03/09/2026
ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት በሲዳማ!
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በበንሳ ዳዬ ከተማና በቡራ ወረዳ እየተካሄዱ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ይህ ጉብኝት በክልሉ እየተካሄደ ያለውን ፈጣንና ፍትሃዊ የልማት እንቅስቃሴ በተግባር ለመመልከት ያስቻለ ነበር።
ሲዳማ ክልል ከሆነ አጭር ጊዜ ቢሆንም፣ በሁሉም ዘርፎች የክልሉን ገጽታ የሚቀይሩና የሕዝቡን አጠቃላይ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ አበይት ሥራዎች ተከናውነዋል። በመንገድ፣ በከተማ ልማት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በሌሎች የመሠረተ ልማት ዘርፎች የተጀመሩና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች የሲዳማን የልማት ጉዞ ጥንካሬ በግልጽ ያሳያሉ።
ይህ ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ከሐዋሳ የኮሪደር ልማት ጀምሮ እስከ ሩቅ የገጠር ቀበሌዎች ድረስ መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት፣ የግብርና ምርታማነትን የማሳደግና የሕዝቡን ኑሮ የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
የልማቱ ፍትሃዊነትም የሚገለጸው በዚህ ሁሉን አቀፍ ተደራሽነቱ ነው፤ ልማት በከተሞች ብቻ ሳይወሰን ለገጠሩ ማኅበረሰብም እኩል እንዲዳረስ የሕዝቡን ፍላጎትና አቅም መሠረት ያደረጉ ሥራዎች በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በበንሳ ዳዬ ከተማና በቡራ ወረዳ የተጎበኙት የልማት ሥራዎችም የዚሁ ፍትሃዊ የልማት አቅጣጫ ሕያው ማሳያ ናቸው። ልማት በክልሉ ማዕከል ወይም በተወሰኑ ከተሞች ብቻ ሳይጠቃለል ወደ ሁሉም የሲዳማ አካባቢዎች እንዲደርስ ማድረግ የክልሉ መንግሥት መሠረታዊ መርህ ነው።
ከክልልነት በኋላ በአጭር ጊዜ የተመዘገቡ ስኬቶች የሕዝብ ተሳትፎን፣ የአመራር ቁርጠኝነትንና የጋራ ርብርብን የሚያሳዩ ናቸው።
የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ነሐሴ 28-2018 ዓ.ም