Visit Sidama

Visit Sidama Welcome to Sidama Land of Vibrant Culture & Coffee

15/03/2026

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሶረሳ ጉዱማሌ የፈረስ ጉግስ

15/03/2026

የፊቼ ጫምባላ በዓል በሶረሳ ጉዱማሌ በቄጣላ

የፊቼ-ጫምባላላ በዓል በታላቁ ሶረሳ ጉዱማሌ  በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል ፡፡አይዴ ጫምባላላፊቼ ጄጂ ጀጂ
15/03/2026

የፊቼ-ጫምባላላ በዓል በታላቁ ሶረሳ ጉዱማሌ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል ፡፡

አይዴ ጫምባላላ
ፊቼ ጄጂ ጀጂ

እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ በዓል  አደረሰን/አደረሳችሁ!‎Ayidde Cambalaalla!መጋቢት 5/2018 ዓ/ምየ‎ሲዳማ ብሔር የዘመን  መለወጫ "ፍቼ ጫምባላላ" "ፊጣራ " በሲዳማ ባህል አዳራሽ...
14/03/2026

እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ በዓል አደረሰን/አደረሳችሁ!
‎Ayidde Cambalaalla!

መጋቢት 5/2018 ዓ/ም

የ‎ሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ "ፍቼ ጫምባላላ" "ፊጣራ " በሲዳማ ባህል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው፡

የሲዳማ ውብ ባህላዊ መገለጫ የሆነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ሰላምና መከባበር፣አብሮትና መቻቻል፣ይቅርባይነትና እርቅ በአንድ ላይ የተጋመዱበት የበጎነት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ደማቅ ባህል ነው።
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፍቼ ጫምባላላ በዓል የሲዳማ አባቶች(አያንቶዎች) የስነ-ፈለክ ዕውቀት እና ጥበብ ላይ ተመስርተው ዘመንን በልዩ የወራት፣የቀናትና የሳምንታት ቀመር አስልተው ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር ያስተላለፉት የሀገራችን አኩሪ መገለጫ እና የዓለም ህዝቦች ውብ ቅርስ ሆነ በማይዳሰስ ቅርስነት በUNESCO የተመዘገበ ታላቅ በዓል ነው።፡
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን/አደረሳችሁ
ዓመቱ የሰላም ፣የፍቅር፣ የአንድነት ፣የመተባበር፣ የልማትና የዕድገት ዓመት ይሁንልን፡፡
አይዴ ጫምባላላ!!!

እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ -ጨምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!! በዓሉ የአብሮነት፣የሰላም፣የፍቅር እና የብልጽግና    ይሁንልን::Ayiidde Cambalaallአይዴ ...
14/03/2026

እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ -ጨምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!!
በዓሉ የአብሮነት፣የሰላም፣የፍቅር እና የብልጽግና ይሁንልን::
Ayiidde Cambalaall
አይዴ ጫምባላላ
ሲዳማን ይጎብኙ

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን !!!ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ነገና ከነገ ወዲያ የሚከበረዉን የፊቼ- ጫምባላላን  በዓል በማሰመልከት የተለያዩ  የካርኒቫል ትዒይቶች  ተካሄደ፡፡
13/03/2026

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን !!!
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ነገና ከነገ ወዲያ የሚከበረዉን የፊቼ- ጫምባላላን በዓል በማሰመልከት የተለያዩ የካርኒቫል ትዒይቶች ተካሄደ፡፡

"ኑ ወደ ሲዳማ እንሂድ" በሚል መሪ ቃል እውቅ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች  የተሳተፉበት  በዉብቱዋ ሀዋሳና ይርጋዓለም አካባቢን ሲጎበኙ፡፡የሲዳማ ዘመን መለወጫ "ፊቼ ጫምባላላ" በመጪው ቅዳሜና ...
12/03/2026

"ኑ ወደ ሲዳማ እንሂድ" በሚል መሪ ቃል እውቅ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተሳተፉበት በዉብቱዋ ሀዋሳና ይርጋዓለም አካባቢን ሲጎበኙ፡፡

የሲዳማ ዘመን መለወጫ "ፊቼ ጫምባላላ" በመጪው ቅዳሜና እሁድ (መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና በዉብቱዋ ሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶችና ካርኒቫሎች ይከበራል ፡፡

የሲዳማ አባቶች ዘመንን የመቁጠር ጥበባቸውንና ሀገር በቀል ዕውቀታቸውን ለትውልድ ያስተላለፉበት ይህ በዓል፣ የሰላም፣ የዕርቅና የአንድነት ተምሳሌት ነው።

‎​ፊቼ-ጫምባላላ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ይቅርታ የሚደረግበትና የአብሮነት እሴት የሚጎለብትበት ታላቅ ዕለት ነው።
ኑ ፊቼ-ጫምባላላን በጋራ እናክብር
ሲዳማን እንወቅ
ሲዳማን ይጎብኙ ሀገርዎን ይወቁ

"ኑ ወደ ሲዳማ እንሂድ" በሚል መሪ ቃል  የቱሪዝም ንቅናቄ ፕሮግራም ተዘጋጀ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ የኪነጥበብ ቡድን  በውቧ ሐዋሳ ከ...
12/03/2026

"ኑ ወደ ሲዳማ እንሂድ" በሚል መሪ ቃል የቱሪዝም ንቅናቄ ፕሮግራም ተዘጋጀ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ የኪነጥበብ ቡድን በውቧ ሐዋሳ ከተማ እና በተለያዩ የክልሉ የቱሪስት መዳረሻዎች በመዘዋወር፣ ከእንግዳ ተቀባዩ የሲዳማ ሕዝብ ጋር ባህላዊ እሴቶችን ለመታደምና ለማስተዋወቅ ወደ ውብቱዋ ሀዋሳ ሲገቡ እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ፡፡
የቱሪዝም ንቅናቄ ፕሮግራም የተዘጋጀው መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት የሚከበረውን የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነው "ፍቼ ጫምባላላ" በዓል ምክንያት በማድረግ ሲሆን ፕሮግራሙ በሲዳማ‎​ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ እና ‎​ጎልደን ሬሽዮ (Golden Ratio) በተሰኘ ተቋም ነው ፡፡
ሁላችሁም ኑ ፊቼ -ጫምባላላን በጋራ እናክብር፡፡
ሲዳማን እንወቅ
'አይዲ ጫምባላላ'

SDQ-Mootimma WTIB sooreessi kalaa Jaggo Agenyohu Sidaamu Daga diru soorro Fichee-Cambalaallate ayyaana lainohunni uyno x...
11/03/2026

SDQ-Mootimma WTIB sooreessi kalaa Jaggo Agenyohu Sidaamu Daga diru soorro Fichee-Cambalaallate ayyaana lainohunni uyno xawishsha.

Badheessa 02/2018 M.D
Hawaasa

SDQ-Mootimma WTIB sooreessi kalaa Jaggo Agenyohu UNISCOte maareekkantunkunni tayxe 11ki diro wo'minoseti baxxino garinni ayirrinsanniha ikkinota ikkase xawishsha uyno.

Sidaamunniti albi geerri (Ayyaanto) beeddahenna agana la'e kiiratenni ayyaanu ayirrisamanno barra Badheessa 05/2018 M.D Fiixaari ayyaana ayirrinsannitanna Badheessa 06/2018 M.D,Cambalaalla ayirrinsannita ayyaanto barra faajje assitinota kulinohu Biironnihu qaru sooreessi kalaa Jaggo Sidaamunnihu diru soorro ayyaani akkalu dirinni haaru dirira riqiwannota ikkase qaagiissite ayyaanu budesinna horinyasi agadhino garinni iibbadu garinni ayirrisamannota ikkase kulino.

Fichee-Cambalaalla Sidaamunni sae UNISCote maareekkantunkunni Wogasenna donase tittirshunni maareekkinoonniha ikkanna,batinye gobbanna giddo Turiste beeqqaancho ikkitino baxxino ayyaana ikkaseno coyi'rino.

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ ክብረ በዓል እሴቶችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መጋቢት 02/2018 ዓ.ም
ሀዋሳ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስ ዝርዝር ከተመዘገበ 11ኛ ዓመት የሞላውና ዘንድሮ በልዩ ሁኔታ ስለሚከበረው ፍቼ-ጫምባላላ በዓል የበዓሉን እሴቶችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሲዳማ ቀደምት ሽማግሌዎች (አያንቶዎች) የስነ ከዋከብት እና ጨረቃ ምልከታ በማድረግ በዓሉ የሚከበርበትን ቀን ከመጋቢት 05_06/2018 ዓ.ም መሆን ቆርጠው ካሳወቁ በኋላ በሚከበረው በዚህ በሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል አሮገው ዓመት በአዲሱ የሚተካበት መሆኑን አስታውሰው በዓሉን ባህላዊ እሴቶችን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል።

ፊቼ ጫምባላላ ከሲዳማ እሴትነት አልፎ በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስ ዝርዝር መዝገብ ላይ መስፈሩን ተከትሎ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የሚታደሙት ልዩ በዓል መሆኑን ጠቁመዋል።

በፊቼ ጫምባላላ በዓል ቅድመ ዝግጅት የሲዳማ ሽማግሌዎች አዲሱን ዓመት የሠላም፣ የበረከት፣ የፍቅር፣ የደስታና የጥጋብ እንዲሆን ፈጣሪን በኡሱራ ጾም ጸሎት ይማፀናሉ፣ጥላቻና ቁርሾ ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ የሚወገድበት፤ ሽማግሌዎች ሀገር እንዲፀና የሚማፀኑበት መሆኑን ገልፀዋል ።

በዓሉ ለሲዳማ ብሔር ከዘመን መለወጫነት ባሻገር ትልቅ ትርጉም ያለው የማንነቱ መገለጫ፤ የነፃነትና የፍቅር ማዕድ ሁሉም በጋራ የሚቋደስበት፤ የመንፃትና የመታደስ፤ አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት፣በዳኤ ቡሹ እርስ በርስ ያላቸውን ፍቅር፣አክብሮትና ደስታ የሚገልጹበት፤በውስጡ ያሉ በርካታ እሴቶች በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች የሚገለጹበት፣ እርቅ የሚፈፀምበትና ሀዘን የሚያበቃበት አልፎ ተርፎም በዓሉ ስከበርም አብሮነትን፣አንድነትን ፣ፍቅርን፣ መረዳዳትን፣ መደማመጥን እንዲሁም መተባበርን የሚያጎሉ ድርጊቶችም የሚፈጸሙበት ነው ብለዋል።

አቶ ጃጎ አገኘሁ በመጨረሻም የዘንድሮው በፍቼ ጫምባላላ በዓል መጋቢት 05_06/2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ከወንድም ህዝቦች፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች ጋር በህብረት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ገልጸው በዓሉ ለመላው ሲዳማ ህዝብ፣ለኢትዮጵያና ለዓለም ህዝቦች የሰላም፣የደስታ፣የጤና እና የብልጽግና እንዲሆን ከወዲሁ ተመኝተው በዓሉን በጋራ ማክበር፣መንከባከብ፣ማድመቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

06/03/2026

ፊቼ-ጫምባላላ

Fiche Chambalala coming soon:::::::::::::::::::::Fiche Chambalala is new year festival of the sidaama's nation, and it i...
03/03/2026

Fiche Chambalala coming soon:::::::::::::::::::::
Fiche Chambalala is new year festival of the sidaama's nation, and it is a multi-purpose and true manifestation of the nation's way of life closely related to the truth of science and nature.

The festival will be celebrating March 14 and 15 /2026 in the beautiful city of Hawassa at regional, national and international level in the Great Gudumale at qexala and various events.

You are all invited to attend this wonderful and beautiful festival.
Hawassa,Sidama,Ethiopia
Visit Sidama
.travel

ፊቼ-ጫምባላላ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል እየደረሰ ነው፣፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥የዘንድሮው የፍቼ ጫምባላላ በዓል መጋቢት  5 ና 6 2018 ዓ/ም እንደሚውል  የሲዳማ አያንቶዎች/Ast...
26/02/2026

ፊቼ-ጫምባላላ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል እየደረሰ ነው፣፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
የዘንድሮው የፍቼ ጫምባላላ በዓል መጋቢት 5 ና 6 2018 ዓ/ም እንደሚውል የሲዳማ አያንቶዎች/Astronomy's/ ይፋ አድርገዋል፡፡ በዓሉ በኮርደር ልማት ብርሃን መስላ ባሸበረቀችው በተሞሽረችው በዉብቱዋ ሀዋሳ ከተማ በታላቁ ጉዱማሌ በቄጣላና በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል ፡፡
በመሆኑም መጋቢት 5ና 6/2018 ዓ/ም የሚከበረውን የፊቼ- ጫምባላላ በዓል ትዕይንት በቦታው ተገኝታችሁ እንዲትታደሙ ሁላችሁም ተጋብዛችሀል::
ይህን ደማቅ ማራክ ውብ አስደማም ባህላዊ ትዕይንቶች እንዳያመልጦት መጋቢት 5ና 6 2018 ዓ/ም ሲዳማ ሀዋሳ አይቀርም::
ኑ በዓሉን ይታደሙ ዉብቱዋን ሀዋሳን ሲዳማን ይጎብኙ
መጋቢት 5ና 6 አይቀርም
ሀዊሳ፣ሲዳማ ኢትዮጵያ
.travel
Sidama@

Address

Hawassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Sidama posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Visit Sidama:

Share