15/08/2026
የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት አባላት የገጠር ለውጥ ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ በተመለከተ የመስክ ምልከታ አደረጉ
ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማኔጅመንት አባላት የገጠር ለውጥ ማዕከላት ያሉበትን የልማት ደረጃ፣ የተከናወኑ ስራዎችንና ቀጣይ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
በጉብኝቱ የመጀመሪያ ዙር የገጠር ለውጥ ማዕከላት ሥራ ተጠናቆ ርክብክብ መፈጸሙ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጊዜ የተጀመረው የለኩ ክላስተር ማዕከል ሥራ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁና በቅርቡ የሚመረቅ መሆኑ ተመላክቷል።
መርሃግብሩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ የመስክ ምልከታው የገጠር ለውጥ ማዕከላትን የበለጠ ተግባራዊ፣ ውጤታማና ተጨባጭ የልማት በረከት የሚያመጡ ማዕከላት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
የገጠር ለውጥ ማዕከላት ሁለተኛ ዙር የመሠረተ ልማት ዝርጋታ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ በምልከታው መረጋገጡን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ሥራውን ከዳር ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
በምልከታው የኃይል አቅርቦትን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚሰሩ ቀሪ የመሠረተ ልማት ስራዎች አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፤ በኮርፖሬሽኑ እየተገነባ የሚገኘው የሞሮቾ ነጋሻ ጤና ኬላ እና የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤትም ምልከታ ከተደረገባቸው ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
For more information:- Visit us on
Website: www.sidaamaipdc.com
Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
YouTube: youtube.com/
Tiktok:
https://www.tiktok.com/.ipdc