Sidaamu Da/Qo/Mo Industirete Latishshi Biiro/ሲዳማ ብ/ክ/መ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Hawassa
  • Sidaamu Da/Qo/Mo Industirete Latishshi Biiro/ሲዳማ ብ/ክ/መ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Sidaamu Da/Qo/Mo Industirete Latishshi Biiro/ሲዳማ ብ/ክ/መ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sidaamu Da/Qo/Mo Industirete Latishshi Biiro/ሲዳማ ብ/ክ/መ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ, Government Organization, Hawassa.

የአምራች ኢንዱስትሪ እመርታ፤ ለብዝኃ ኢኮኖሚ ከፍታ! #ጳጉሜ 1 የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ እመርታ ለሁለንተናዊ ከፍተቻን መሰረት ነው።
04/09/2026

የአምራች ኢንዱስትሪ እመርታ፤ ለብዝኃ ኢኮኖሚ ከፍታ!
#ጳጉሜ 1 የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ እመርታ ለሁለንተናዊ ከፍተቻን መሰረት ነው።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልል ደረጃ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡==============================ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም  የሲዳማ ክልል ...
04/09/2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልል ደረጃ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡
==============================
ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይረክቶረት

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባለፉት ዓመታት ንቅናቄው በሁሉም ክላስተር እቅድ አፈፃፀም በተገኙ ውጤቶች እና የቀጣይ ቀሪ አራት ዓመታት መካከለኛ ዘመን መነሻ እቅድ ዙሪያ ከፌደራል እና ከክልል ክላስተር የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት መድረክ ውይይት ላይ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሻሻሞ ሊቂሳ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልል ደረጃ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተለይም በክልሉ ንቅናቄው በከፍተኛ አመራሮች እንዲመራ በማድረግ በክልል ደረጃ የክላስተር አባላት በማደራጀት ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ለዘርፉ ውጤታማነት ተናባቢ የሆነ አደረጃጀት እስከታችኛው መዋቅር መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የማምረት አቅም አጠቃቀም በማሳደግ፣ እንቨስትመንትን በመሳብና የስራ ዕድል በመፍጠር ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል፡፡

ንቅናቄው ሲጀመር ከ760 ያልበልጡ አምራች ኢንዱስትሪዎች ነበሩ ያሉ ያሉት አቶ ሻሻሞ በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ ወደ 1 ሺህ 7 መቶ 4 በአነስተኛ፣ መካከለኛ፣ ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በክልል ደረጃ መድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡

ለአምራች ኢንዱስትሪው የብድር አቅርቦት፣ የኃይል አቅርቦት እና የመሰረተ ልማት በማመቻቸት የመስራያ ቦታ አቅርቦት በክልሉ በቅንጅት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ብርቅነሽ ሻንቆ በበኩላቸው ኢንዱስትሪዎች በስራ ላይ የሚያጋጠማቸውን ችግሮች በማረጋገጥ እንዲደገፉ በማድረግ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

በክልሉ የመስሪያ ቦታ በመስጠት፣ ብድር በማመቻቸት፣ የኃይል እጥረቶቻቸውን በመፍታት አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ወደ ውጤታማነት እንዲቀየሩ ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ባዛሮች በመዘጋጀት በአካባቢው ላይ ያሉትን አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበረሰቡ አውቆ ከእነሱ የሚያመርቱትን ምርት እንዲገዛ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡

በቅንጅት በጥበብ መስራት ከቻልን እንደ ሀገር በጂዲፒው(GDP) ላይ ኢንዱስትሪው ያለውን ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ ለማሳደግ የሁላችንም ጥረት እና እርብርብ የሚጠይቅ ስለሆነ በቀጣይነት አጠናክረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

👉የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

ለበለጠ መረጃ :-
➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

በሀዋሳ የምስራቅ ክ/ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የ2019 ዓመት ዕቅድ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።‎ነሐሴ 28/2018 ሲዳማ ክ/ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮት የሲ...
03/09/2026

በሀዋሳ የምስራቅ ክ/ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የ2019 ዓመት ዕቅድ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

ነሐሴ 28/2018 ሲዳማ ክ/ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮት

የሲዳማ ክልል በሀዋሳ ‎የምስራቅ ክፍለ ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የ2019 ዓመት ዕቅድ የንቅናቄ መድረክ በክፍለ ከተማዉ የሚገኙ በግልና በማህበር የተደራጁ የዘርፉ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል ።

‎የንቅናቄውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የሀዋሳ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ በሀይሉ ጌታቸው ባስተላለፉት መልዕክት በተናጠል ከሚደረገው እንቅስቃሴ ይልቅ እንደዚህ ባለው ህጋዊ ማዕቀፍ መደራጀት ተገቢ መሆኑን በማንሳት ሁሉም ለም/ቤቱ መጠናከር የበኩሉን እንድወጣም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ለበለጠ መረጃ :-
➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

የተኪ ምርት ስትራቴጂካዊ ሚናየኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለመቅረፍ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ እያ...
02/09/2026

የተኪ ምርት ስትራቴጂካዊ ሚና

የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለመቅረፍ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ እያካሄደ ይገኛል።

ይህ የተኪ ምርት ስራ ጅማሮ በዋናነት ያነጣጠረው በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን በሀገር ውስጥ በማስቀረት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ነው።

ቀደም ሲል የነበሩ የተበታተኑ የማምረት ሙከራዎችን ወደ ተቋማዊ አሰራር ለመቀየር ይፋዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጸድቆ ወደ ስራ ገብቷል።

ይህ ስትራቴጂ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚቆይ ፍኖተ ካርታ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ለትግበራው መፋጠን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደ ትልቅ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

ሀገራዊ ንቅናቄው በ2016 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ለጀመረው ብሔራዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ትልቅ አቅም የፈጠረ ነው።

የስትራቴጂው መውጣት እና ወደ ተግባር መግባት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማስገኘት ጀምሯል።

ትልቁ እና ዋነኛው ፋይዳም የውጭ ምንዛሬን ማዳን ሲሆን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸው የምርት ድርሻ ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅምም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ብሏል።

ይህ መነቃቃት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ከመሆኑም በላይ የፋብሪካዎችን የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ምርቶች ጋር በማስተሳሰር የአቅርቦት ሰንሰለቱን አጠናክሮታል።

ይህንኑ ሀገራዊ ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች ላይ የዘርፉን ስልታዊ ጠቀሜታ በተደጋጋሚ አንስተዋል።

በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የምግብ እና የማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል በመጥቀስ፣ የሀገር ውስጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ኢትዮጵያን የምግብ እጥረት እንደታደጋት ገልጸዋል።

ተኪ ምርት ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነት እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይወጣባቸው የነበሩ የድንጋይ ከሰል እና የችፑድ ምርቶች አሁን ላይ በሀገር ውስጥ በስፋት እየተመረቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥራትን መሰረት አድርገው በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከተኪ ምርት ስራዎች ያገኘውን ስኬት ይበልጥ ለማስፋት እና ዘላቂ ለማድረግ አዳዲስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ግቦችን አስቀምጧል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት የሀገር ውስጥ አምራቾችን የገበያ ድርሻ ወደ 49 ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ቁጠባውን ወደ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ለዚህም ስኬት አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ምርቶቻቸውን ያለ ደላላ ለገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የዲጂታል የገበያ ትስስር ፕላትፎርም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ይፋ ተደርጓል።

ወደፊትም ከቀላል የሸማች ዕቃዎች ባለፈ እንደ ተሽከርካሪዎች፣ ኬሚካሎች እና ብረታብረት ያሉ አስራ አምስት ስልታዊ የከባድ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመተካት ባለፈ የማኑፋክቸሪንግ ወጪ ንግድ ገቢን በማሳደግ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ተወዳዳሪ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ተሰንቋል።

በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የተኪ ምርት ስራ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ምርታማነት እያሸጋገረ የሚገኝ ስልታዊ እርምጃም ነው።

በጥናት የተለዩት 96 ቁልፍ ስልታዊ ምርቶች በሙሉ አቅም ወደ ማምረት መሸጋገራቸው ለሀገር በቀል እውቀትና ለፈጠራ ስራዎች ሰፊ በር ከመክፈቱም በላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ላይ ያላትን የድርድር እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል።

ለበለጠ መረጃ :-
➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

''Gobbanke Laalcho Hidhino'' Yaanno Birxichinni Daddalu Lamala Lainse Qixxeessinoonni Bare Harinsani Hee'noonniWoxawaajj...
31/08/2026

''Gobbanke Laalcho Hidhino'' Yaanno Birxichinni Daddalu Lamala Lainse Qixxeessinoonni Bare Harinsani Hee'noonni

Woxawaajje 25/2018 M.D Qoqqowu industirete latishshi biiro kominikeeshinete hajo Dayirkitore

Barete Leelle Sokkasi Sayiisinohu Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Prezidaantichi Kalaa Desti Ledamohu Daddalu Sidaami Dagara Kaajjado Horo Aanno Gede Massaga Hasiisanno Yino. Loosu Tekinoolojete Dukkisame Lifixa Owaante Aanno Gede Massagatenni Seeru Giddo Worroonni Garinni Calla Kaajjado Qorqorsha Assinanni Massaga Hasiisannota Xawisino. Tennera Hajo La'annonsa Bissa Daddalunna Dikkote Latishshi Biiro Ledo Halante Loosa Noonsata Xawisino.

Sidaami Deerrinni Daddalu Budi Jawaata Ikke Dagate Beeqqono Kaajjinshe Jiro Kalaqira Hasiissanno Yee Daddalu Baalanta Heeshshote Ikkitubba Kikkisanno Daafira Kaayyo Seekke Horoonsira Hasiisanno Yino. Daddalu Jirote Buicho Ikkase Anfe Loosate Qarrissanno Ikkitubba Xinqe Tiratenni Dagate Horaameessimma Buuxisiisa Noota Xawise Aantete Kaajjado Sharro Assatenni Halamme Baxxino Illachinni Loosa Hasiisannota Huwachishino.

SDQM Daddalunna Dikkote Latishshi Biiro Sooreette Baabba Selaamaawit Makuriti Ise Widoonni Konni Albaanni Daddalu Poolise Nookkiha Ikkitte Keeshsh*tinoha Ikkanna Xa Kayiinni Tini Poolise Qixxaawaase Lowo Kaayyo Kalaqqino Yitino. Gobbate Giddo Laalcho Hidhate Hajo Lowo Horo Afidhinota Kulte Kalqete Sonase Soorritanni Qarrissino Dikkote Akati Qarra Tirate Kaa'litanno Yitino.
168 Daddalu Uurrinshubba Beeqqitanno Yine Agarranni Baazare Aantete Faajjete Fannannitano Biirote Sooreette Xawissino.

Barete Sidaamu Qoqqowi Xaphooma Yoo Mini Prezidaantichi Kalaa Damisse Dullachihu, Qoqqowu Loosu Massagaano,Hawaasi Quchumi Kantiiwi Kalaa Xiraatu Beyyenehu, Zoonnatennte, Woraddatenna Quchummate Massagaano, Daddalaanonna Woshshatto Assinoonninsari Hajo La'annonsa Bissa Beeqqitanni Afantanno.



Woriidi Mashalaqqete Teesso Kissine Industirete Latishshi biiro Maate Ikke❗️

➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ በአፍሪካ መድረክ ለሚያደርገው ተሳትፎ የአሸኛኘትና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነውኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ መድረክ ለሚሳተፈው የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለ...
30/08/2026

ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ በአፍሪካ መድረክ ለሚያደርገው ተሳትፎ የአሸኛኘትና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ መድረክ ለሚሳተፈው የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የአሸኛኘትና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

መርሐግብሩ በ2018 ዓ.ም ዓመቱን ሙሉ ሊጉን በመምራት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ለሆነው ለሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ በቀጣይ አፍሪካ መድረክ መልካም ዕድል እንዲገጥመው የክብር አሸኛኘት ማድረግንና ክለቡን በገንዘብ ለመደገፍ ገቢ ማሰባሰብን ታሳቢ ያደረገ ስሆን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶች*************************** የአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የ...
30/08/2026

ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶች
***************************

የአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚረጋገጠው ከውጭ ጥገኝነት ተላቅቃ የራሷን ፍላጎት በራሷ ማምረት ስትችል ነው።

የመደመር መንግሥት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የጀመራቸው “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ እና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማነቃቃት አስደናቂ ለውጦችን ማምጣት ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአፈጻጸም ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከውጭ ጥገኝነት በመላቀቅ የሀገር ውስጥ አቅምን ወደ መገንባት በተኪ ምርት የተሳካ ሽግግር እያደረገ ይገኛል።

የማምረት አቅም ማደግ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሚና

ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከነበራቸው የማምረት አቅም ከግማሽ በታች (በአማካይ 47 በመቶ) ብቻ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም በኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግሮች የተተበተበ ነበር።

ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ እንዳብራሩት፣ አሁን ላይ አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል።

የዚህ ከፍተኛ ለውጥ ዋነኛ ሞተር በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እየተመራ ያለው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በተለያዩ ምክንያቶች ተዘግተው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ፣ እንዲሁም የአምራቾችን የፋይናንስ እና የመሠረተ ልማት ማነቆዎች በመፍታት ምርታማነትን በእጅጉ አነቃቅቷል።

➡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ምቹ የኢንቨስትመንት መሠረተ ልማት ማቅረብ ነው። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ነባር ከሆኑት የኮምቦልቻ፣ የመቐለ እና የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ ዐሥር አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ተችሏል።

የእነዚህ ፓርኮች መስፋፋት የሀገር ውስጥ አቅምን ከማጎልበት ባለፈ፣ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለመሳብ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

የውጭ ኢንቨስተሮች ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያመጡ እና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።

➡ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት፦ የ5 ቢሊዮን ዶላር ስኬት

ለዘመናት የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሲፈታተን የነበረው ዋነኛ ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በገቢ ምርቶች ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት ነበር።

ይህንን ለመቀልበስ "የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት" ስትራቴጂ በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ብርጭቆ እና ሴራሚክስን የመሳሰሉ ከባድ እና ወሳኝ የግንባታ/የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ብቻ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል።

መንግሥት ቀደም ሲል በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሒደት በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ፖሊሲውን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

በግብርናው (በተለይም በስንዴ ምርት) የተገኘው የገቢ ምርትን የመተካት ስኬት ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍም በተጨባጭ ተሸጋግሯል።
➡ የተቀናጀ የዘርፎች ዕድገት

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ መነቃቃት በሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይም አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። የኢንዱስትሪ ዕድገት ብቻውን ሊመጣ አይችልም፤ ኃይል እና የጥሬ ዕቃ ግብዓት ይፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘርፉ እያስመዘገበ ባለው ፈጣን ዕድገት ምክንያት፦ በማዕድን ዘርፍ 24 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20.3 በመቶ፣ እና በኢነርጂ ዘርፍ 23 በመቶ ጭማሪ መታየቱን አብራርተዋል። እነዚህ ሦስቱ ዘርፎች (ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኢነርጂ) እርስ በርስ በመመጋገባቸው የመጣ "የተቀናጀ ዕድገት" (Synergy) መሆኑን ያሳያል።

➡ የወደፊቱ አቅጣጫ እና ራዕይ

የተገኙት ስኬቶች የጉዞው ጅማሮ እንጂ ማቆሚያ አይደሉም። ይህንን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ በመጪው ዓመት ግልጽ ዒላማዎች ተቀምጠዋል። እነዚህም፦

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ የ12.7 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ እና ከኢንዱስትሪ ምርቶች ኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) የ1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ሲሆኑ ለስኬቱም በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እውነተኛ ዕምርታ እያሳየ ነው። “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚለው ብሔራዊ ንቅናቄ በመመራት፣ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ማሳደግ ተችሏል።

አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመክፈት ኢንቨስትመንትን መሳብ እና ቁልፍ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉም ሀገራችን ከሸማችነት ወጥታ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች አምራች ኢኮኖሚ ወደ መገንባት የተጨበጠ ዕርምጃ መጀመሯን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ራዕዩ ግቡን ሲመታም፣ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብልጽግናዋ ዋነኛ የጀርባ አጥንት መሆኑ አይቀርም።



ለበለጠ መረጃ :-
➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

Sidaamu Qoqqowi Mootimmate Owaante Woyyeessate Uurrinshuwate Riforme Assinanni Gede Qoqqowu Kaabine Gumultu***********‎‎...
28/08/2026

Sidaamu Qoqqowi Mootimmate Owaante Woyyeessate Uurrinshuwate Riforme Assinanni Gede Qoqqowu Kaabine Gumultu
***********

‎Sidaamu Qoqqowira deerra deerranko mootimmatenni uynanni owaante rakkinota, lifixanna owaatamaanote tootayyaaw ajishshannota hattono, qansootu kasseenya luphi assitannota ikkitanno gede uurrinshuwate riforme assinanni gede qoqqowu kaabine gumultino.

‎Qoqqowoho dagate fakkana owaante uytanno uurrinshuwa giddonni Hawaasi Quchuminna Sidaamu Qoqqowi Hodhishshu Biiro uytanno owaante lainohunni noo mitiimma bande xiinxallo assinoonni.

‎Hatte uurrinshuwa sooreeyye mitiimma baddenna malu doorshuwa xiinxallatenni shiqishshino ripoorteno qoqqowu kaabine hajo la'annonsa bissa ledo seekkite keentino.

‎Kaabine keenotenni bandoonni hajubba la'e; taalannore taashsh*te; shiqqino riformete doorshuwa loosu aana hossanno gede gumultino.

‎Uurrinshuwate riformeti qara mixono mootimma uytanno owaante lifixanna baalanko iillitannota assatenni owaatamaanote yannanna fulo ajishatenninna ragiweelo orao hoolatenni qansootu kasseenna luphi assate ikkase Pirezidaantichu Borro Mini taje leellishshanno.

በሲዳማ ክልል የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማሻሻል የተቋማት ሪፎርም እንዲካሄድ በክልሉ ካቢኔ ተወሰነ

ነሐሴ 22/2018 የሲዳማ ክ/ኢ/ል/ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይረክቶሬት

በሲዳማ ክልል በየደረጃው በመንግሥት የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና የተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንሱ እንዲሁም የዜጎችን እርካታ የሚያሳድጉ እንዲሆኑ የተቋማት ሪፎርም እንዲካሄድ በክልሉ ካቢኔ ተወስኗል።

በክልሉ ሰፊ የሕዝብ ተጠቃሚነት ካላቸው ተቋማት መካከል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ ያሉ ችግሮች ተለይተው ጥናት ተካሂዷል።

የተቋማቱ ኃላፊዎች ችግሮቹን በመለየት እና የመፍትሔ አማራጮችን በማጥናት ያቀረቡት ሪፖርትም በክልሉ ካቢኔ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በጥልቀት ተገምግሟል።
ካቢኔው በግምገማው የተለዩ ጉዳዮችን በመመልከት ተጨማሪ ማሻሻያዎችን በማከል የቀረቡት የሪፎርም አማራጮች ተግባራዊ እንዲሆኑ አጽድቋል።

የተቋማት ሪፎርሙ ዋና ዓላማም የመንግሥት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ፤ የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ በመቀነስ እና አላስፈላጊ እንግልትን በማስወገድ የዜጎችን እርካታ

ለበለጠ መረጃ :-
➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

27/08/2026

Sidaamu Qoqqowi Industirete Latishshi biiro 2018 B.D Gumulshira Luphiima Guma Maareekkisiisse Gobbate Deerrinni Baraarsha Afidhinohura biirote loosaasine ledo Hagiirre xawisate Amanyoote Assini yannara......

Ledamate, halamatenna qinaawatenni luphiima guma Maareekkisiinsoonnita Industirete latishshi biiro xawissuWoxawaajje 20/...
26/08/2026

Ledamate, halamatenna qinaawatenni luphiima guma Maareekkisiinsoonnita Industirete latishshi biiro xawissu

Woxawaajje 20/2018 M.D Qoqqowu industirete latishshi biiro kominikeeshinete hajo Dayirkitore

Sidaamu Qoqqowi Industirete Latishshi biiro 2018 B.D Gumulshira Luphiima Guma Maareekkisiisse Gobbate Deerrinni Baraarsha Afidhinohura biirote loosaasine ledo Ledamate, halamatenna qinaawatenni luphiima guma Maareekkisiinsoonnita biirote sooreessi kalaa Ashaagire Jenberehu xawisi.

Ledoteno, Luphiima guma Maareekkisiisate guulcho hajubba, Haaro industire kalaqa, Laashate dhukki horo lossa, Gobbara sonkanni laalcho bikkunni leda, Riqiwote laalcho gobbate giddo laashshal, Gobbara sonke afi'nanni doolaare leda, hattono, qansootaho Loosu kaayyo kalanqoonnita biirote sooreessi lede huwachiishino.

Sidaamu Dagoomu qoqqowi amaale mine quchumunna xintu latishshi hajubba uurrinshu komite Gambisaancho Ayirrado Dukko Mintiwaab G/mesqeliti Coyidhanni , Biiro Gobbomu deerrinni heewisante luphiima guma Maereekkisiisinohura hawalle hagiidhinoommo yite, biirote deerrinni Loonsoonni loosinni gobbate deerrinni assinoonni heewora guma mareekkisiisse afansha afirase wole uurrinshubbara lawishsha ikkitanota xawissino.

Xaphoomunni Qoqqowu Mootimma Laashaano Indusitirera uyitino illachi onte Diro Aante deerra fulatenni afansha afi'noonniha ikkanna kunni gumi halamaano bissa ledo ledamate,halamatenna qinaawatenni dayinoha ikkasinni, aantetenno woyyaawino gumira kakkayisannota xawinsoonni.

Woriidi Mashalaqqete Teesso Kissine Industirete Latishshi biiro Maate Ikke❗️

➚ webise:_ https://www.sbid.gov.et/
➚Fecebook፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100095093058023
➚Telegram፦https://t.me/Sidaamu_Indu_Lat_Biir
➚WhatsApp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbBKATbFMqrTdW3oFy1F
➚YouTube https://www.youtube.com/.Industry

Address

Hawassa

Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Tuesday 02:30 - 11:30
Wednesday 02:30 - 11:30
Thursday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 10:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidaamu Da/Qo/Mo Industirete Latishshi Biiro/ሲዳማ ብ/ክ/መ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share