Snnprs Public Service And Human Resource Development Bureau

Snnprs Public Service And Human Resource Development Bureau likes

13/05/2023

ስህተትን ሰርቶ ስህተትን የማያርም ሰው የላቀ ስህተትን ሰርቷል። ካነበብኩት

ሥልጠናዉሂደት
05/03/2018

ሥልጠናዉሂደት

በተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ሥርዓት (ICSMIS) ላይ የኢፌዲሪ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰ/ሚ/ር  ሥልጠና ሰጠ፡፡በኢፌዲሪ  ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ሚ/ር  አማካይነት የለማዉ የተቀናጀ የሲቪ...
05/03/2018

በተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ሥርዓት (ICSMIS) ላይ የኢፌዲሪ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰ/ሚ/ር ሥልጠና ሰጠ፡፡
በኢፌዲሪ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ሚ/ር አማካይነት የለማዉ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ ስራ አመራር መረጃ ሥርዓት ከ2008 እስከ 2010 የበጀት ዓመት ድረስ ቢሮአችንን ጨምሮ በ9 ዞኖች፡ በ1 ከተማ አስ/ር፡ በ1 ልዩ ወረዳና በ34ወረዳዎች በድምሩ በ45 ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ተቋማት በማስፋትና በመተግበር ላይ እንደምገኝ ከቢሮዉ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ የሰዉ ሀብት አሠራርና ሥርዓት በማዘመን የዕለት ተዕለት ተግባራትን ከማኑዋል ይልቅ በሲስተም ዳታቤዝ የታገዘ ዘመናዊ አሠራር የተከተለ እንድሆን ለማስቻል የለማ እነደሆነ የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ሀላፍ ዶ/ር ጌታቸዉ ገልፀዋል፡፡

ለተቋሙ ሠራተኞች እና ለህዝብ ክንፍ አመራሮቾ በተቋሙ ዜጎች ቻርተር እና በህዝብ ክንፍ ሚና: አደረጃጄት፡ አሠራርና በምዘና ሥርዓት ማኑዋል ላይ በይርጋዓለም ከተማ ከየካቲት 23-24/2010 ...
03/03/2018

ለተቋሙ ሠራተኞች እና ለህዝብ ክንፍ አመራሮቾ በተቋሙ ዜጎች ቻርተር እና በህዝብ ክንፍ ሚና: አደረጃጄት፡ አሠራርና በምዘና ሥርዓት ማኑዋል ላይ በይርጋዓለም ከተማ ከየካቲት 23-24/2010 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
በሥልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የቢሮዉ ም/ሀላፍና የመልካም አስ/ር ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፍ የሆኑት ወ/ሮ ፈለቀች ተ/ማሪያም እንደተናገሩት የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት ለተገልጋዮች ፈጣን፡ ቀልጣፋና ፍትሀዊ እንድሆን በማድረግ የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ ሥልጠናዉ ወሳኝ በመሆኑ ሠልጣኞች በንቃት ተከታትለዉ ለተግባራዊነቱ የበኩላቸዉን እንድወጡ አሳስበዋል፡፡

ለክልሉ የህዝብ ክንፍ አመራሮች በህዝብ ክንፍ ሚና፤አደረጃጀት፤አሰራርና ምዘና ስርዓት ማኑዋል ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡በስልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት ም/ቢሮ ሀላፊና የተቋማዊ ለዉጥ...
23/02/2018

ለክልሉ የህዝብ ክንፍ አመራሮች በህዝብ ክንፍ ሚና፤አደረጃጀት፤አሰራርና ምዘና ስርዓት ማኑዋል ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት ም/ቢሮ ሀላፊና የተቋማዊ ለዉጥና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ እንደገለጹት መንግስታዊ አገልግሎትን ቀልጣፋ ዉጤታማና ፍትሀዊ ለማድረግ የህዝብ ክንፉን በተደራጀ ሁኔታ ግንዛቤ በመፍጠር በተቋማት የዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራና ግምገማ ሂደት በንቃት እንዲሳተፍ በማድረግ የዕቅድ አፈጻጸም ዉጤታማነት ማሳደግ፣ ተቋማት በሚሰጡት አገልግሎት የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ እንዲሁም ኪራይ ሰብሳቢነትን በማክስም መልካም አስተዳደርን እዉን ለማድረግ የህዝብ ክንፉ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በማከልም የህዝብ ክንፍ የወከለዉን የህ/ሰብ ክፍል ጥቅም ለማስከበርና የመንግስት ተቋማት የህዝብ ክንፎችን በዕቅድ ዝግጅት በማሳተፍ ፍላጎቱን እንድገልጽበት፣ የምርታማነት አቅሙ እየጨመረ በሂደቱም በባለቤትነት ስሜት በታጀበ ተሳትፎ የዕቅድ ስኬት የሚረጋገጥበትና በዉጤቱም ደግሞ መብቱንና ጥቅሙን ከማስከበር አንጻር የተጠያቂነት ስርዓት የሚያጠናክርበትን ስርዓት በማጠናከር የዕድገትና የለዉጥ ጉዟችን ቁልፍ ተግዳሮት የሆነዉን ኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር፣ የህዝብ መብትና ጥቅም የሚጎዱ ጉዳዮች በተደራጀ ሁኔታ ትግል እንዲደረግ ግንዛቤ የምያዝበት ስልጠና በመሆኑ ሠልጣኞች ሥልጠናዉን በንቃት ተሳትፈዉ ለወከሉዋቸዉ ህብረተሰብ መብትና ጥቅም መከበር በሀላፍነት መንፈስ እንድንቀሳቀሱ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በህዝብ ክንፍ ሚና፤አደረጃጀት፤አሰራርና ሚዘና ስረዓት ማኑዋል ላይ ለክልሉ መንግስት ተጠሪ ከሆኑ የክልል ተቋማት ለተወጣጡ የቢሮ ኃላፊዎችና ከ...
15/02/2018

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በህዝብ ክንፍ ሚና፤አደረጃጀት፤አሰራርና ሚዘና ስረዓት ማኑዋል ላይ ለክልሉ መንግስት ተጠሪ ከሆኑ የክልል ተቋማት ለተወጣጡ የቢሮ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ኃላፊና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፈለቀች ተ/ማሪያም እንደገለጹት ለአንድ ሀገር የልማት ቀጣይነት የልማት ሀይሎችን ማለትም የመንግስት፣ የሲቪል ማህበራት እና የግል ዘርፉን በሙሉ አቅም አስተሳስሮ ማንቀሳቀስ መቻል መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም መንግስታዊ አገልግሎትን ቀልጣፋ፣ውጤታማና ፍትሃዊ ለማድረግ የህዝብ ክንፋን ለማደራጀትና ግንዛቤ ለመፍጠር በተቋማት የዕቅድ ዝግጅት፣የተግባር አፈፃፀምና ግምገማ ሂደት በንቃት እንዲሳተፍ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎችም በበኩላቸው የዝህን አይነት የስልጠና ዘርፎች ፋይዳቸው ከፍተኛ በመሆኑ ቀጣይነት እንድኖራቸውና ተጠናክረው እንድቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

የቢሮዉ ማኔጅመንትአባላት የቢሮዉ ህንፃ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡ ከህንፃ ግንባታ አማካሪ መሀንድስ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
14/02/2018

የቢሮዉ ማኔጅመንትአባላት የቢሮዉ ህንፃ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡ ከህንፃ ግንባታ አማካሪ መሀንድስ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰ/ሀ/ል/ቢሮ እና ተጠሪ ተቋም የሆነዉ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኤጀንሲ ፐብሊክ ሰርቫንት በጥልቀት የመታደስ የዉይይት መድረክ ‹‹ብቁና ዉጤታማ ፐብሊክ ሰርቪሱ ለሀገ...
04/02/2017

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰ/ሀ/ል/ቢሮ እና ተጠሪ ተቋም የሆነዉ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኤጀንሲ ፐብሊክ ሰርቫንት በጥልቀት የመታደስ የዉይይት መድረክ ‹‹ብቁና ዉጤታማ ፐብሊክ ሰርቪሱ ለሀገራዊ ህዳሴ›› በሚል ሰነድ ላይ በ22/05/09 ዓ.ም በመለስ አካዳሚ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡

በዉይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ም/ር/መስተዳድርና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ መለስ ዓለሙ የመድረኩን አስፈላጊነት ሲገልጹ ይህ የተሃድሶ መድረክ በድርጅት ዉስጥ የተለኮሰዉን ተሀድሶ ወደ ህዝቡ ለማድረስ የተጀመረዉ ንቅናቄ አካል መሆኑን አስረድተዉ ፐብሊክ ሰርቫንቱ ከህብረተሰብ ክፍሎች አንዱ በመሆኑ የንቅናቄዉ አካል እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ሀገራችን ባለፉት 25 አመታት ዉስጥ በተለይም በ15 ዓመታት ጉዞ ወደ ለዉጥ እንቅስቃሴ መግባቷን አዉስተዉ ለዉጡን የህ/ሰብ ክፍል በሆነዉ ፐብሊክ ሰርቨንቱ ዉስጥ ማስቀጠል ለመንግስት ተቋማት ዉጤታማነት አስፈላጊ መሆኑን የጋራ ግንዛቤ እንድጨብጥ ለማድረግ ታስቦ ነዉ፡፡
ዓላማዉም ፐ/ሰርቫንቱ ዉጤታማ አገልጋይ እንዲሆን በማድረግ ለቀጣይ ተልዕኮ በመዘጋጀት የአመለካከትና የተግባር ችግሮች ተለይቶ ባለቤት አግኝቶ መማርና መስተካከል ስላለበት ነዉ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
አያይዘዉም ከዉይይቱ ቦኃላ የፐብሊክ ሰርቪሱ አባላት
 የልማታዊ መንግስት ባህሪያትና ተልዕኮዎችን አዉቀዉ የራሳቸዉን ገንቢ ሚና እንድጫወቱ ማስቻል
 በድክመቶች ዙሪያ በመግባባት ጉዳቱን ማሳየትና ድክመቶችንና ጉድለቶችን ማረም
 በእኩል ዕድልና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ ግልጽነትን መፍጠር
 በተቋሙ አመራርና ሰራተኛች መካከል ያለዉ ግንኙነት ጤናማና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ የለዉጥ ሀይል ስለመሆናቸዉ መተማመን
 በለዉጥ ስራዎችና መሳሪያዎች ጠቀሜታ ላይ በመተማመን ለተፈጻሚነታቸዉ ዝግጁ ማድረግና ተቋማዊ የሆነ ቋሚ አሰራር ወደ መሆን ለመሸጋገር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Address

Hawassa

Telephone

0462123120

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Snnprs Public Service And Human Resource Development Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Snnprs Public Service And Human Resource Development Bureau:

Share