Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/

Ethiopian Food  and  Drug Authority /EFDA/ Address up-to-date regulatory information about the safety, quality, efficacy, rationale use and performance of regulated products.

ራዕይ

በአፍሪካ ውስጥ በምግብ እና በጤና ምርቶች ቁጥጥር የልህቀት ማዕከል መሆን፡፡

ተልዕኮ

ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ምርቶች ደህንነት፣ ውጤታማነት፣ ጥራት እና ትክክለኛ አጠቃቀም በፈቃድ፣ በምርመራ፣ በምዝገባ፣ በላብራቶሪ ምርመራ፣ በድህረ-ገበያ ክትትልና በማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲሁም ወቅታዊ የቁጥጥር መረጃ በማቅረብ የህዝብ ጤናን መጠበቅና ማሻሻል፡፡

Africa Avenue, near wolosefer, Kirkos sub city, 02/03 kebelle, 02

http://www.fmhaca.gov.et/
E-mail [email protected]
Telegram
https://t.me/ethiopianfoodanddrugauthority
YouTube channel link

 #የምግብ  #ደህንነት  #የሁሉም  #ሰው  #ጉዳይ ነው!ምግባችን ደህንነት የሚወሰነው በምግብ ሰንሰለት ሂደት ማለትም ከምርት እስከ ተጠቃሚው ባለው ሂደት ጥሩ ልምዶች እና ጥሩ ግንኙነት  በ...
03/06/2026

#የምግብ #ደህንነት #የሁሉም #ሰው #ጉዳይ ነው!
ምግባችን ደህንነት የሚወሰነው በምግብ ሰንሰለት ሂደት ማለትም ከምርት እስከ ተጠቃሚው ባለው ሂደት ጥሩ ልምዶች እና ጥሩ ግንኙነት በማድረግ ሁሉም ሰው የበኩሉን ሚና ሲተገብርና በመመሪያው መሰረት የበኩሉን ሃላፊነት ሲወጣ ነው። በማንኛውም የምርት ሂደት ሰንሰለት ውስጥ ያለ አምራቹ፣ አስመጪዉ፣ አጓጓዡ፣ አከፋፋዩ፣ በችርቻሮ ንግድ ላይ ያለዉ ፣ ምግብ የሚያዘጋጀውና የሚያቀርበው እንዲሁም ተጠቃሚውን ጨምሮ ሁሉም ሊያከናውነው የሚገባውን ለምግብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን ምግብ ደህንነት ይጠበቃል። ስለሆነም የምግብ ደህንነትን ማስጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው።

27/05/2026
ተቋማዊ ትልሞችን ለማሳካት አመራሮች ውጤታማ የተግባቦት ስራን በምሳሌነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ቢሾፍቱ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድ...
26/05/2026

ተቋማዊ ትልሞችን ለማሳካት አመራሮች ውጤታማ የተግባቦት ስራን በምሳሌነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ቢሾፍቱ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ለማኔጅመንትና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በአዘጋጀው ውጤታማ የመሪነት ተግባቦት ስልጠና ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ስራዎችን ለማሳለጥ አመራሮች ዘርፈ ብዙ የተግባቦት ሰራዎችን በትኩረት ሊከውኑ ይገባል ለዚህም ወርደው ሰርተው ማሳየት ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡
እያንዳንዱ አመራር በወሰደው ስልጠና መሰረት ለተቋሙ ኮሙኒኬተር በመሆኑ የተግባቦት ስራን በንቃት መከወን ግዴታው እንደሆነ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ በየሩብ ዓመቱም በመገናኛ ብዙሀን በኩል ለህብረተሰቡ የተሠሩ ስራዎችን ማሳወቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
አመራሮች ካገኙት ስልጠና ተነስተው የተቋሙን የ3 ዓመት የኢንቨስትመንትና የልማት ዕቅድ እንዲሁም ከሚዲያና ከባለድርሻ አካላት አንፃር ሊደረጉ የሚገባቸው የተግባቦት ስራዎችን ከወዲሁ ማሰብ እንዳለባቸው ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል፡፡
ስልጠናው በቀጣይነት ለቡድን መሪዎችና ለዴስክ ኃላፊዎች እንደሚሰጥም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የባለሥልጣኑ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጋራ የዕቅድ ግመገማ መድረክ ችግር ፈቺና ውጤታማነትን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋፆ እያደረገ መምጣቱ ተገለፀ፡፡ግንቦት 14/2018 ዓ.ም ጅማ፡-  የባለስ...
22/05/2026

የባለሥልጣኑ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጋራ የዕቅድ ግመገማ መድረክ ችግር ፈቺና ውጤታማነትን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋፆ እያደረገ መምጣቱ ተገለፀ፡፡
ግንቦት 14/2018 ዓ.ም ጅማ፡- የባለስልጣኑ 3ኛው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የጋራ የዕቅድ ግምገማ መድረክ በጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲጀመር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የባለስልጣኑ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማስተባበሪያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ ቀጠለ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በድሬዳዋና በሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከተካሄዱ የእቅድ ግመገማ መድረኮች ወዲህ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በኩል የሚከወኑ የቁጥጥር ስራዎች ችግር በመፍታም ሆነ ውጤታማነትን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተዋል፡፡
የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በቃሉ አረጋ በበኩላቸው የግምግማ መድረኩ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የግምገማ መድረክ በባለስልጣኑ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጠው መምጣቱን ጠቁመው የብቃትና ሰው ሀብት፣ ግዥና ፋይናንስ፣ እስራቴጂክ ጉዳዮች እና የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን የመሳሰሉት የሥራ ክፍሎች በመድረኩ እንዲሳተፉ ማድረግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚያነሷቸውን ማነቆዎች ለመፍታት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
በ3ኛው የባለስልጣኑ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የጋራ የዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ የሰባቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም፣ የምግብ ማበልጸግ፣ የፋርማሲ ቤቶች ደረጃዎችን የማስተግበር እና ከክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር በቅንጅት ስለሚሠሩ የቁጥጥር ስራዎች በተመለከተ የተገኙ ስኬቶች ፣ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ምርጥ ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውስጥ ጥራት ያላቸውና ስነ-ምግባራዊ የህክምና ሙከራዎች ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- ይፋ...
21/05/2026

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውስጥ ጥራት ያላቸውና ስነ-ምግባራዊ የህክምና ሙከራዎች ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- ይፋዊ የምረቃ ስነ-ስርዓቱን በይፋ የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤት ክብርት ፍሬህይወት አበበ እንደተናገሩት የኤልክትሮኒክ የህክምና ሙከራ ስርዓት የህክምና ሙከራ የአሰራር ሂደቶችን ዘመናዊ ለማድረግ፣ ግልጽነትን ለማሳደግ፣ የጊዜ እና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ እንዲሁም ተመራማሪዎች ፍትሃዊ እና ቀላል አገልግሎት እንዲያገኙ ታላቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

የባለስልጣኑ የህክምና ሙከራ ኤልክትሮኒክ የቁጥጥር የመረጃ ስርዓት ይፋ ማድረጊያ ስነ-ሥርዓት ሲካሄድ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን የህክምና ሙከራ ቁጥጥር በዓለም አቀፍ የህክምና ሙከራ መመዘኛዎችን ለማሟላት ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የአደረጃጀትና የአሰራር ለውጥ አድርጎ በርካታ ውጤቶች አግኝቷል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውስጥ ጥራት ያላቸውና ስነ-ምግባራዊ የህክምና ሙከራዎች ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆን ጠቀሙው ዛሬ በይፋ የተመረቀው የባለስልጣኑ የህክምና ሙከራ ኤልክትሮኒክ የቁጥጥር የመረጃ ስርዓት የዚህ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የህክምና ሙከራ እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና ሰርተፍኬት ከክብርት ሚኒስትር ድኤታ ፍሬህይወት እጅ ተቀብለዋል፡፡

የምግብ አምራቾችና አስመጪዎች አገሪቷ ያወጣቸውን ደረጃዎችና ደንቦች በማክበር መሥራት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡ግንቦት 11/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ፡-የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት  ባላስልጣን...
19/05/2026

የምግብ አምራቾችና አስመጪዎች አገሪቷ ያወጣቸውን ደረጃዎችና ደንቦች በማክበር መሥራት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡

ግንቦት 11/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ፡-የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባላስልጣን የበለጸጉ ምግቦች እና ማበልጸጊያዎች የመልካም አመራረት ስርዓት ቁጥጥር መመሪያ ለማጠናከር የሚያስችል ተጨማሪ
ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦች ለማሰባሰብ ያለመ ከስንዴ ዱቄት እና ከምግብ ዘይት አምራቾችና አስመጪዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የምግብ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ እያደገች እና በለውጥ ጎዳና ውስጥ ያለች በመሆኑ ጤናማ አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር የተመጣጠነ እና ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ ምግብ ለህብረተሰቡ መቅረብ እንዳለበት ገልፀው በዚህ ሂደት ውስጥ የምግብ መበልፀግ አንዱና ወሳኝ ተግበር መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ለዚህም ካውንስል ተቋቁሞ የምግብ ደረጃዎች ተዘጋጅተው ለገበያ እንዲቀርቡ ተወስኗል፡፡በዚህም መሠረት የሀገሪቷን ደረጃ አሟልተው ለገበያ የሚቀርቡት የስንዴ ዱቄትና የምግብ ዘይቶች ላይ ጥሩ መሻሻሎች አሉ ብለዋል፡፡
በክልል ደረጃም በተለይ በምግብ ዘይት የመበልፀግ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን የድህረ-ገበያ ቁጥጥር ስራዎች እንደሚያመለክቱ አብራርተዋል፡፡

Address

Ethiopian Food And Drug Authority/EFDA/የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
Hawassa
5681

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/:

Share