጅት እንዲሰራ አሳስበዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የቋሚ ኮሚቴ አባሉቱ በክልሉ በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በሚመለከት የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር በክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ የተመራ ቡድን ሁለተኛው የከተማ ውሃ አቅርቦት እና ንፅህና  የተከናወኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የመስክ ጉብኝት በማድረግ የስራ መመሪያ ...
16/05/2022

በሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር በክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ የተመራ ቡድን ሁለተኛው የከተማ ውሃ አቅርቦት እና ንፅህና የተከናወኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የመስክ ጉብኝት በማድረግ የስራ መመሪያ አሰተላልፎዋል
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ ከ30 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ የተከናወኑ ፕሮጀክቶች ስራ ያስጀመሩ ሲሆን ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችንም ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቀው ስራ እንዲጀምሩም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የክልሉ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኒ ረመዳን ፕሮጀክቶችን አስመልክተው እንደተናገሩት በክልሉ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተከናወኑ ከነበሩ 17 ፕሮጀክቶች መካከል ሰምንቱ ተጠናቀው በእለቱ ስራ ጀምረዋል።
ቀሪዎቹ ፕሮጀክቶችም ከ95 በመቶ በላይ ተጠናቀዋል ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ በተለይም የድሃ ድሃ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ከማድረግና ክልሉንም ፅዱ ከማድረግ አንፃር ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ከተከናወኑ ፕሮጀክቶችም የጋራ መፀዳጃ ቤቶች፣ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 4 መቶ 9 የድሃ ድሃ እማወራዎችንና አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ የውሃ መሰረተ ልማት መከናወኑንም ገልፀዋል።

የሀረሪ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የፌስ-ቡክ ገጽ
16/05/2022

የሀረሪ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የፌስ-ቡክ ገጽ

Address

Harer

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share