NETSA Ethiopia 2007

NETSA Ethiopia 2007 This page is created to aware people about the abuse of freedom by the weyane/hiwehat/ mafia group a

15/08/2014

እነሆ 2006 ዓ.ም ማብቂያ ለይ ደርሰናል፡፡ የክረምቱ ወቅትም ብዙ ሳናስተውለው እያለቀ ነው፡፡ ለምን ብዬ ሳስብ የብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ደህና ሳያዘናጋን አልቀረም፡፡ አሁን ደግሞ ከአንድ ቀን በኋላ አብዛኛዎቻችን የምንዝናናበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች ይጀመራሉ፡፡ የዘንድሮውን ውድድር ቼልሲ ያሸንፋል የሚል ቅድመግምት በ ጎል/goal.com/ ድረ ገጽ ለይ አንብቢያለሁ፡፡ ለማንኛውም ለኛ ለወጣቶች አሪፍ መዝናኛ እንደሚሆን እጠብቃለሁ፡፡
ከዚህ ባሻገር በአገራችን ፖለቲካ ላይም ከፍተኛ የሆነ የስርዓት ለውጥ የምናካሄድበት ጊዜ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ እድሜ ለቴክኖሎጂ ሁላችንም አገራችን ስላለችበት የእድገት ደረጃ ወያኔ እንደሚነግረን ከ ደርግ አንጻር ሳይሆን ከዓለም አገሮች አንጻር እጅግ ኋላ ቀር እንደሆንን ተረድተናል፡፡ ሲጀመር በግሎባላይዜሽን ዘመን እና የአንድ አገር እድገት በወጪ ገቢ ንግድ ለይ መሰረት ያደረግ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ እንዴት ወያኔ እራሱን ከሞተ ስርዓት ከደርግ ጋር እንደሚያወዳድር ሁላችንንም ግራ አጋብቶናል፡፡ ለማንኛውም አሁን አውቀናል ነቅተናልም፡፡ በወያኔ ስርዓት አይደለም የዛሬ 20 ዓመት የዛሬ 200 ዓመትም አናድግም፡፡ ምክንያቱም ከሌላው ዓለም አንጻር የአገራችን እድገት ባለህበት እርገጥ እንደሚባለው ነው፡፡ እኛ ወጣቶችም ይህንን በሚገባ ተረድተናል/ለአንድ አመት ያክል ባደረኩት ጥናት/፡፡
በመሆኑም ይህን ሊሞት እያጣጣረ ያለ እና አገርን የመምራት እውቀቱም ሞራሉም የሌለውን የወንበዴዎችና አገር ቦጥቧጮች/ዘራፊዎች/ ቡድን ታግለን የምናስወግድበት ዓመት ይሆናል፡፡
ድል ለሰፊው የኢትዮጲያ ሕዝብ!!!!!!!!!!!!

30/05/2014

ወያኔን ለምን ጠላነው?
ይህ ቡድን ስልጣን ከያዘ እነሆ 23 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡አንድ ትውልድ ተተካ ማለት ነው፡፡ዛሬም ድረስ ግን ከጥቂቶች በቀር ቀሪው የሀገራችን ህዝብ በድህነት እና ኌላቀርነት ህይወት ውስጥ እንገኛለን፡፡እነዛ ጥቂቶቹ ስልጣን ላይ ያሉት ሀገሪቱን እየዘረፉ ግዙፍ ህንጻዎችን እና ፋብሪካዎችን ገንብተዋል; እየገነቡም ይገኛሉ፡፡በግብርና ስራ የሚተዳደረው አብዛኛው ህዝብ ግን ዛሬም ድረስ የእርሻ ስራውን የኌላቀርነት መገለጫ በሆነው በጋማ ከብቶች እየሰራ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ እየገፋ ይገኛል፡፡በዚህ አይነት አሰራር ደግሞ መቼም ቢሆን እድገት አይመጣም፡፡በጣም የሚገርመው ደግሞ የተፋሰስ ስራ ተብሎ ሜዳማ መሬት ላይ አርሶአደሩ ቦይ እንዲቆርጥ ይደረጋል፡፡ከዛ በኌላ ምርቴ በሶስት እጥፍ ጨመረ በል ተብሎ በኢቲቪ ይቀርባል፡፡እንግዲህ በዚህ መልክ ነው ወያኔ ከ 85% በላይ ለሆነው የሀገራችን ህዝብ ለውጥ እና ዕድገትን አመጣለሁ ብሎ የተስፋ እንጀራ እየመገበ 23 ዓመታት ባክነው ያለፉት፡፡
እነዚህ ቡድኖች/ህወሃት/ ታዲያ አገሪቱ እና ህዝቡ ላይ እየቀለዱ እና እየገደሉን አይደል እንዴ; በቃን! ወያኔ በቃን በቃችሁ!!ለውጥ እና ዕድገት እንፈልጋለን፡፡
ነጻ እና ሁሉም በእኩልነት ሰርቶ የሚኖርባት የበለጸገች ኢትዮጲያን እውን እናደርጋለን!!!

29/05/2014

Hello,
It is time to wake up of our deep sleep once again.We have to get back our freedom by 2007 E.C, weather by the fake electoral drama of EPRDF or by the option the group brings.FREEDOM FREEDOM FREEDOM!

Address

Hawassa
147

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NETSA Ethiopia 2007 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share